ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሳይመን ፒተር የመጀመሪያ አጋማሽ ብቸኛ ግብ መቐለ 70 እንደርታን በማሸነፍ ሦስት ነጥብ አሳክተዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግቦችን ለማስቆጠር ገና በማለዳው ወደ ተጋጣሚያቸው ሳጥን በመድረስ በታተሩበት በምሽቱ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች የንግድ ባንክ ጫና የበረታበትን እና አከታትለው ወደ ተጋጣሚያቸው ግብ ክልል መድረስ የቻሉበትን እንቅስቃሴ ሲያስመለክተን ምዕም አናብስቶች በአንፃራዊነት መረጋጋት ተስኗቸው የተስተዋሉበት ነበር።
21ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ግደይ ከማዕዘን ምት ያሻማውን ኳስ ሳይመን ፒተር በግንባሩ ገጭቶ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል ፤ ከግቧ መቆጠር በኋላ የተነቃቁት ምዕም ዓናብስቶች ወደ ጨዋታ ተመልሰው በጥሩ እንቅስቃሴ ኳስ ሲያንሸራሽሩ ተመልክተናል።
35ኛው ደቂቃ ላይ ኪቲካ ጅማ በቀኝ መስመር በኩል በረጅሙ የተሻገረለትን ኳስ እየገፋ ይዞ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ያለቀ ኳስ ብቻውን ለነበረው አዲስ ግደይ አቀብሎት ወደ ግብ ቢመታም ሶፎንያስ ሰይፈ በጥሩ ቅልጥፍና ኳሱን ሲያግድበት ራሱ ኳስ ተነካክቶ ድጋሚ አዲስ ግደይ ጋር ደርሶ ከሳጥን ውጪ ሆኖ ጠንከር ያለ ሙከራ ቢያደርግም ለጥቂት ከግቡ አግዳሚ ከፍ ብሎ ያለፈበት እንዲሁም አጋማሹ ሊጠናቀቅ አከባቢ ኤፍሬም ታምራት ከሳይመን ፒተር የተሻገረለትን ኳስ ከሳጥኑ ቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ አክርሮ ወደ ግብ የመታት እና ሶፎንያስ ሰይፈ እንዴትም ጨርፎ ያወጣበት አጋጣሚዎች ንግድ ባንኮች ተጨማሪ ግብ ለማግኘት የቀረቡበት አደገኛ ሙከራዎች ነበሩ።
ጨዋታው ከመልበሻ ክፍል መልስ ቀጥሎ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ንግድ ባንኮች ተጨማሪ ግብ ለመሆን የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል። 62ኛው ደቂቃ ላይ ባሲሩ ዑመር የመቐለ 70 ተከላካዮችን አታሎ በማለፍ ሳጥን ውስጥ ሆኖ ያደረገውን ሙከራ የግብ ዘቡ ያገደበት ሙከራ ተጠቃሽ ነበር።
የመቐለዎች ጫና አይሎ በቀጠለበት ጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠርበት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሳይመን ፒተር መጀመሪያ አጋማሽ ብቸኛ ግብ ሙሉ ሶስት ነጥብ በማጎናፀፍ ተጠናቋል።