ነብሮቹ በስብስባቸው ላይ ለውጦችን በማድረግ በአዲሱ የውድድር ዘመን ወጥ አቋም ለማሳየት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ፤ እኛም በተከታዩ ፅሁፋችን የቡድኑን ዝግጅት ዳሰናል። በ2014 የውድድር ዘመን እጅግ የተቀዛቀዘ አጀማመርን በማድረግ ከመጀመሪያዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ሦስት ነጥቦችን ብቻ አግኝተው የነበሩት ነብሮቹ ከዚህ አስከፊ አጀማመር መልስ ምንም እንኳን በወጥነት ውጤቶችን ለማስመዝገብ ቢቸገሩም ዓመቱን ከወራጅ ቀጠና በጥቂቱRead More →

ኢትዮጵያ ቡና ራሱን በአዲስ መልክ አደራጅቶ ለሊጉ ፍልሚያ ያዘጋጀበትን መንገድ በቀጣዩ ፅሁፋችን ተመልክተነዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከጀመረ አንስቶ በተሳታፊነት ከቆዩ ሁለት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና 25ኛ የውድድር ዓመቱን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል። አንድ ጊዜ ቻምፒዮን መሆን የቻሉት ቡናዎች ያለፈው ዓመት ጉዟቸው እንዳሰቡት ስኬታማ አልነበረም። የመጀመሪያ ድሉን ለማሳካት አምስት ሳምንታትRead More →

ከሦስት የውድድር ዘመናት በኋላ ዓምና ዳግም የሊጉን ዘውድ የደፉት ፈረሰኞቹ በተረጋጋ የቡድን ስብስብ ዘንድሮም የተሻሉ ሆነው ስለመቅረብ ያልማሉ ፤ ሶከር ኢትዮጵያም በተከታዩ ዳሰሳ ለአዲሱ የውድድር ዘመን ስላደረጉት ዝግጅት ልታስቃኛችሁ ወዳለች። በ2014 የውድድር ዘመን በ30 የጨዋታ ሳምንታት በአንዱ ብቻ ሽንፈትን በማስተናገድ በድምሩ 65 ነጥቦች በማሳካት ከሦስት የውድድር ዘመናት ቆይታ በኋላ አስራRead More →

ለገጣፎ ለገዳዲ የታሪኩን የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ለማድረግ ከወትሮው የአዲስ አዳጊዎች መንገድ የተለየ አቅጣጫን መርጧል። ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ ዕርከን ለማደግ ከፍ ያለ ፉክክር በሚደረግበት የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከ2009 ጀምሮ ሲፋለም የቆየው ለገጣፎ ለገዳዲ በተለይም በ2011 እና በኮቪድ ምክንያት በተቋረጠው ቀጣዩ የውድድር ዓመት ሊጉን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ ሳይሳካለት ቀርቶ ነበር።Read More →

ያለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ለአዳማ ከተማዎች እምብዛም ለማስታወስ የሚፈልጓቸው እንዳልነበሩ መናገር ይቻላል ፤ ዘንድሮ ይህን ሂደት ለመቀልበስ በቀድሞው ኮከባቸው እየተመሩ ውድድሩን በተስፋ ይጀምራሉ። እኛም ዝግጅታቸው ምን ይመስላል ስንል ተከታዩን ፅሁፍ አሰናድተናል። በ2014 የውድድር ዘመን አዳማ ከተማዎች ከተወሰኑ ጨዋታዎች በስተቀር በአመዛኙ ጨዋታዎች ከተጋጣሚዎቻቸው በተሻለ መንቀሳቀስ ቢችሉም ከጨዋታዎች ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዘውRead More →

በ1980ዎቹ አጋማሽ ከሀገር አልፎ በአህጉራዊ ውድድሮች የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው ቡድን ከ1990ዎቹ መጨረሻ አንስቶ የነበረው ገናናነት ታሪክ ሆኖ አሁን ላይ ሊጉን ከስምንት ዓመታት ጥበቃ በኋላ ዳግም ተቀላቅሏል ፤ እኛም በዚህኛው ፅሁፋችን መድን ራሱን ለፕሪሚየር ሊግ ህይወት እያዘጋጀበት ስላለው መንገድ ተከታዩን ዳሰሳ አሰናድተናል። በኢትዮጵያ እግርኳስ በቀደመው ዘመን በገናናነታቸው ከሚጠቀሱ ክለቦች አንዱRead More →

በሊጉ ሰንጠረዥ ቀዳሚዎቹን ሁለት ስፍራዎች ይዘው ስለማጠናቀቅ የሚያልሙት ሲዳማ ቡናዎች በአሰልጣኙ እምነት ካለፉት ዓመታት የተሻለውን ስብስብ ይዘው አዲሱን የውድድር ዘመን የሚጀምሩ ይሆናል ፤ እኛም የክቡን የአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅት በተከታዩ ፅሁፋችን ዳሰነዋል። ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በሊጉ እጅግ ደካማ አጀማመርን አድርገው የነበሩት ሲዳማዎች ከውጤት ማጣት ባለፈ በቡድኑ አባላት እና በደጋፊዎቹ መካከልRead More →

አርባምንጭ ከተማ ከአምናው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በነባር ስብስቡ ላይ መጠነኛ ለውጦችን አድርጎ መቅረብን መርጧል። ከሰባት ዓመታት የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ በኋላ ወደ ሁለተኛው የሊግ ዕርከን የወረደው አርባምንጭ ከተማ ወደ ሊጉ ያደረገውን ምልሰት ዐምና በመልካም ውጤት አጅቦ ጨርሷል። በመጣበት ዓመት ከሊጉ ወገብ በአንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ያገባደደው አርባምንጭ በተወሰኑ ሳምንታት ላለመውረድ ከሚጫወቱRead More →

ያለፉትን የውድድር ዓመታት በደረጃ ሰንጠረዡ የታችኛው ፉክክር ራሱን ሲያገኝ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ የዘንድሮውን የሊግ ውድድር ሊቀርብ ያሰበበትን መንገድ እና ዝግጅት አስመልክቶ ተከታዩን ዳሰሳ አሰናድተናል። 1975 ላይ የተመሰረተው ድሬዳዋ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መልክ 1990 ላይ ከተጀመረ በኋላ ለ10ኛ ጊዜያት ተሳትፏል። እርግጥ ክለቡ በእነዚህ ዓመታት በአብዛኞቹ ላለመውረድ በሚደረገው ፉክክር እራሱንRead More →

የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የቅድመ ውድድር ዝግጅትን የተመለከቱ መረጃዎች ላይ የሚያተኩረው ፅሁፋችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስመለክተናል። የአስራ አራት ጊዜ የሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘንድሮ በሀገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ብቻ የሚሳተፍበትን የውድድር ዓመት ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ከ2006 አንስቶ ለተከታታይ አራት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ጊዮርጊስ አምና አምስተኛውን ለመድገም ያደረገው ጥረት እስከ 30ኛውRead More →