Soccer Ethiopia

የአፍሪካ ዋንጫ

ዋልያዎቹ በኒያሜ የመጀመርያ ልምምድ አከናውነዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኒጀር የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ሰርቷል። ለካሜሩኑ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ ትናንት ወደ ሥፍራው ያቀናው ብሔራዊ ቡድኑ ከሰዓት በኋላ ኒያሜ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን በኑም ሆቴል ማረፊያውን አድርጎ ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በብሔራዊ ስታዲየም ግቢ ውስጥ በሚገኝ የመለማመጃ ሜዳ የመጀመርያ ልምምድ ማከናወኑን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ዋልያዎቹ ሜዳው ለልምምድ ምችት የማይሰጥ ቢሆንም የልምምድ ፕሮግራሙን […]

ዋልያዎቹ ኒያሜ ደርሰዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ኒጀር ደርሷል። ካሜሩን ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከኮትዲቯር፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር ጋር ተደልድሎ የማጣሪያ ጨዋታዎቸን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎችን ለማድረግ የመጨረሻ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ቡድኑም በትናንትናው ዕለት የመጨረሻ ልምምዱን መቀመጫውን አድርጎበት በነበረው የካፍ የልህቀት ማዕከል ካከናወነ በኋላ ዛሬ ረፋድ 5 […]

አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ | ወደ ኒጀር የሚጓዙ 23 ተጫዋቾች ይፋ ሆነዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ የምድብ ማጣርያ ከኒጀር ጋር ኒያሜ ላይ ይጫወታል። ወደ ስፍራዎ የሚጓዙ 23 ተጫዋቾችም ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል። በዚህ መሰረት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በስብስባቸው ከነበሩት 26 ተጫዋቾች መካከል ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ አማካዩ ሀብታሙ ተከስተ እና ጉዳት ላይ የሚገኘው ሙጂብ ቃሲም አብረው የማይጓዙ ሲሆን አሰልጣኙ ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ ባስታወቁት መሰረት […]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወቅታዊ መረጃዎች

በኅዳር ወር መጀመርያ ከኒጀር ጋር የምድቡን ሦስተኛ እና አራተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርገት ዋልያዎቹ አሁን የሚገኙበትን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲህ አጠናቅረናል። * ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት በሚጫወትበት የግብፅ ሊግ ውድድር የነበረበት በመሆኑ ቡድንን ሳይቀላቀል የቆየው ሽመልስ በቀለ ትናንት አመሻሽ ላይ አዲስ አበባ መግባቱ ተረጋግጧል። ሆኖም ዛሬ ልምምድ ይጀምራል ቢባልም ሐሙስ በግብፅ ሊግ ጨዋታ የነበረው በመሆኑ ዛሬ […]

ይህን ያውቁ ኖሯል? (፮) | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ…

ዕለተ ሐሙስ ወደ እናንተ በምናደርሰው ይህን ያውቁ ኖሯል? አምዳችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የተመለከቱ ዕውነታዎችን ለአምስት ተከታታይ ሳምንታት ስናቀርብ ቆይተናል። ዛሬም ብሔራዊ ቡድኑን የተመለከቱ ነጥቦችን አጠናክረን በተከታይ ክፍል ይዘን ቀርበናል። (1) – ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው 22 የማጣርያ ውድድሮች በአጠቃላይ 107 ጨዋታ ያደረገች አከናውናለች። የጨዋታ ብዛቱም ፎርፌ እና የተሰረዙትን ውጤቶችን ያካተተ ነው። – ኢትዮጵያ ካከናወነቻቸው 107 ጨዋታዎች መካከል […]

ሽመልስ በቀለ ብሔራዊ ቡድኑን የሚቀላቀልበት ቀን ታውቋል

የዋልያዎቹ አንበል እና ቁልፍ ተጫዋች የሆነው ሽመልስ በቀለ ዋልያዎቹን የሚቀላቀልበት ቀን ታውቋል። በቀጣይ ወር መጀመርያ ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ምድብ ማጣርያ ጨዋታዋን ከኒጀር ጋር የምታደርገው ኢትዮጵያ ዋሳኙ ተጫዋቿን የፊታችን አርብ የምታገኝ ይሆናል። ሽመልስ አርብ ጠዋት አዲስ አበባ በመግባት ወድያውኑ ከሰዓት አልያም ቅዳሜ ከቡድኑ ጋር በመቀላቀል ልምምድ እንደሚጀምር ለማወቅ ችለናል። የአማካዩ ስብስቡን በመቀላቀል በቡድኑ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት […]

የብሔራዊ ቡድኑ ስድስት ተጫዋቾች ጉዳይ…?

በሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ ያልተሰለፉት ስድስት ተጫዋቾች ጉዳይ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል ? በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አሁጉራዊ ውድድሮች መቋረጥ በኃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዲስ አሰልጣኝ እየተመራ ለአርባ አንድ ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከሳምንታት በፊት አያት በሚገኘው የካፍ ልኅቀት ማዕከል ሲዘጋጅ መቆየቱ ይታወቃል። የቡድኑን ወቅታዊ ሁኔታ ለመመልከት እንዲረዳ እና ክፍተቶቹን ከዋናው […]

መስፍን ታፈሰ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጪ ሆኗል

አጥቂው መስፍን ታፈሰ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆኗል፡፡ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አማካኝነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የኒጀሩ የደርሶ መልስ ጨዋታ ለአርባ አንድ ተጫዋቾች ጥሪ ሲደረግ የሀዋሳ ከተማው አጥቂ መስፍን ታፈሰ ከተጠሩት መካከል አንዱ ነበር፡፡ ሆኖም ተጫዋቹ ለሙከራ ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ጳጉሜ 4-2012 አምርቶ ፉትሮ ኪንግስ ለተባለ ክለብ ለአምስት ቀናት የሙከራ ጊዜ እንደሚያሳልፍ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ በጊኒው […]

“ወደ አፍሪካ ዋንጫ የምናደርገው ጉዞ የሚወሰነው ከኢትዮጵያ ጋር በምናደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ነው” – ዣን ሚሸል ካቫሊ

አዲሱ የኒጀር ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዣን ሚሸል ካቫሊ የቡድናቸው የአፍሪካ ዋንጫ ተስፋ በኢትዮጵያ የደርሶ መልስ ጨዋታ እንደሚወሰን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ለተዘዋወረው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ጋር የተደለደለችው ኒጀር ከሳምንታት በፊት አዲሱን የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዣን ሚሸል ካቫሊን በይፋ የቡድኗ ዋና አሠልጣኝ አድርጋ መሾሟ ይታወሳል። የ63 ዓመቱ ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ካቫሊም ቡድኑን ለ2022 […]

የኒጀር እና የኢትዮጵያን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ኅዳር 4 በኒያሜው ስታድ ጀነራል ሴኒ ኮንቼ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን የኒጀር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታን የላይቤሪያ ዜግነት ያላቸው ዳኞች ይመሩታል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ልምምዱን አዲስ አበባ በሚገኘው የካፍ አካዳሚ እየሰራ ቀናቶችን አስቆጥሯል፡፡ ቡድኑ ከልምምድ ባለፈም በወዳጅነት ጨዋታ ባለፈው ሐሙስ ከዛምቢያ አቻው ጋር የተገናኛ ሲሆን በነገው ዕለትም […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top