ሰውነት ቢሻው የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን አሳወቁ

ከ10 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ለሚደረገው የሃገር ውስጥ ሊግ ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ቻን ውድድር እየተዘጋጀች የምትገኘው ኢትዮጵያ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን አሳውቃለች ፡፡

በመጀመርያው የ27 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ያልነበረው አበባው ቡታቆ በስብስቡ ውስጥ ውስጥ ሲካተት ግብ ጠባቂው ሲሳይ ባንጫ ከምርጫው ተዘሏል፡፡ ግልፅ ምክንያት ባይቀርብም የደደቢቱ ግብ ጠባቂ ራሱን ከምርጫው እንዳገለለ ተነግሯል፡፡

ከ27 የመጀመርያ ተመራጮች መካከል የንግድ ባንኩ መሃሪ መና ፣ የአርባምንጮቹ ገ/ሚካኤል ያዕቆብ እና ሙሉአለም መስፍን ፣ የደደቢቱ ሽመክት ጉግሳ ፣ የሲዳማ ቡናው ሞገስ ታደሰ በ23 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል፡፡

የመጨረሻ 23 ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው(ኢ/ቡና) ፣ ደረጄ አለሙ (ዳሸን ቢራ) ፣ ታሪክ ጌትነት (ደደቢት)

ተከላካዮች

አበባው ቡታቆ(ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ሳላዲን በርጊቾ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ቶክ ጄምስ (ኢ/ቡና) ፣ ስዩም ተስፋዬ (ደደቢት) ፣ ብርሃኑ ቦጋለ (ደደቢት) ፣ አሉላ ግርማ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ደጉ ደበበ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ አይናለም ኃይለ (ዳሸን ቢራ)

አማካዮች

ፋሲካ አስፋው (ኢ/ቡና) ፣ አስራት መገርሳ (ዳሸን ቢራ) ፣ በኃይሉ አሰፋ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ምንያህል ተሸመ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ታደለ መንገሻ (ደደቢት) ፣ አዳነ ግርማ (ቅ/ጊዮርጊስ) ፣ ኤፍሬም አሻሞ (ኢ/ቡና) ፣ ምንተስኖት አዳነ (ቅ/ጊዮርጊስ)

አጥቂዎች

ማናዬ ፋንቱ (መከላከያ) ፣ ዳዊት ፍቃዱ (ደደቢት) ፣ ኡመድ ኡኩሪ (ቅ/ጊዮርጊስ)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቻን ውድድር የመጀመርያ ጨዋታውን ጃንዋሪ 13 ቀን 2014 ከ ሊቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል ፡፡ ከዛ ቀደም ብሎ የፊታችን ቅዳሜ ከናይጄርያ አቻው ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