ኢትዮጵያዊው አጥቂ ፍቅሩ ተፈራ በደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪምየርሺፕ ለአዲሱ ክለቡ ቤደቬስት ዊትስ ማክሰኞ ምሽት በተደረገ ጨዋታ ማርቲዝበርግ ዩናይትድ ላይ ግብ አስቆጠረ፡፡ ፍቅሩ በመጀመሪያው ጨዋታው ለዊትስ ግብ ማስቆጠሩ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ማርቲዝበርግ ዩናይትዶች በጨዋታው መምራት ቢችልም ዊትስ 2 ግቦችን አስቆጥሮ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወጥቷል፡፡ ለዊትስ 2ኛውን ግብ ኢትዮጵያዊው ፍቅሩ ተፈራ የመጀመሪያውRead More →

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በመጪው ቅዳሜ ከሲሸልሱ ኮት ዲ ኦር ክለብ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ስለ ቡድኑ ግብ የማስቆጠር ችግር የመጀመርያው ምክንያት የአጥቂዎቻችን ቁጥር ማነስ ነው፡፡ ያሉኝ አጥቂዎች እጅግ በጣም ጥቂት በመሆናቸው የግብ ማስቆጠር ችግር በአንድና በሁለት ሳምንት ውስጥ የሚስተካከል አይደለም፡፡ ነገሮችን በዘላቂነት የምናስተካክልበት ጊዜRead More →

የ2006 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ደደቢት በ2015 የአፍሪካ ኮንፌድሬሽንስ ዋንጫ የመጀመርያ ጨዋታ ከሲሸልሱ ኮት ዲ ኦር ጋር ይጫወታል፡፡ ቅዳሜ ለሚያደርገው ጨዋታም ዛሬ አመሻሽ 11፡00 ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በኬንያ በኩል ሐሙስ ወደ ስፍራው እንደሚደርስ ታውቋል፡፡ የሲሸልሱ ተጋጣሚ ኮት ዲ ኦር 2,000 ተመልካች የሚይዝ ስታድ አሚቴ የተሰኘ የራሱ ሜዳ ያለው ሲሆን ከዋናRead More →

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵጵን የሚወክለው ቅዱስ ጊየርጊስ የመልስ ጨዋታቸውን በባህርዳር ብሄራዊ ስታድየም ማከናወን እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለኢንተርናሽናል ውድድሮች ያስመዘገበው ሜዳ አዲስ አበባ ስታድየም ቢሆንም የመዲናዋ ስታድየም ለአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ውድድር በእድሳት ላይ የሚደረግ በመሆኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአልጄርያው ኤም ሲ ኡልማ ጋር ፌብሩወሪ 29 የሚያደርገው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግRead More →

ከ10 አመታት የየመን ቆይታ በኋላ ወደ ሃገር ቤት ተመልሶ የቀድሞ ክለቡ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው ዮርዳኖስ አባይ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ፕላኔት ስፖርት የሬድዮ ፕሮግራም ዘግቧል፡፡ ለዮርዳኖስ እና ክለቡ መለያየት እንደ ምክንያት የተቀመጠው ከክለቡ አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ጋር የፈጠረው አለመግባባት መሆኑ ታውቋል፡፡ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 በረታበት የሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ ላይ አለመሰለፉም ላለመግባባታቸውRead More →

ሶከር ኢትዮጵያ የወሩ የፕሪሚየር ምርጦችን መምረጧን ቀጥላ 3ኛ ወር ላይ ደርሳለች፡፡ የዚህ ወር ምርጦች የሚከተሉት ናቸው፡፡   ለአለም ብርሃኑ ለአለም ዘንድሮው ጠንክሮ በመጣው ሲዳማ ቡና ላይ የራሱን ድንቅ ብቃት አክሎበት ከፊቱ ካሉት ተከላካዮች ጋር የማይበገር የኋላ መስመር መስርቷል፡፡ ከፊቱ የሚገኙት ተከላካዮች ጠንካሮች ቢሆኑም በበርካታ አጋጣሚዎች ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አድኗል፡፡ ከሁሉምRead More →

ባለፈው ወር የኢትዮጵያ ፐሪሚየር ሊግ የወሩ ኮከቦችን ለመጀመርያ ጊዜ የመረጠችው የሶከር ኢትዮጵያ የ2ኛውን ወር ኮከቦች ጊዜውን ጠብቃ መርጣለች፡፡ ባለፈው ወር ከተካተቱት ተጫዋቾች መካከል አንድም ተጫዋች በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት የቀረ ሲሆን ከአንዳንዶቹ ውጪ አብዛኛዎቸ ተጫዋቾች በዚህኛው ወር ደካማ አቋም ማሳየታቸው የሊጉ ተጫዋቾች ወጥ አቋም የማሳየት ችግር ያመላከተ ሆኗል፡፡ በዚህ ምርጫRead More →

የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ከተጀመረ 1 ወር እና የ4 ሳምንት ጨዋታዎች እድሜ አስቆጥሯል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም በአንዱ ወር ውስጥ (ከጥቅምት 16 እስከ ህዳር 16) ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩ ተጫዋቾች እና አሰልጣኝ መርጣለች፡፡ ግብ ጠባቂ – ወንድወሰን አሸናፊ ( ሙገር ሲሚንቶ ) ወንድወሰን አሰግድ አክሊሉ ጥሎት የሄደውን ቦታ በሚገባ ሸፍኗል፡፡ የማይታመኑ ኳሶችን የማዳንRead More →

ይህ የሶከር ኢትዮጵያ ኦንላይን ቁጥር ሁለት እትም ነው፡፡ መፅሄቱ ሙሉ ለሙሉ የሚያተኩረውም ኢትዮጵያ ከፊቷ በሚጠብቃት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዙርያ ነው፡፡ በኢንተርኔት ፍጥነት እና በሌሎች ችግሮች ቀደም ብለን ባለማውጣታችን ይቅርታ እየጠየቅን በፒዲኤፍ ፎርማት የተዘጋጀውን መፅሄት ዳውንሎድ በማድረግ እንዲያነቡ ጋብዘንዎታል፡፡ መልካም ንባብ ፤ መልካም እድል ለብሄራዊ ቡድናችን !!!! https://dl.dropboxusercontent.com/s/ymjh74rlmzst6ci/Soccer%20Ethiopia%202.pdf?dl=0Read More →

ሳላዲን ሰዒድ በትላንትናው እለት የመጀመርያ የአል አህሊ ልምምዱን ከሰራ በኋላ የተሰማውን ደስታ ገልጧል፡፡ የአፍሪካውን ትልቅ ቡድን አካል በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማውና በአጀማመሩም ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ሳላዲን ከመጀመርያው ልምምድ በኋላ የቀዮቹ አሰልጣኝ ሁዋን ካርሎስ ጋሪዶ እንዳበረታቱት ለአህሊ ድረ-ገፅ ተናግሯል፡፡ ‹‹ ጋሪዶ ከልምምዱ በኋላ ያበረታቱኝ ሲሆን ከዚህ የተሸለ መሻሻል እንደሚገባኝም ነግረውኛል፡፡ ለአንድ ወርRead More →