የኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ከ2 ሳምንት በኋላ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ሩብ ፍፃሜ የሚካሄዱበትን ቀናት አስታውቋል፡፡ ሁሉም ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄዱበት ውድድር ዘንድሮ 16 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ብቻ እየተሳተፉበት ሲሆን የመጀመርያ ጨዋታዎች ህዳር 30 እና የካቲት 12 መካሄዳቸው ይታወሳል፡፡


ሀረር ቢራን ማክሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2006 .. የሚገጥመው የአምናው ሻምፒዮን መከላከያ በተከታታይ ጨዋታዎች ከገባበት የውጤት ቀውስ ለመውጣት ይህ ጨዋታ ወሳኝ ነው፡፡ሁለቱ ቡድኖች ለሩብ ፍፃሜ የመቁት መከላከያ ወላይታ ዲቻን 1-0 ሀረር ቢራ ደግሞ መብራት ኃይልን በመለያ ምቶች አሸንፈው ነው፡፡

የአምናው የፍፃሜ ተፋላሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ላይ ይካሄዳል፡፡ 2006 የውድድር ዘመን 2 ጨዋታዎች ብቻ የተሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንም ጨዋታ ሳያደርግ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፈ ሲሆን ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ መድንን በመለያ ምቶች አሸንፎ ለሩብ ፍፃሜ በቅቷል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከሙገር ሲሚንቶ ጋር ማክሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2006 ይጫወታል፡፡ 5 ጊዜ ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ ቡና ዳሸን ቢራን 2-0 1 ጊዜ ሻምፒዮኑ ሙገር ሲሚንቶ ደግሞ ሀዋሳ ከነማን 2-1 አሸንፈው ለሩብ ፍፃሜ ደርሰዋል፡፡

ደደቢት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ደደቢት በርካታ ተስተካካይ ጨዋታዎች ስለሚቀሩት ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *