Soccer Ethiopia

Archives

አዳነ በላይነህ በወልቂጤ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል

ወልቂጤ ከተማ የመስመር ተከላካዩ አዳነ በላይነህን ለተጨማሪ ዓመታት ለማቆየት ከስምምነት ደርሷል። በተቋረጠው ውድድር ዓመት የመጀመርያ የፕሪምየር ሊግ ላደረጉት ወልቂጤዎች በግራ መስመር ጥሩ ግልጋሎት የሰጠው አዳነ በላይነህ በሠራተኞቹ ቤት ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ጉዳይ ሲያነጋግር የቆየ ቢሆንም በመጨረሻም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል አድሷል። አዳነ በላይነህ ከዚህ ቀደም በወልቂጤ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ መድን እና አዲስ አበባ ከተማ […]

ወልቂጤ ከተማ አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

ወልቂጤ ከተማ የአጥቂ መስመር ተሰላፊው አሜ መሐመድን ለማስፈረም ተስማምቷል። የቀድሞው የጅማ አባ ቡና እና ኢትዮጵያ ወጣት ቡድን አጥቂ አባ ቡናን ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳደጉ ወሳኝ ሚና የተጫወተ ሲሆን በሊጉ ያሳየውን ጥሩ እንቅስቃሴ ተከትሎ በ2009 ክረምት ነበር ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው። በፈረሰኞቹ የተጠበቀውን ያህል የተሰላፊነት እድል ያላገኘው አሜ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር በመለያየት ወልቂጤን ለመቀላቀል […]

ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

ጀማል ጣሰው ወደ ወልቂጤ ከተማ ለማምራት ቅድመ ስምምነት ፈፀመ። በእግር ኳስ ሕይወቱ ለሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ ጅማ አባ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ የተጫወተው ይህ ግብ ጠባቂ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በፋሲል ከነማ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ወልቂጤ ለማምራት መስማማቱን ተከትሎ ወደ ፋሲል ያመራው ይድነቃቸው ኪዳኔን ቦታ ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። በዝውውር መስኮቱ የነባር […]

ወልቂጤዎች በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

ቀደም ብለው ወደ እንቅስቃሴ በመግባት የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የሚገኙት ሠራተኞቹ ረመዳን የሱፍ እና ሀብታሙ ሽዋለምን ሲያስፈርሙ የዳግም ንጉሤን ውል አራዝመዋል። ከንግድ ባንክ ሁለተኛ ቡድን አድጎ ለንስር እና ለስሑል ሽረ የተጫወተው ተስፈኛው ረመዳን የሱፍ ስሙ ከበርካታ የሊጉ ክለቦች እየተያያዘ ቢቆይም በስተመጨረሻ ወደ ሠራተኞቹ አቅንቷል። የግራ መስመር ተከላካይ የሆነውና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]

ሀዲያ ሆሳዕናዎች ሦስት ተጫዋቾች በማስፈረም ወደ ዝውውሩ ገብተዋል

አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ሦስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማምተዋል። ከቀናት በፊት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ነብሮቹ የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች የነበሩት በረከት ደስታ፣ አዲስ ህንፃ እና ቴዎድሮስ በቀለን ነው ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት። ከአዳማ ሁለተኛ ቡድን ካደገ በኃላ የክለቡ ወሳኝ ተጫዋች ለመሆን ጊዜ ያልወሰደበት በረከት ደስታ ባለፉት ሦስት ዓመታት የአዳማ ወሳኝ ተጫዋች መሆን ችሎ ነበር። […]

ወልቂጤ ከተማ ከአንጋፋው ተጫዋች እና ምክትል አሰልጣኙ ጋር ተለያይቷል

አዳነ ግርማ እና ወልቂጤ ከተማ መለያየታቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል። በተሰረዘው ውድድር ዓመት ሀዋሳ ከተማን ለቆ ወደ ሌላኛው ደቡብ ቡድን የተቀላቀለው አንጋፋው ተጫዋች በተለይ በመጀመርያዎቹ ሳምንታት በተጫዋችነት ክለቡን ሲያገለግል የነበረ ሲሆን በተጨማሪነትም ምክትል አሰልጣኝነትም ሲሰራ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ዓመት ከተጫዋችነት እንደሚገለል የተነገረለት የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ከክለቡ ጋር በስምምነት እንደተለያየ የክለቡ ምክትል […]

ወልቂጤ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

ወልቂጤዎች በቀጣይ የውድድር ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ ውል የጨረሱ ተጫዋቾች ውል በማደስ እንዲሁም አዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የዝውውር መስኮቱ እስኪከፈት ቀድመው የቤት ሥራቸውን እየከወኑ ይገኛሉ። አሁን ደግሞ አቡበከር ሳኒ እና ተስፋዬ ነጋሽን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ተስማምተዋል። አቡበከር ሳኒ ወልቂጤ ከተማን ለመቀላቀል ከተስማሙት አንዱ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ተገኝቶ በዋናው ቡድን ለአምስት ዓመታት የተጫወተው አቡበከር በብሔራዊ ቡድንም […]

ወልቂጤ ከተማ ከወሳኝ ተጫዋቹ ጋር ይቀጥላል

ወልቂጤ ከተማ የመስመር ተጫዋቹ ጫላ ተሺታን በክለቡ ለማቆየት ከስምምነት ላይ ደርሷል። ከሰሞኑ የአሰልጣኙን እና የስድስት ተጫዋቾች ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ያራዘመው ቡድኑ በዛሬው ዕለት ከሲዳማ ቡና ወደ ወልቂጤ ከተማ በተሰረዘው ዓመት ተዘዋውሮ የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆን የቻለው የመስመር አጥቂ ጫላ ተሺታን ውል ለሁለት ዓመታት ነው ማራዘም የቻለው። የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች ጫላ […]

ወልቂጤ አዲስ ተጫዋች ለማስፈረም ሲስማማ የአጥቂውን ውል አድሷል

ወልቂጤ ከተማ ሁለተኛውን አዲስ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ሲስማማ የአንድ የነባር ተጫዋች ውል አራዝሟል። በዛሬው እለት በሁለት ዓመት ውል ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማማው የፊት መስመር ተጫዋቹ ምንይሉ ወንድሙ ነው። በመከላከያ ዋናው ቡድን ከ2007 ጀምሮ ሲጫወት የቆየው ምንይሉ ባለፉት ዓመታት በሊጉ ከታዩ ጥሩ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን በተሰረዘው ውድድር ዓመት የጎል አስቆጣሪ ችግር ለነበረበት ወልቂጤ […]

ወልቂጤ ከተማ የአምስት ተጫዋቾቹን ውል አድሷል

ዛሬ አንድ ተጫዋች በእጁ ያስገባው ወልቂጤ ከተማ የአምስት ነባር ተጫዋቾቹን ውል ለማደስ ከስምምነት ደርሷል። በተከላካይ ሥፍራ የሚጫወተው ቶማስ ስምረቱ ካደሱት ተጫዋቾች አንዱ ነው። በሱልልታ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ቡና የተጫወተውና በተሰረዘው የውድድር ዓመት ወደ ወልቂጤ ያመራው ቶማስ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በክለቡ ለመጫወት ተስማምቷል፡፡ ሁለተኛው ውሉን በክለቡ ያራዘመው አማካዩ ኤፍሬም ዘካርያስ ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top