በክለቦች እና በተጫዋቾች ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች በቀጣይ ቀናት እንደሚገለፅ ሊግ ካምፓኒው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ዛሬ ለግማሽ ቀን የቆየ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በሂልተን ሆቴል አካሂዷል ፤ በጉባኤውም ላይ የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት መቶ ዓለቃ ፈቃደ ማሞ ጨምሮ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የክብር እንግዳነት እና የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ተወካዮች ተገኝተውበታል።
በጉባኤውም የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የውድድር አፈፃፀም ሪፖርት በአክሲዮን ማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ የቀረበ ሲሆን በተለይም ከፋይናንስ መመሪያ አተገባበር፣ ውድድር እና ልምምድ ሜዳ ፣ ከዳኝነት ፣ ከቀጥታ ስርጭት ፣ ከህክምና እና ተጫዋቾች ደህንነት፣ ከፀጥታና ሌሎችም ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በቀረበው ሰነድ መሰረት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በተጨማሪም ከፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴው በክለቦች እና በተጫዋቾች ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች በቀጣይ ቀናት እንደሚገለፅ መጠቆሙን ከሊግ ካምፓኒው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።