የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመልስ ጨዋታ የዩንጋዳ ብሔራዊ ቡድንን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ካለፈበት ጨዋታ በኋላ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ከሚዲያዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተከታዩን መልስ ሰጥተዋል።
ጨዋታው እንዴት ነበር?
”የመጀመሪያ ጨዋታ ከሜዳችን ውጪ ስለነበረ በተቻለን መጠን የሆነ ነገር ይዘን ለመምጣት አስበን ነበር ፤ ጨዋታውን እስከ ዘጠና ደቂቃ ለመቆጣጥር ሞክረን ነበር፤ በቆመ ኳስ ተሸንፈን ነበር የመጣነው የመልሱ ጨዋታ እንደሚከብደን አውቃለሁ ምክንያቱም ተጋጣሚያችን ነጥብ ይዞ ስለመጣ ሜዳው ላይ እንደሚጫወት፣ ሰዓት እንደሚገድል ረጃጅም ኳስ እንደሚጫወት እናስብ ነበረ እና ኳሱን ተቆጣጥረን ለመጫወት ነበር ያሰብነው። ውድድራችን ተቋርጦ ነው ወደ ዝግጅት የመጣነው የዝግጅት ጊዜያችን አስራ አምስት ቀን ስለነበረ የምንፈልገውን ቲም መሥራት አልቻልንም ግን በነበረን ነገር ያው ባለን ጊዜ አጭርም ቢሆን ቲማችንን አዋቅረን ነው የሠራነው። ጨዋታው እኛ ሜዳ እንደመምጣቱ ያለንን ነገሮች በሙሉ ለመጠቀም በምንችለው መንገድ እዛ ከነበረብን ደካማ ስህተቶች እዛ በነበረን ነገር ኳሶቻችን ይቆራረጡ ነበር ኳስ ይዘን ለመጫወት ምንም አልነበረም ፕሬስ ሲያደርጉን ነበር ረጃጅም ኳሶችን ነበር ስንጫወት የነበረው ያንን ሁሉ ከግምት አስገብተን በቀረን ጊዜያቶች ውስጥ ይሄንን ቡድን ለማሸነፍ መስራት የሚጠበቅብንን ነገሮች አድርገን በሜዳችን እንደመጫወታችን ፈርስት አርባ አምስት ብዙ የጎል እድሎችን አግኝተናል መጠቀም አልቻልንም ፤ ከዕረፍት መልስ ደግሞ ስትረስ ውስጥ ገብተን ነው የመጣነው የግድ ማሸነፍ ስለነበረብን በምንችለው መንገድ የምንችለውን አድርገን ጨዋታው ወደ ፔናሊቲ መጥቶ ጨዋታውን ማሸነፍ ችለናል ብዬ ነው የማስበው።”
ከቅያሪ በፊት እና ከቅያሪ በኋላ የነበረውን የቡድን እንቅስቃሴ እንዴት ያዩታል?
”ጨዋታው በጎዶሎ ጎል ሳናገባ ተጫዋች ውጥቶባቸው ነበር። ልጆች ጫና ውስጥ ስለነበሩ ለማሸነፍ የነበራቸው ጉጉት ምንፈልገውን ነገር ፈርስት አርባ አምስት ስንጫወት የነበረውን ነገር በሰከንድ አርባ አምስት መጫወት አልቻልንም ያ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው ልጆች ጫና ውስጥ ስለገቡ ነው ፤ እና የግድ ጎዶሎ ስለነበሩ ቁጥር አብዝተን አጥቅተን ለመጫወት ሞክረን ነበር። ልጅቷ ከወጣች በኋላ ጎል አገባን ያው የታሰበ ቅያሪ ስለነበረ ነው ያልተቀየረው ምክንያቱም አረጋሽ ናት ጎል ያገባችው ማለት ቀድመን ጎል ከመግባቱ በፊት ያሰብነው ቅያሪ ስለሆነ መቀየር ስለነበረበት አዲስ ጉልበት መጠቀም ስለነበረብን ያንን አድርገናል። ተቀይራ የገባችውም ልጅ ባለቀ ሰዓት ስኮር አድርጋ ቲሙን ወደቀጣዩ ዙር ማለት ጨዋታው ወደ ፔናሊቲ እንዲመጣ አድርጋዋለች ስለዚህ የገቡት ልጆች በምንፈልገው ደረጃ ሆነዋል? አልሆኑም! ያው እግር ኳሳዊ ነገር ነው ግን እኛ ባሰብነው መንገድ ጌሙ ባይሄድልንም እግዚአብሔር ይመስገን የምንፈልገውን ነገር አድርገን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈናል።”
የዛሬው አጨዋወት ተጋጣሚያውን ታሳቢ በማድረግ የታቀደ ነው? በቀጣዩ ጉዟችሁ ላይ ምን ዓይነት የጨዋታ አቀራረብ አስበዋል?
