ቻምፒዮንስ ሊግ

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉት ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከማን ጋር እንደሚያደርጉ ነገ ያውቃሉ። በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 54 እና 41 ነጥቦችን በመያዝ አንደኛ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ከፊታቸው ላለባቸው አህጉራዊ ውድድር ዝግጅት ማድረግዝርዝር

ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ባህር ዳር የከተመው ፋሲል ከነማ ልምምድ ሲጀምር ሁለቱ ተጫዋቾችም ስብስቡን ተቀላቅለዋል። በአሠልጣኝ ሥዩም ከበደ የሚመሩት የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ፋሲል ከነማዎች ከዓመቱ መገባደጃ ቀናት ጀምሮ ላለባቸው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለማድረግ ከትናንት በስትያ በባህር ዳር ከተማ እንደተሰባሰቡ ዘግበን ነበር። ለብሔራዊዝርዝር

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚወክለው ፋሲል ከነማ ለውድድሩ ዝግጅት ባህር ዳር ገብቷል። የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከነማ ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር እና ለቀጣይ ዓመት የሊጉ ፍልሚያ ራሱን ለማጠናከር ከአንድ ወር በላይ ባስቆጠረው የዝውውር መስኮት ገበያ ላይ በመውጣት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ ራሱን ሲያጠናክር ሰንብቷል።ዝርዝር

የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ በጳጉሜ ወር ላለበት የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እና ለ2014 የሀገር ውስጥ ውድድር በቀጣዩ ሳምንት ወደ ዝግጅት ይገባል፡፡ በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ እየተመራ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2013 ቻምፒዮን መሆን የቻለው ፋሲል ከነማ ለሦስተኛ ጊዜ በአፍሪካ መድረክ ውድድር ያደርጋል፡፡ በተከታታይ ለሁለት ዓመታትዝርዝር

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነው መቐለ 70 እንደርታ ባለው የተጫዋች ብዛት ለመሳተፍ ለካፍ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንድርታ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር ግብፅ ላይ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ጨዋታ እንዲያደርግ ካፍ አስቀድሞ መርሐግብር ቢያወጣም አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊዝርዝር

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው መቐለ 70 እንደርታ ጉዳይ መፍትሄ ያስገኛል የተባለ ደብዳቤ ወደ ካፍ ተልኳል። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን መደልደሉ ይታወቃል። በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ከኅዳር 18 – 20 ባሉት ቀናት ከሜዳው ውጭ ግብፅዝርዝር

በአፍሪካ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው መቐለ 70 እንደርታ ከአንድ ሳምንት በኋላ ያለበትን ጨዋታ አሰመልክቶ በምን ሁኔታ ይገኛል? የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ እና የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ ፋሲል ከነማ በአፍሪካ የክለቦች ውድድር ኢትዮጵያን እንደሚወክሉ ይታወቃል። ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን የተደለደው ኢትዮጵያዊውዝርዝር

ኢትዮጵያን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚወክሉት መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ  የቅድመ ማጣርያ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንድርታ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር ሲደለደል ይህን ዙር የሚያልፍ ከሆነ በአንደኛ ዙር የቱኒዚያው ጠንካራ ክለብ ኤስፔራንስ ደ ቱኒስን የሚገጥም ይሆናል። በዛው ዓመት የኢትዮጵያ ጥሎዝርዝር

በዚህ የውድድር ዓመት በካፍ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች እንደሌሉ ቢወሰንም በቀጣይ የኢትዮጵያ ክለቦች በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ውድድሮች ላይ የመሳተፋቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ በትላንትናው እለት የ2020/21 የቻምፒየንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ውድድሮች የሚደረጉበትን የጊዜ ሰሌዳ አስታውቋል። ካፍ መርሐ-ግብሩን ሲያወጣ ጎን ለጎን በተሳታፊ ክለቦችዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኩባንያ የዘንድሮ የውድድር ዘመን በኮሮና ምክንያት እንዲሰረዝ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የአፍሪካ ውድድር ተሳትፎ አለመኖር ውሳኔን እንደሚቃወም መቐለ 70 እንደርታ አስታውቋል። ክለቡ ለሊግ ኩባንያው በላከው ባለ ሦስት ገፅ ደብዳቤ የሊጉን መቋረጥ እንደሚቀበለው የገለፀ ሲሆን የአፍሪካ ውድድር ተሳታፊዎች እንዳይኖሩ መወሰኑ ግን አግባብ አለመሆኑን አስቀምጧል። የአፍሪካ ውድድር አለመኖር ያለውን ተፅዕኖዝርዝር