ኤልያስ ኢብራሂም

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ለመጀመርያ ጊዜ የተሳተፈው ፋሲል ከነማ በቅድመ ማጣርያው የመጀመርያ ጨዋታ ባህር ዳር አለማቀፍ ስታዲየም ላይ አል ሂላልን አስተናግዶ ሁለት አቻ ተለያይቷል። በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ዐፄዎቹ ጨዋታው በመቆጣጠር የጨዋታ ብልጫ ወስደው ለመጫወት ጥረት ሲያደርጉ ተጠቃሽ ሙከራ በማድረግ ረገድም ቀዳሚ ነበሩ። 3ኛው ደቂቃ ላይ ኦኪኪ አፎላቢ ወደ ግብ ኳስ እየነዳ በሚሄድበትዝርዝር

በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጠናክሮ ለመቅረብ ዝውውሮች ላይ ጠንክሮ እየሰራ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ አራተኛ ተጫዋች አስፈርሟል። አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ከቀጠሩ በኋላ ፉዐድ ፈረጃ፣ መሳይ አገኘሁ እና ተመስገን ደረሰን የግላቸው ያደረጉት ባህር ዳር ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት በሁለት ዓመት ውል አለልኝ አዘነን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል። በአርባምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን በ2008ዝርዝር

በፋሲል ከነማ ቤት በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ግቦችን እና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ሲያመቻች የነበረው ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ውሉን አራዝሟል። የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት በመሆን በካፍ የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ በአዲስ መልክ አስቻለው ታመነን፣ ኦኪኪ አፎላቢ እና አብዱልከሪም መሐመድን ማስፈረሙ ይታወቃል። ከአዲስ ተጫዋቾቹ በተጨማሪ የዳንኤል ዘመዴ፣ ኪሩቤል ኃይሉ፣ዝርዝር

ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ያገናኘው የሴካፋ የመጀመሪያ ጨዋታ ከማራኪ እንቅስቃሴ ጋር 3-3 ተጠናቋል። በጨዋታው ጅማሮ የኤርትራ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ወደ ግብ መድረስ የቻለ ሲሆን በ2ኛ ደቂቃ በተከታታይ ስህተት የተገኘውን ኳስ የኤርትራው የመስመር አጥቂ ደህያን ግብሳዊን ወደ ግብ ሞክሮ ግብጠባቂ አድኖበታል። በድጋሚ ከሁለት ደቂቃ በኋላ ከቀኝ መስመር ከዓሊ የተሻገረለትንዝርዝር

ትናንት በአዲስ አበባ የነበራቸውን ዝግጅት ጨርሰው ወደ ባህር ዳር የተጓዙት የኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ልምምድ አከናውነዋል። በአቫንቲ ሆቴል መቀመጫውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ከቀኑ 9 ሰዓት በቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ ላይ ልምምዱን የሰራ ሲሆን ቀለል ያለ ልምምድ እንዲሁም ከሁለት ተከፍለው በግማሽ ሜዳ ጨዋታ በማድረግ አከናውነዋል። በዛሬው ልምምድዝርዝር

የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ለኮንፌፌሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ቡድናቸው ስላደረገው ዝግጅት፣ የቡድኑ ወቅታዊ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ወደ ቱኒዚያ ከማምራታቸው በፊት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገዋል። ስለ ዝግጅት  ጎንደር ላይ ነው ዝግጅት የጀመርነው። ከጎንደር የተሳካ የዝግጅት ጊዜ በኋላ ወደ አዲስ አበባ አቅንተን ብሔራዊ ቡድን ላይ የነበሩዝርዝር

በኮንፌደሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲርን ከሜዳ ውጭ የሚገጥመው ፋሲል ከነማ ቱኒዝያ ገብቷል ። ዐፄዎቹ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ቢሆንም ከኢትዮጵያ ቀጥታ ወደ ቱኒዚያ የአየር በረራ ባለመኖሩ ቀደም ብለው በማመቻቸት ሊገሸዙ ችለዋል። ትናንት ምሽት ወደ ቱኒዚያ ጉዞ የጀመሩት የቡድኑ አባላትም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያዝርዝር

በዛሬው የተስፈኞች አምዳችን ላይ ከፈጣኑ እና ሁለገቡ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ጋር ቆይታ አድርገናል። በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ተወልዶ ያደገው ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት እግርኳስን የጀመረ ሲሆን በ2009 አማራ ክልልን ወክሎ ከተጫወተ በኋላ በዛው ዓመት ፋሲል ከነማ ተስፋ ተቀላቅሏል። ለሁለት ዓመት በተስፋ በቡድኑ ቆይታ ያደረገው ናትናኤል በውበቱ አባተዝርዝር

ከፋሲል ከነማው ፊዚዮቴራፒስት ሽመልስ ደሳለኝ ጋር ከክፍል አንድ የቀጠለ በኢትዮጵያ እግርኳስ ስለሚያጋጥሙ ጉዳቶች እና በህክምና ወቅት ስለሚያጋጥሙ ችግሮች ባለፈው ሳምንት በክፍል አንድ ቆይታ ማድረጋችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በክፍል ሁለት ተከታዩን መሰናዶ ይዘን ቀርበናል። (ክፍል አንድ ለማንበብ | LINK) ማሳጅ ሳይንስ ነው ማለት እንችላለን ? ማሳጅ ጥበብ እና ሳይንስ ነው። ማሳጅዝርዝር

የፋሲል ከነማው ፊዚዮቴራፒስት ሽመልስ ደሳለኝ በኢትዮጵያ እግርኳስ የተጫዋቾች ጉዳት እና ህክምናው ዙርያ ያለውን ልምድ ከከሳይንሱ ጋር በማስደገፍ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል። በፕሪምየር ሊግ ደረጃ በፊዚዮትራፒስትነት ለሰባት ዓመታት ያገለገለው ሽመለስ ደሳለኝ የህክምና ሙያውን በጎንደር መምህራን ኮሌጅ በጤና እና ሰውነት መጎልመሻ (Health and Physical education ) ዲፕሎማ ከተማረ በኋላ ጎንደር ዩኒቨርስቲዝርዝር