ሀምበሪቾ ዱራሜን ባለፈው ዓመት ተረክበው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካሳደጉት አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ጋር ሶከር ኢትዮጵያ ቆይታን አድርጋለች። ሀምበሪቾ ዱራሜ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ ቡድኑን በመምራት በሊጉ ላይ መታየት እንዲችል በዋና አሰልጣኝነት በመምራት ለስኬት አብቅተውታል። ሀምበሪቾ ዱራሜን ባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ በዋናRead More →

ሻሸመኔ ከተማን ከ15 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደጉት አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ አጠር ያለ ቆይታን ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል። የ2015 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሦስት ምድቦች ተከፍሎ የአንደኛውን ዙር ጨምሮ በስድስት የተለያዩ ከተሞች ተደርጎ ተጠናቋል። በውድድሩ ምድብ ለ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት ከ15 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ሻሸመኔ ከተማRead More →

“ውጤቱ አደጋ ለደረሰባቸው ደጋፊዎቻችን መታሰቢያ ይሁንልን” ደግአረግ ይግዛው “በመጀመርያው አጋማሽ የሰራናቸው ስህተቶች ውጤቱን እንዳናገኝ አድርጎናል” ፋሲል ተካልኝ ደግአረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ ስለ ጨዋታው ጨዋታው ጥሩ ነበር። ጨዋታው በመጀመርያው አጋማሽ ለመጨረስ ስራዎች ሰርተናል። የፉዐድ አስገዳጅ ቅያሪም ትንሽ በማጥቃቱ እንድንቀንስ አድርጎናል ፤ በተረፈ ግን ከሽንፈት ነው የመጣነው። መድንም እየተጠጋ ነውRead More →

ጠንካራ ፉክክርን ያስመለከተን የባህርዳር ከተማ እና መቻል ጨዋታ በመጨረሻም በባህርዳር ከተማ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል። መቻሎች በመጨረሻ ደቂቃ ጎል ከሀዋሳ ጋር ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ከተጠቀሙት አሰላለፍ በሁለቱ ላይ ለውጥ አድርገዋል። ሳሙኤል ሳሊሶ እና ግርማ ዲሳሳን በበረከት ደስታ እና ከነዐን ማርክነህ ሲተኳቸው በ25ኛው ሳምንት ጨዋታ ባህርዳሮች በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ከገጠመው ስብስባቸው አደምRead More →

“ሥራው የተበላሸው የመጀመሪያው ምልመላ ላይ ነው።” – አሰልጣኝ ቅጣው ሙሉ “በቀጣይ አዳማ ላይ ለሚኖረን ቆይታ ይህ ትልቅ የሞራል ስንቅ ይሆነናል።” – አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ አሰልጣኝ ቅጣው ሙሉ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስለ ጨዋታው… “እንቅስቃሴው በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጥሩ ነበር። መጀመሪያ ግብ አስቆጠሩብን የገባው ጎልም አላስፈላጊ ነው ፤ ጥፋት ተሠርቶ ነበር። ከዛRead More →

ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ1 በመርታት በደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ ላይ ተቀምጦ የሀዋሳ ቆይታውን አጠናቋል። ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡናው ሽንፈቱ በሦስት ተጫዋች ላይ ለውጥ አድርጎ ገብቷል። ፔፕ ሰይዶን በያሬድ በቀለ ፣ዳግም በቀለን በሔኖክ አርፊጮ ፣ ዘካሪያስ ፍቅሬን በባዬ ገዛኸኝ ሲተካ በአርባምንጭ ከተርታው ስብስባቸው ኤሌክትሪኮች ደግሞ ዮናስ ሰለሞንን በሚኪያስ መኮንን በብቸኝነት የተኩበትRead More →

“ወራጁን እንኳን አሁን ሳይሆን በመጨረሻው ቀን ነው የሚለየው ብዬ አስባለሁ” አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ “ከታች የመጣ ነው ፣ ስሜቱን እረዳዋለሁ ፣ ግን ምንም እስካልሰራ ድረስ ከቡድኑ ማንም አይበልጥም” አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ወልቂጤ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የሀዋሳ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያለ ጎል ከፈፀሙ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው። አሰልጣኝ ገብረክርስቶስRead More →

የወልቂጤ እና ፋሲል የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት ፍፃሜን አግኝቷል። ወልቂጤ ከተማ ድል ካደረጉበት የመድኑ ጨዋታቸው ቅያሪ ሳያደርጉ ሲገቡ በአንፃሩ ከድሬዳዋው ሽንፈታቸው ፋሲሎች የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጡም አስቻለው ታመነን በዓለምብርሀን ይግዛው ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝን በዱላ ሙላቱ ተክተዋል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የዕለቱ ዋና ዳኛ ተካልኝ ለማ ፋሲሎች ያደረጉት መለያRead More →

“ቡድናችን ዛሬ ድክመት ነበረበት።” – አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ “ያለንን አቅም አውጥተን ነው የተጫወትነው።” – ምክትል አሰልጣኝ ለይኩን ታደሰ ኢትዮጵያ መድን የሀዋሳ ቆይታውን ኢትዮጵያ ቡና ላይ የ 2-1 ድል በመቀዳጀት ከቋጨ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ – ኢትዮጵያ ቡና ስለ ጨዋታው… “በመጀመሪያው አጋማሽ በጣምRead More →

ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 በመርታት የሀዋሳ ቆይታውን በድል ዘግቷል። ኢትዮጵያ መድን ከወልቂጤው ሽንፈት በሦስት ተጫዋች ላይ ቅያሪ አስፈልጎታል። ሐቢብ መሐመድ ፣ ዮናስ ገረመው እና ሀብታሙ ሸዋለምን በፀጋሰው ድማሙ ፣ አሚር ሙደሲር እና ወገኔ ገዛኸኝ ሲተኩ ሀድያ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ድል ካደረገው ስብስቡ ጉዳት በገጠመው ሬድዋን ናስር ምትክ ጫላ ተሺታንRead More →