ሀዋሳ ከተማ ይግባኝ ጠይቋል

ሀዋሳ ከተማ ይግባኝ ጠይቋል

ሀዋሳ ከተማ በቡድኑ ላይ ለቀረበበት ውሳኔ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ደብዳቤ አስገብቷል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ ስርዓት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በአራት የሊጉ ክለቦች እና በአስራ አምስት ተጫዋቾች ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወሳል።

የቅጣት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሀዋሳ ከተማ ከመቐለ 70 እንደርታ ፣ ሲዳማ ቡና እና መቻል በመቀጠል ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ደብዳቤን አስገብቷል።

ቡድኑ በቀረበበት ክስ ዙርያ በቂ ምስረጃዎችን ባቀርብም ኮሚቴው ይህን ወደ ጎን በማለት ውሳኔ አሳልፎብኛል ያለ ሲሆን በተለይም ከሰኔ 2016 እስከ መስከረም 20/2017 ዓ.ም ላይ ከገቢው በላይ የሆነ ገንዘብ ወደ ሂሳብ ቋት ስለገባበት አግባብ ክለቡ ሰፊ ማብራሪያ በይግባኙ ላይ ሰጥቷል።

ቡድኑ በደብዳቤው የተላለፈበት ውሳኔ አግባብነት ያለው አለመሆኑን በመጠቆም ምላሽ እንዲሰጠውም ጠይቋል።