“እኛ በጭቃ ሁለት ጊዜ ሁለት ቀን ሙሉ በተለያየ ቀን በተጫወትናቸው ጨዋታዎች ድካም አለብን” ሥዩም ከበደ “ባለንበት ቦታ ተጫዋቾች በመጠኑ ስሜታዊ ሆነዋል” በረከት ደሙ ሥዩም ከበደ – ሲዳማ ቡና ስለ ጨዋታው…? “ለእኛ በተለይ ወሳኝ ነው። ለእነርሱም ወሳኝ ነው። ከእኛ በበለጠ ትልቁ ነገር ሜዳችን ላይ አራት ጨዋታ አሸንፈናል ሁለት ጨዋታ አቻ ወጥተናልRead More →

በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ የተደረገው የሲዳማ ቡና እና የአርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል። ቡድኖቹ በተመሳሳይ የሁለት ተጫዋቾችን ለውጥ ባደረጉበት ለውጦቻቸው ሲዳማ ቡና ከድቻው የአቻ ውጤቱ አማኑኤል እንዳለን በደግፌ ዓለሙ እና እንዳለ ከበደን በይስሐቅ ከኖ ሲተኩ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ላይ ድልን ያሳኩት አርባምንጮች በበኩላቸው ወርቅይታደስ አበበን በአካሉ አትሞ እንዲሁም ቡጣቃRead More →

የሊጉ የውድድር እና ሥነ ስርዐት ኮሚቴ በሀዋሳ የሚደረጉ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ለውጥ ሲያደርግ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችም ተያይዘው ወጥተዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የውድድር እና ሥነ ስርዐት ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ቀጣዩ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሀዋሳ ከ12 ሰዓት በኋላ እየጣለ ባለው ሰሞነኛ ከባድ ዝናብ አንፃር የሀዋሳRead More →

ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዓመቱ ሦስተኛ አሰልጣኙን ሲያሰናብት ቀሪ ጨዋታዎችን በግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ይመራል። በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ የገነነ ስምን የያዘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ2011 ከፕሪምየር ሊጉ ከወረደ በኋላ ነበር በያዝነው ዓመት ዳግም መመለስ የቻለው። ክለቡ ከታችኛው የሊግ ዕርከን ካሳደገው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር ለሰባት የሊግ ጨዋታዎች ከቆየ በኋላ በምትኩ ለረዳትRead More →

“በእንደዚህ ዓይነት ሜዳ እንደዚህ ዓይነት ጨዋታ ተጫውተህ ማሸነፍ ትልቅ ነገር ነው” አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ “ጭቃው ትንሽ ከብዶን ነበር” አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ኢትዮጵያ ቡና በአማኑኤል ዮሐንስ እና መስፍን ታፈሰ ግቦች ታግዞ ሀድያ ሆሳዕናን ባሸነፈበት እና ደረጃውን ካሻሸለበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ስለ ጨዋታው… ጨዋታውRead More →

ኢትዮጵያ ቡና በአማኑኤል ዮሐንስ እና መስፍን ታፈሰ ጎሎች ሀድያ ሆሳዕናን 2-1 በማሸነፍ ደረጃውን ከፍ አድርጓል። ሀድያ ሆሳዕና የባህር ዳር ድሉ ላይ የተጠቀመበትን አሰላለፍ ሳይቀይር ለጨዋታው ሲቀርብ ከለገጣፎ ነጥብ የተጋሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በአንፃሩ ራምኬል ጀምስን በክዋኩ ዱሀ ፣ መሐመድ ኑርናስርን አብዱልከሪም ወርቁ ተክተው ቀርበዋል። ቀዝቀዝ ባለ ዐየር ጅምሩን ያደረገው የሁለቱ ቡድኖችRead More →

“የሜዳው ጭቃማነት እና የኛ የተቀዛቀዘ አቀራረብ ጨዋታውን ከባድ አድርጎብናል።” – ምክትል አሰልጣኝ ለይኩን ታደሰ “በዚህ ዓይነት ብቃት ልንወርድ አይገባም። ያንንም ተጫዋቾቼ ያሳካሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።” – አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ወልቂጤ ከተማ በጌታነህ ከበደ ግቦች ኢትዮጵያ መድንን 2-0 ከረታ በኋላ አሰልጣኝ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል። ምክትል አሰልጣኝ ለይኩን ታደሰ – ኢትዮጵያ መድንRead More →

ወልቂጤ ከተማ ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ መድንን 2ለ0 በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው ከፍ ያለበትን ውጤት አሳክቷል። ሁለቱ ቡድኖች ካለፈው ሳምንት ጨዋታቸው በሦስቱ ላይ ለውጥ ማድረግ አስፈልጓቸዋል። መድኖች ከሀዋሳው የአቻ ውጤታቸው ጀማል ጣሰው ፣ ማቲያስ ወልደ አረጋይ እና ኤፍሬም ዘካሪያስን በፋሪስ ዕላዊ ፣ ብዙአየው ስይፉ እናRead More →

“ምንም እንኳን ዝናቡ ቆመ እንጂ ሜዳው ጉልበት እና ኃይል የሚጠይቅ ነው” አሰልጣኝ ስዩም ከበደ “ሜዳው ከነበረበው ጭቃማነት አንፃር በጣም ጉልበት የሚጨርስ እና እልህ አስጨራሽ ነው” አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ትናንት በዝናብ ተቋርጦ የነበረው እና ዛሬ ቀትር በሁለተኛው አጋማሽ በበርካታ ደጋፊዎች መካከል የተደረገው የሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ያለ ጎል ከተጠናቀቀRead More →

ትላንት በዝናብ ተቋርጦ ዛሬ በሁለተኛው አጋማሽ የቀጠለው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ 0-0 ተቋጭቷል። ሲዳማ ቡና በፋሲሉ ድላቸው የተጠቀሙትን ቋሚ አሰላለፍ ቅያሪን ሳያደርጉ ለጨዋታው ሲቀርቡ ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ሽንፈት አንፃር ወላይታ ድቻዎች ቅጣት ባሰሰተናገደው ያሬድ ዳዊት ምትክ አናጋው ባደግን ተክተው ጀምረዋል። የቡድኖቹ ጨዋታ ከጀመረ ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ በጣለው ከባድ ዝናብRead More →