የአፍሪካ ዋንጫ

ባሳለፍነው ሳምንት የወጣውን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድልን በተመለከተ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ገለፃ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ ከሰዓት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መግለጫ ሰጥተዋል። ዝግጅታቸውን በተመለከተ የተነሳውን ሀሳብ ከደቂቃዎች በፊት ያስነበብን ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንትዝርዝር

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎ እና በቀጣይ ስለሚገጥማቸው የምድብ ቡድኖች ዕውነታ ተከታዩን ጥንክር አዘጋጅተናል። 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በቀጣይ ዓመት በካሜሩን አስተናጋጅነት እንደሚከናወን ይታወቃል። የውድድሩ የምድብ ድልድልም ከደቂቃዎች በፊት በካሜሩን ያውንዴ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ወጥቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ ካሜሩን፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኬፕ ቬርድ ጋር መደልደሉ እርግጥ ሆኗል።ዝርዝር

በካሜሩን አስተናጋጅነት በሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ ሀገራት የምድብ ድልድላቸውን አውቀዋል። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በካሜሩን በተከናወነው የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ላይ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪክ ሙሴፔን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴሬሽን አመራሮች፣ የቀድሞ ተጫዋቾች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የካፍ የውድድር ዳይሬክተር ሳምሶን አዳሙ የቀድሞ ተጫዋቾቹን ሳሙኤል ኢቶ፣ ጋዬል ኢንጋናሙቲ፣ ራባህ ማጄር፣ዝርዝር

ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ትልቁ አህጉራዊ ውድድር የተመለሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ተጋጣሚዎቹን አውቋል። በቀጣይ ዓመት በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማለፉ ይታወቃል። 24 ተሳታፊዎች ያሉበት ትልቁ የአህጉሩ ሀገራት ውድድር ከጥር 1 – 29 (ጃኑዋሪ 9 – ፌብሩዋሪ 6) ድረስ የሚደረግ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊትዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ነገ ማለዳ ከሀገር ውጪ ጉዞ እንደሚያደርጉ ታውቋል። ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለመብቃት ከፊቱ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጠብቁት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዳማ መቀመጫውን በማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል። የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ውበቱ አባተም ቡድኑን በቀን ሁለት ጊዜ እያዘጋጁት የሚገኝ ቢሆንም ነገ ማለዳ ግን ወደ ካሜሩንዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊው ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር አቅንተዋል። በካሜሩን አስተናጋጅነት በቀጣይ ዓመት በሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ በየትኛው ምድብ ትደለደላለች የሚለውን ነገ አመሻሻሽ ላይ በካሜሩን ያውንዴ ከተማ የሚታወቅ ይሆናል። በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደምም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ እና ዋና ፀሐፊውዝርዝር

ዋልያዎቹ የሚሳተፉበት የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል መራዘሙን ተከትሎ በቀጣይ መቼ ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል። ወደ 2022 የተዘዋወረው የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ 24 የአህጉሪቱን ብሔራዊ ቡድኖች ለማፋለም ቀን እየጠበቀ ይገኛል። ከሦስት ቀን በፊትም በውድድሩ የሚሳተፉት ሁሉም ሀገራት ተለይተው ታውቀዋል። የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ የሆነው ካፍ ከጥር 1 እስከ 29 እንደሚደረግ የተገለፀውን ውድድር አራትዝርዝር

በኮቪድ ውዝግብ ምክንያት ከተያዘለት ጊዜ እጅግ ተራዝሞ በዛሬው ዕለት የተከናወነው የሴራሊዮን እና የቤኒን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ከደቂቃዎች በፊት ተጠናቋል። ከ2021 ወደ 2022 የተዘዋወረው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የአህጉሪቱ ብሔራዊ ቡድኖች በአስራ ሁለት ምድብ ተከፋፍለው የምድብ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ እንደነበር ይታወሳል። ከአንደኛው ምድብ አንድ ጨዋታ ውጪም ሁሉም ጨዋታዎች ተጠናቀው ወደዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደመሠረተው የአፍሪካ ዋንጫ ሲመለስ የዋልያዎቹ አሠልጣኝ እና ተጫዋቾች ያጋሩትን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ሰብስበን ይዘን ቀርበናል። በምድብ 11 ተደልድሎ ካሜሩን ለምታስተናግደው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ሲያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በትናንትናው ዕለት ሦስት ለአንድ ያሸነፈውን የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድንን ተከትሎ ወደ አፍሪካዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች በተፈጠሩ ድራማዊ ክስተቶች ታጅቦ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈበትን ጣፋጭ ዕድል አግኝቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከቀናት በፊት የማዳጋስካር አቻውን በባህር ዳር ካሸነፉበት ቀዳሚ አሰላለፍ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ተክለማርያምም ሻንቆ፣ አስራት ቱንጆ፣ ያሬድ ባዬህ፣ አስቻለው ታመነ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ዝርዝር