”እግር ኳስ ነው ከሜዳ ውጪና ሜዳህ ላይ ስትጫወት የተለያየ ነገር ትጠቀማለህ፤ እኛ በመጀመሪያ እዛ ስንሄድ እዛም ያደረግነው እንቅስቃሴ መጥፎ አይደለም ማለት ፈርተን አይደለም የተጫወትነው አጥቅተን ነው የተጫወትነው ዛሬ በያዝናቸው አጥቂዎች ነው የጀመርነው ግን ጨዋታውን ለማሸነፍ ታክቲካል ዲስፕሊን ሆነን ለመጫወት ነው ያሰብነው አልተሳካልንም ግን ሜዳችን ላይ ስንመጣ ደግሞ ተጋጣሚያችን ምን ይዞ እንደሚመጣ ከዛ ተረድተን የመጣነው እንቅስቃሴ ስለነበር ኳሱን ከሜዳችን መስርተን ለመጫወት ይዘን የመጣነው ሞክረነዋልም ይቆራረጥ ነበር። ትራንዚሽን ላይ ጥሩ ደርሰናል ፖዝሺን አድርገን ደርሰናል ያገኘነውን ነገር አልተጠቀምንም አሁንም ምንቀጥለው ቆንጆ ቆንጆ አማካዮች አሉን ስለዚህ ከሜዳ ውጭ ስንጫወት እና ሜዳ ላይ ስለሚለያይ ሜዳችን ላይ ተመልካችንም አስደስተን ጥሩ እግር ኳስ ተጫውተን ለቀጣይ ለአፍሪካ ዋንጫ ስለማለፍ ነው የምናስበው እንጂ ምንም ሜዳችን ላይ ስንጫወት ከሜዳ ውጭ ብዙ ለውጥ የለውም።”
ጥሩ እንቅሰቃሴ እያደረጉ የነበሩ ተጫዋቾችን ቀይረዋልና ትንሽ መታገስ አልበረባችሁም?
”አረጋሽ እና ሎዛ የመጡት ከውጪ ነው ከቲሙ ጋር ብዙ ነገር መስራት አልቻሉም ግን አምነንበት ስላመጣናቸው ሙሉ ነገር ነው የሰጠናቸው፤ አሁን ተጫዋት እንዲህ ነው እንዲህ ነው መወቃቀስ አልፈልግም። አረጋሽ ጎል ከማግባቷ በፊት የተወሰነ ቅያሪዎች ስለሆኑ እንጂ ስላገባች መቀጠል አለመቀጠል አይደለም የሷ ጎል ወደቀጣይ እንዲንመጣ አድርጎናል እንድንነሳሳ አድርጎናል። መሳይም ጥሩ ክሮስ ኳስ ያደረገችው መሳይ ናት ግን ቀድመን ያሰብነው ቅያሪ ስለሆነ ነው የተገደድነው እንጂ ከቆዩ ከዚህ የተሻለ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ ላያደርጉ ይችላሉ እግር ኳስ ስለሆነ ከእዚህ አሁን ካየነው ስህተት ተምረን ለቀጣይ ደግሞ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን ነገር ተምረን የተሻለ ነገር ሰርተን እንመጣለን ብዬ አስባለሁ።”