ዮናታን ሙሉጌታ (Page 90)

የስድስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማገባደጃ መርሀ ግብር 11: 45 ላይ መከላከያን ከጅማ አባ ቡና አገናኝቶ ጦሩ 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ። ቀዝቀዝ ባለ አየር እና በቀኝ ከማን አንሼ በኩል በዛ ብለው ጨዋታውን ሲያደምቁ በነበሩት የእንግዳው ቡድን ጅማ አባ ቡና ደጋፊዎች ሞቅ ያለ ዝማሬ የተጀመረው የሁለቱ ብድኖች ፉክክር የመጀመሪያ አጋማሽዝርዝር

  በአምስተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ስታድየም ላይሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ኢትዮጽያ ቡና 2-1 በማሽነፍ የአመቱን የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል። ባለሜዳው ኢትዮጵያ ቡና በ 4-3-3 አሰላለፍ ወደሜዳ ሲገባ ከግብ ጠባቂው ሀሪስተን ሄሱ ፊት ኤፍሬም ወንድወሰን እና ኤኮ ፌቨርን በመሀል ተከላካይነት እንዲሁም አብዱልከሪም መሀመድ እና አህመድ ረሽድ በቀኝና ግራ ተከላካይነት ተጠቅሟል።ዝርዝር

በአራተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ቀን ውሎ አዲስ አበባ ስታድየም ሁለት ጨዋታዎችን ሲያስተናግድ በ9፡00 መከላከያ ወልዲያን 2-0 ያሸነፈ ሲሆን በመቀጠል ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ እና ኤሌክትሪክ ባደረጉት ጨዋታ 1-1 ተለያይተዋል።   መከላከያ 2-0 ወልዲያ በወልዲያዎች የሜዳ ክልል ላይ ባመዘነው የመጀመሪያ ግማሽ የጨዋታ ሂደት ገና በ2ኛው ደቂቃ ነበር ሳሙኤል ታዬ ሶስትዝርዝር

በ3ኛ ሳምንት የኢትዮጽያ ፕርሚየር ሊግ በደቡብ ደርቢ አርባምንጭ ከተማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ በፍሬው ሰለሞን የሁለተኛ አጋማሽ ግቦች በመታገዝ 2-0 አሸንፏል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ህይወቱ ያለፈው የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠበቂ ክብረዐብ ዳዊትን በህሊና ፀሎት በማሰብ ነበር የተጀመረው ። ይህንን አሰቃቂ አጋጣሚን በማስመልከትም የሀዋሳዝርዝር

በ2ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትልቅ ግምት ያገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት ጨዋታ በፈረሰኞቹ የበላይነት ተጠናቋል፡፡ በጨዋታው የታዩ ታክቲካዊ ጉዳዮችን ሶከር ኢትዮጵያ እንደተለመደው ይዛላችሁ ቀርባለች። የመጀመሪያ አሰላለፍ ደደቢት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በሚታወቁበት የ4-4-2 ቅርፅ ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን ከሁለቱ የመሀል አማካዮች አስራት መገርሳ በተከላካይ አማካይነት እንዲሁም ሳምሶን ጥላሁን ከሳጥን እስከሳጥንዝርዝር

የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታድየም በይፋ ሲጀመር የአምናው ቻምፒዮን ቅድስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከተማን ባስተናገደበት ጨዋታ 3-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። ሶከር ኢትዮጵያም የጨዋታውን ታክቲካዊ ይዘት እንደሚከተለው ይዛላችሁ ቀርባለች። ባለሜዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደተለመደው በ 4-3-3 ቅርፅ ወደሜዳ ሲገባ በመሀል ተከላካይነት አይዛክ ኢዜንዴ እና አስቻለው ታመነ ባልነበሩበት ደጉ ደበበንዝርዝር

ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት ቀጥለው ሲካሄዱ በአዲስ አበባ ስታዲየም ማምሻውን በተደረገው ጨዋታ በሊጉ ሁለተኛ ዙር በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር ደደቢትን 3-0 ረቷል፡፡  ሶከር ኢትዮጵያ የጨዋታውን ታክቲካዊ ጉዳዮች እንደሚከተለው ታስቃኛለች፡፡ የቡድኖቹ ጨዋታ አቀራረብ በያዝነው የውድድር ዓመት የቡድኑ የመጀመሪያ አሰላለፎች ላይ የፊት አጥቂነቱንዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ባለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄዱ ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ደደቢት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በገጠሙበት የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ንግድ ባንኮች በፊሊፕ ዳውዚ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡ በጨዋታው ላይ የነበሩ ዋና ዋና ታክቲካዊ ጉዳዮችንም እንደተለመደው ሶከር ኢትዮጵያ ይዛላችሁ ቀርባለች፡፡ ከሳምንት በፊት በሁለተኛው ዙር መጀመሪያዝርዝር

የ2008 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ተጠናቆ ሁለተኛው ዙር ሲጀምር ከትላንት በስትያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ የዙሩ መጀመሪያ ፍልሚያ ነበር፡፡ በ90+5ኛው ደቂቃ ላይ በተገኘችው የያቤውን ዊልያም የፍፁም ቅጣት ምት ጎል በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት የተጠናቀቀውን የዚህን ጨዋታ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ሶከር ኢትዮጵያ እንደሚከተለው አቅርባላችኋለች፡፡ዝርዝር

  ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ በተደጋጋሚ ጨዋታዎች ነጥብ ሲጥል የቆየው ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የተቀመጠውን ሀዲያ ሆሳዕናን በጨዋታው መገባደጃ ላይ በተገኘችው የፓትሪክ ጐል በመታገዝ 2-1 በሆነ ውጤት ለመርታት ችሏል፡፡ የሶከር ኢትዮጵያው ዮናታን ሙሉጌታ በዛሬው የታክቲክ ትዝብቱ በጨዋታውን የታዩ ዋናዝርዝር