ካለፈው ህዳር ወር አንስቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሲያሰለጥኑ የቆዩት ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ማርት ኖይ የታንዛንያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ቀጣዩ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ የሚሆነው በራሳቸው ማርት ኖይ ጠቋሚነት ከውጪ እንደሚመጣ ልሳነ ጊዮርጊስ ዘግቧል፡፡
በማርት ኖይ ጠቋሚነት በእጩነት የተያዙት አሰልጣኞች የስራ ልምዳቸውን እና ማስረጃቸውን እንደሚልኩ ሲጠበቅ አሰልጣኙ ወደ ታንዛንያ ከማምራታቸው በፊት እጩዎቹ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡም ጨምሮ ዘግቧል፡፡
አሰልጣኙ በይፋ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተያይተው የታንዛንያ ስራቸውን የሚጀምሩት የማርች ወር ከተጠናቀቀ በኋላ ሲሆን እስከ ኤፕሪል መጀመርያ አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ማርት ኖይ በታንዛንያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው የሚከፈላቸው የደሞዝ መጠን 13ሺህ ዶላር ሲሆን ከቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አባላት ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት ኮንትራታቸው ሳይፈርስ ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ጎን ለጎን ክለቡን የማማከር ተግባር እንዲፈፅሙ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
{jcomments on}