ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል ተስማምቷል

ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል ተስማምቷል

ለአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች ሁለት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማምቷል።


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን የሁለተኛውን ዙር ውድድራቸውን ከመቻል ጋር ያለ ጎል በማጠናቀቅ የጀመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች ከሰሞኑ ከቡድኑ ጋር ልምምድን ሲሰሩ የቆዩትን ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ስለመድረሳቸው ታውቋል።

ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው የመጀመሪያው ተጫዋች አቡበከር ወንድሙ ነው ፤ የቀድሞው የሀላባ ከተማ ፣ አዲስ አበባ እና አዳማ ከተማ የመስመር አጥቂ አቡበከር ከቀድሞው አሰልጣኙ አሰልጣኝ ይታገሱ ጋር ዳግም በድሬዳዋ ከተማ የሚገናኙ ይሆናል።

ሌላኛው የቡድኑ አዲሱ ተጫዋች ዮሐንስ ደረጀ ነው ፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በባቱ ከተማ እና በያዝነው የውድር ዘመን አጋማሹን በእንጂባራ ከተማ የነበረው አጥቂ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ክለብ ማምራቱ የተረጋገጠ ሲሆን ሁለቱ ተጫዋቾች ለአዲሱ ክለባቸው በነገው ዕለት ይፋዊ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።