ወልዋሎ አማካዩን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ወልዋሎ አማካዩን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

በትናንትናው ዕለት ከሲዳማ ቡና ጋር ነጥብ በመጋራት የሁለተኛ ዙር ጉዟቸው የጀመሩት ቢጫዎቹ አማካዩን ለማስፈረም ተቃርበዋል።

በሁለተኛው ዙር ተጠናክረው ለመቅረብ ቀደም ብለው ተከላካዩ ሳሙኤል ዮሐንስን ያስፈረሙት እና የሁለተኛው ዙር ጉዟቸው በአቻ ውጤት የጀመሩት ወልዋሎዎች አማካዩ ሀብታሙ ንጉሴ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ላለፉት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመስራት የቆየው ተጫዋቹ ቡድኑን ለመቀላቀል መስማማቱን ተከትሎ በቀጣይ ቀናት በይፋ ፊርማውን አኑሮ በቀጣይ መርሐ-ግብሮች ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ክለቡን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው አማካዩ ሀብታሙ ንጉሴ ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ ፣ ወልዲያ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባ ጅፋር መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን ለሁለት ዓመታት በወላይታ ድቻ ካሳለፈ በኋላም ባለፈው የውድድር ዓመት በሻሸመኔ ከተማ ቆይታ ማድረጉም ይታወቃል።