Soccer Ethiopia

ቻምፒዮንስ ሊግ

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ይመራሉ

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲከናወኑ አንጎላ ላይ የሚደረገው ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመራል። የአንጎላው ፔትሮ ዲ ሎዋንዳ ከ ዩኤስኤም አልጀር የሚደርጉትን ይህን ጨዋታ በአምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ሲመራው ረዳት ዳኞች ደግሞ ክንዴ ሙሴ እና ተመስገን ሳሙኤል እንዲሁም አራተኛ ዳኛ በላይ ታደሰ እንዲሆኑ ተመድበዋል። ፔትሮ ሉዋንዳ ከዚህ ቀደም በቻምፒየንስ ሊጉ ማጣርያ ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ […]

ካፍ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይ ቅጣት አስተላልፏል

(መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው) የ2011ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ከተያዘላቸው ጊዜ በመዝግየት መጠናቀቃቸው ይታወሳል። የመዘግየታቸው ዋንኛ ምክንያቶች በስታዲየሞች አካባቢ የነበሩ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደሎች እና ሀገራዊ የነበሩ ጸጥታ ችግሮች ውድድሮች ላይ ጫና የፈጠሩ እና በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ምክንያት ሆነዋል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአፍሪካ ቻንፒዮንስ […]

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ይመራሉ

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ሲከናወኑ ሉዋንዳ ላይ የሚደረገው ጨዋታም በኢትዮጵያ ዳኞች ይመራል። የአንጎላው ፔትሮ አትሌቲኮ ሎዋንዳ እና በዩጋንዳው ኬሲሲኤ መካከል የሚደረገው ይህ ጨዋታ ሎዋንዳ ላይ በ12፡00 የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታውንም በላይ ታደሰ በዋና ዳኝነት፣ ክንዴ ሙሴ እና ትግል ግዛው ደግሞ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ብሩክ የማነብርሃን በአራተኛ ዳኝነት እንዲመሩ እንዲሆኑ በካፍ […]

የአሰልጣኞች አስትያየት | መቐለ 70 እንደርታ 1-1 ካኖ ስፖርት አካዳሚ

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ከካኖ ስፖርት ጋር 1-1 አቻ ተለያይቶ በድምር የ3-2 ሽንፈት ወደ ተከታዩ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል። የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞችም ከጨዋታ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል። “ከድላችን ጀርባ ያለው ነገር ቡድናችን ህዝባዊና የአካዳሚ ቡድን መሆኑ ነው” ሌቪኢላ አንገዝሙ (የካኖ አሰልጣኞች ቡድን አባል) ስለ ጨዋታው ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር። መቐለ በጣም […]

ሪፖርት | መቐለ 70 እንደርታ ከካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ውጭ ሆኗል

የኢኳቶርያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚን በመልስ ጨዋታ የገጠሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አቻ በመለያየታቸው በድምር ውጤት ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል። በግሩም የደጋፊዎች ድባብ በጀመረው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታዎች ከመጀመርያው ዙር ተሰላፊዎቻቸው ውስጥ በያሬድ ከበደ እና ታፈሰ ሰርካ ምትክ ያሬድ ብርሃኑ እና ኄኖክ ኢሳያስን ተጠቅመዋል። ከመጀመርያው ደቂቃ አንስተው አጥቅተው ለመጫወት ድፍረት የነበራቸው መቐለዎች ለግብ የቀረበ ሙከራ ለማድረግ ብዙ […]

መቐለ 70 እንደርታ ከ ካኖ ስፖርት አካዳሚ – ቀጥታ የውጤት መግለጫ

እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2011 FT’ መቐለ 70 እ. 1-1 ካኖ ስፖርት አ. ድምር ውጤት፡ 2-3 11′ አማኑኤል ገ/ሚካኤል 37′ ቤንጃሚን ናኦኔ ቅያሪዎች 54′  ሐይደር  ኤፍሬም 32′  ኦቢያንግ  ኢሪያ 62′  ያሬድ  ሙሉጌታ 63′  ቤርናርዶ ካኩ 70′  ሄኖክ  ታፈሠ – ካርዶች 35′  ሄኖክ ኢሳይያስ 58′  ዮናስ ገረመው 7′  ቪሰንት ኦሳሙ 42′  ፓብሎ ቤርናርዶ 56′  መሪየም ኦንዶ አሰላለፍ መቐለ 70 እንደርታ ካኖ ስፖርት አካዳሚ 1 ፊሊፕ ኦቮኖ 13 ሥዩም ተስፋዬ 2 አሌክስ […]

ቻምፒየንስ ሊግ | ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች አመሻሽ ላይ የመጨረሻ ልምምዳቸውን አጠናቀዋል

የመቐለ 70 እንደርታ ተጋጣሚ ካኖ ስፖርት አካዳሚ የመጨረሻ ልምምዳቸው ሲያከናውኑ ዋና አሰልጣኙም ሃሳባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል። በመጀመርያው ዙር በሜዳቸው የኢትዮጵያው መቐለ 70 እንደርታን ሁለት ለአንድ አሸንፈው ለመልሱ ጨዋታ ትናንት ኢትዮጵያ የገቡት ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች ዛሬ ጠዋት መቐለ በመግባት አመሻሽ ላይ በትግራይ ስቴድየም ልምምድ ሰርተዋል። ሳይጠበቅ ከተለመደው አሰራር ወጣ ብለው በመጨረሻው ልምምድ ረጅም ሰዓት የወሰደ እና […]

ቻምፒየንስ ሊግ | መቐለ 70 እንደርታዎች የመጨረሻ ልምምዳቸውን አከናውነዋል

ምዓም አናብስት ለነገው ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅታቸው አጠናቀዋል። በቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ነገ 9:00 የኢኳቶሪያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚን የሚገጥሙት መቐለ 70 እንደርታዎች ዛሬ የመጨረሻው ልምምዳቸው አከናውነዋል። በርከት ባሉ ደጋፊዎች ታጅበው ልምምዳቸው ያከናወኑት መቐለዎች በጉዳት ከዚ ጨዋታ ውጭ ከሆነው ያሬድ ከበደ ውጭ ሙሉ ቡድኑን በዚ ልምምድ ያሳተፉ ሲሆን ለወሳኙ ጨዋታ የሚከተሉት አጨዋወት ላይም ፍንጭ አሳይተዋል። በመጀመርያው […]

ቻምፒየንስ ሊግ| የመቐለ ጨዋታ በሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ ይተላለፋል

በመጪው እሁድ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ከካኖ ስፖርት አካዳሚ የሚያደርጉትን ጨዋታ የትግራይ መገናኛ ብዙሀን (ኤመሐት) እና ድምፂ ወያነ ትግራይ ቀጥታ የቴሌቪዥን ሽፋን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንዳጠናቀቁ ገልፀዋል። ባለፈው የውድድር ዓመት የመቐለ የሜዳ ላይ ጨዋታዎች የቀጥታ ሽፋን የሰጠው ትግራይ ቴሌቭዥን ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ በድጋሚ የክለቡን ጨዋታ በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን በቅርቡ የቴሌቭዥን ስርጭት […]

ቻምፒየንስ ሊግ| ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች አዲስ አበባ ገብተዋል

በቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታ ተጋጣሚ የሆኑት ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች ትናንት አመሻሽ አዲስ አበባ ገብተዋል። በውድድሩ እንደ መቐለ ሁሉ የመጀመርያ ተሳትፏቸውን እያደረጉ የሚገኙት ካኖዎች በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ በመግባት አፎሊ ሆቴል ማረፍያቸውን ሲያደርጉ ለኢኳቶርያል ጊኒ ብሄራዊ ቡድን ያስመረጧቸው የቡድኑ ወሳኝ ተከላካይ ቪሴንቴ አሲሙ እና አጥቂው ልዊስ ሚግዌል ኔቮን ጨምሮ የመጀመርያው ዙር […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top