ቢጫዎቹ የቀድሞ ተጫዋቻቸው ለማስፈረም ተቃርበዋል

ቢጫዎቹ የቀድሞ ተጫዋቻቸው ለማስፈረም ተቃርበዋል

የመስመር ተከላካዩ ከዓመታት ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ወልዋሎ ተመልሶ ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል።

ላለፈው አንድ ዓመት ተኩል ከነብሮቹ ጋር ቆይታ የነበረው የመስመር ተከላካዩ ሳሙኤል ዮሐንስ ወልዋሎን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል ፤ በዛሬው ዕለት ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ቀሪ ውል እያለው በስምምነት የተለያየው ተጫዋቹ በግማሽ ውድድር ዓመቱ ክለቡን በዘጠኝ ጨዋታዎች ማገልገል ችሏል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተስፋ ቡድኑ እስከ ዋናው ቡድን በመጫወት እግር ኳስን የጀመረው የመስመር ተከላካዩ ከዚህ ቀደም በአማራ ውሃ ስራ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ ፣ ፋሲል ከነማ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ሀድያ ሆሳዕና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዓመታት በኋላ በአምበልነት ወደ አገለገለበት ወልዋሎ ተመልሶ ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል ፤ ተጫዋቹ በቃል ደረጃ ከክለቡ ጋር የተስማማ ሲሆን የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት በይፋ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰባት ነጥቦች በሊጉ ግርጌ የተቀመጡት እና በሁለተኛው ዙር ተጠናክረው ለመቅረብ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች
የሁለተኛው ዙር ጉዟቸው ሲዳማ ቡናን በመግጠም የሚጀምሩ ይሆናል።