የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴፌሽን ቀጣዩን የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ለማሳወቅ የወሰደው ጊዜ እየረዘመ በታዛቢዎች በኩል ጥያቄን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ከ15 ቀን በፊት የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝነት ለመያዝ ያመለከቱ 27 አሰልጣኞችን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገው ፌዴሬሽኑ ይፋዊ ማብራርያ ባይሰጥም አመልካቾችን በመገምገም የመጨረሻዎቹን 5 እጩዎች መለየቱ እየተነገረ ነው፡፡
ኢትዮ ቲዩብ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ካለው መረጃ የመጨረሻዎቹ 5 ተመራጭ አሰልጣኞች የሚከተሉት ናቸው፡–
1. ጎራን ስቲቫኖቪች — ሰርቢያ
2- ማሪያኖ ባሬቶ — ፖርቹጋል
3. ዞራን ፊሊፖቪች — ፖርቹጋል
4. ላርስ ኦሎፍ – ስዊድን
5. ዲይጎ ጋርዚያቶ – ጣሊያን
በተያያዘ የቀድሞው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚቀጠረውን አዲስ አሰልጣኝ ደሞዝ ለመሸፈን ቃል እንደገቡ ኢትዮ ኪክ ኦፍ ዘግቧል፡፡
{jcomments on}