የመጀመሪያው የሲዳማ ሊግ ተጀመረ

የመጀመሪያው የሲዳማ ሊግ ተጀመረ

የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ክልል አቀፍ የሊግ ውድድር ዛሬ አስጀምሯል።

የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ በፊት የክለቦች ሻምፒዮና በሚል የሚያዘጋጀውን ውድድር ወደ ሊግ አሳድጎ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በይርጋዓለም ሁለገብ ስታዲየም በይፋ አስጀምሯል።

በአስራ ስድስት ቡድኖች መካከል የሚደረገው ውድድሩ ከክልሉ አራቱም ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ቡድኖች የሚሳተፉበት ሲሆን ውድድሩም ቅዳሜ እሁድ ብቻ እንደሚከናወንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ ባራሳ ፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አቶ አንበሴ አበበን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሦራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይርጋለም ሁለገብ ስታድየም ጅማሮውን አድርጓል።

በመክፈቻ ጨዋታውም ሲዳማ ልማት ኮርፖሬሽን እና ከይርጋለም ከነማ መካከል ተድርጎ ጨዋታው በይርጋለም ከነማ አንድ ለምንም አሸናፊነት ተጠናቋል።