አምሐ ተስፋዬ

ወልቂጤ ከተማ የአማካይ እና አጥቂ ስፍራ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። ጫላ ተሺታ ከፈራሚዎቹ አንዱ ነው። በሻሸመኔ ከተማ፣ ሰበታ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም በ2012 በወልቂጤ ከተማ የተጫወተው የመስመር አጥቂው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ እስከ አጋማሽ ድረስ ቆይታ አድርጓል። አሁን ደግሞ ድንቅ ጊዜ ወዳሳለፈበት ወልቂጤ ከተማ የሚመልሰውን ዝውውር አከናውኗል።ዝርዝር

በአሠልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው የሚመሩት ወልቂጤ ከተማዎች አዲስ ምክትል አሠልጣኝ ሾመዋል። የትግራይ ክልል ክለቦችን ለመተካት በተደረገው ውድድር በሊጉ መክረማቸውን ያረጋገጡት ወልቂጤ ከተማዎች አረፋፍደውም ቢሆን ቡድናቸውን እያጠናከሩ እንደሆነ ይታወቃል። ሶከር ኢትዮጵያ ዛሬ እንዳስነበበችው ክለቡ አይቮሪኮስታዊው የግብ ዘብ ጉልስጎኖን ሲላቫይን ጎቦሆ አስፈርሟል። አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ የአሠልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ሁለተኛ ምክትል የሚሆን አሠልጣኝዝርዝር

የፊታችን ዕሁድ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩት ወልቂጤ ከተማዎች የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂን አስፈርመዋል። ዘግየት ብለው በዝውውር ገበያው ላይ መሳተፍ የጀመሩት ወልቂጤ ከተማዎች በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ ማስፈረማቸው ታውቋል። ለሠራተኞቹ ፊርማውን ያኖረው ተጫዋች ሲላቫይን ጎቦሆ ነው። የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የነበረው እና በክለብ ደረጃ ከቲፒ ማዜንቤ ጋር ጥሩ ቆይታዝርዝር

ወልቂጤ ከተማ ለ2014 የሊጉ ውድድር ዝግጅት የሚያደርጉበት ቦታ እና የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል። ከሊጉ ወርዶ የነበረ ቢሆንም በድጋሚ ያገኘውን ዕድል በመጠቀም የቤትኪንግ የኢትዮጽያ ፕሪምየር ሊግ መቆየት የቻለው ወልቂጤ ከተማ የአሠልጣኙ ጳውሎስ ጌታቸውን ውል ካደሰ በኋላ ጥቂት ተጫዋቾች በማዘዋወር ቆይቶል። ቀደም ብሎ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ለመጀመር አስቦ የነበረው ክለቡ በተለያዩ ምክንያቶች ቀኑንዝርዝር

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚወዳደረው ኢትዮጵያ መድን የቀድሞ አሠልጣኙን ዳግም ቀጥሯል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው የሊግ እርከን (ከፍተኛ ሊግ) የሚወዳደረው ኢትዮጵያ መድን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በምድብ ሐ 35 ነጥቦችን በመያዝ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በአሠልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመራ ያለፈውን የውድድር ዓመት ያሳለፈው ክለብ ከአሠልጣኙ ጋር ከተለያየ በኋላ የቀድሞ አሠልጣኙን ወደ መንበሩ መልሷል።ዝርዝር

በዝውውር መስኮቱ እንቅስቃሴ ሳያደርግ የቆየው ወልቂጤ ከተማ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። የውጪ ተጫዋችም ከፈረሙት መካከል ይገኝበታል።  ለቀጣዩ የውድድር ዓመት የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ያደረገውና ይህን ተከትሎ በደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ክለቡ ከዚህ ቀደም የአሰልጣኙን ውል ማራዘም እና ከወጣት ቡድኑ ተጫዋቾች ለማሳደግ ላይ ብቻ ተገድቦ መቆየቱ የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ለማስፈረም እንደተስማሙዝርዝር

በፕሪምየር ሊጉ የመቆየታቸውን ጉዳይ ያረጋገጡት ወልቂጤ ከተማዎች የአሠልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን ውል ባረዘሙ ማግስት አራት ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድናቸው አሳድገዋል። ሠራተኞቹ በቀጣይ የውድድር ዘመን ተጠናክረው ለመቅረብ ከወዲሁ ለእድሜ እርከን ቡድኖቻቸው ዕድል በመስጠት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን በአረንጎዴ እና ቢጫ መታወቂያ ማሳደግ ችለዋል። በአረንጓዴ መታወቂያ ወደ ዋናው ቡድን ያደገው በግራ መስመር የሚጫወተው ቴዎድሮስዝርዝር

በፕሪምየር ሊጉ የመቆየትን ዕድል በእጁ ያስገባው ወልቂጤ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር አብሮ እንደሚቆይ ታውቋል። የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ከጀመረበት የተነቃቃ አኳኋን አንፃር ባልተጠበቀ መልኩ በወራጅነት ያጠናቀቀው ወልቂጤ ከተማ በቀጣይ ዓመት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የትግራይ ክልል ክለቦችን ቦታ ለሟሟላት በተደረገው ውድድር ላይ ባስመዘገበው ውጤት በሀገሪቱ የመጀመሪያው የሊግ ዕርከን የመቀጠል ዕድልን አሳክቷል። በተጠናቀቀውዝርዝር

በጌዲኦ ዲላ ስፖርት ክለብ አስተናጋጅነት በጌዲኦ በ8 ዞን ከአምስቱም ከተማ አስተዳደር በተወጣጡ 16 ክለቦች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው ከ17 ዓመት በታች ውድድር በተስፋ ስንቅ አሸናፊነት ተጠናቋል። ዛሬ በተከናወነው የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የጌዴኦ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዩሴፍ ማሩ (ዕጬ ዶ/ር) እንዲሁም የክለቡ የቦርድ አባልና የዞኑ ዋና አስተዳደር ተወካይ በክብርዝርዝር

ላለመውረድ እየታገሉ የሚገኙት ሠራተኞቹ “አላስፈላጊ ቦታ ተገኝተዋል” ያሏቸው ሦስት ተጫዋቾችን ከቡድኑ ካምፕ አስወጥተዋል። ከሰዓታት በፊት አሠልጣኝ ሲሳይ አብርሃን በአሠልጣኝነት የሾሙት ወልቂጤ ከተማዎች “የዲሲፕሊን ጥሰት ፈፅመው ተገኝተዋል” ያሏቸው ሦስት ተጫዋቾቻቸውን ከቡድኑ ካምፕ ማስወጣታቸው ተረጋግጧል። ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ መሠረትም ተጫዋቾቹ ፍሬው ሰለሞን፣ ይበልጣል ሽባባው እና አዳነ በላይነህ ናቸው። ስማቸው የተጠቀሰው እነኚህዝርዝር