የአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ቅድመ ክፍያ የተቀበሉ ተጫዋቾች ራሳቸውን ካጋለጡ ነፃ እንደሚሆኑ አመላክተዋል።
“እኛ ገንዘብ መሰብሰብ አይደለም ዓላማችን። ዓላማችን የፀዳ እግርኳስ እንዲኖር እና ጥሩ ብሔራዊ ቡድን እንዲገነባ ነው።” ያሉት የአክሲዮን ማኅበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ባሳለፍነው ሰኞ ውሳኔው ከወጣ በኋላ በርካታ ጥቆማዎች እየመጡ እንደሆነ አንስተው የመጡትን ጥቆማዎች ለፌዴራል ፖሊስ በመስጠት ፌዴራል ፖሊስ ከመረጃና ደህንነት ቢሮ ጋር በመሆን ማጣራቱ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
በቀጣይ የማጣራት ሂደቶች ተጠናክረው ሲሄዱ ተጫዋቾች ራሳቸውን በማጋለጥ ቅድመ ክፍያ እንደተቀበሉ የሚገልፁ ከሆነ ነፃ ሆነው የከፈለው ክለብ ብቻ እንደሚቀጣ ተገልጿል።
