የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብ/ቡድን ነገ ወደ ሲሸልስ ያመራል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ ማጣርያ እሁድ ከ ሲሸልስ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ነገ ረፋድ ላይ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በሴኔጋል የሚካሄደው 19ኛው የአፍሪካ ከ20 አመት በታች አፍሪካ ዋንጫን አላማው ያደረገው ብሄራዊ ቡድኑ በአንጋፋው አሰልጣኝ ወነድምአገኝ ከበደ እየተመራ በኤም አር አይ የተመረመሩ 21 ወጣቶችን ይዞ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ከተላያዩ የክፍለ ከተማ እና የክልል ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ወጣት ቡድኑ የሲሸልስ አቻውን በደርሶ መልስ አሸንፎ የሚያልፍ ከሆነ የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታውን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በመድረኩ ለመጨረሻ ጊዜ የተካፈለው በ2001(1993) ሃገራችን ላይ በተዘጋጀው ውድድር እንደሆነ ይታወሳል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *