“መሬት ሸጬ ነው ያለን ተጫዋች አለ” አቶ ክፍሌ ሰይፈ

“መሬት ሸጬ ነው ያለን ተጫዋች አለ” አቶ ክፍሌ ሰይፈ

የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደርን በተመለከተ በአሁኑ ሰዓት መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከቀናት በፊት በፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የተወሰነውን ውሳኔ በተመለከተ ለብዙሃን መገናኛ አባላት መግለጫ እየሰጠ ሲሆን በቅድሚያ የማኅበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በምርመራ ሂደት ያጋጠማቸውን ነገር ሲያብራሩ ትኩረት የሚስብ ነገር ተነስቷል።

በዚህም ጥቆማ ደርሶባቸው በኮሚቴው ተጠርተው ከተጠየቁ 26 ተጫዋቾች መካከል አንዱ የገንዘቡን ምንጭ አስረዳ ሲባል መሬት ሸጬ ነው ብሎናል። በዚህም ኮሚቴው ተጫዋቹ የሸጠውን መሬት ማስረጃ እንዲያሳይ ሸጬዋለው ያለው ቦታ ድረስ ባለሙያ ልኮ ውል እና ማስረጃ መረጃ ሲፈልግ እንዳልተገኘ አንስተዋል።