ሴካፋ (Page 2)

ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ከሰዓት ይከናወናል። 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በ23 ዓመት በታች ቡድኖች መካከል ከሐምሌ 10 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ይደረጋል። ምንም እንኳን በውድድሩ የሚሳተፉ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች ቀስ በቀስ ራሳቸውን እያገለሉ ቢመጡም ባሉት ሀገራት የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩ በዛሬው ዕለትዝርዝር

የፊታችን ቅዳሜ ለሚጀመረው የሴካፋ ውድድር በአዲስ አበባ ሲዘጋጅ የከረመው ብሔራዊ ቡድኑ አንድ ተጫዋች ቀንሶ በምትኩ ለአንድ ተጫዋች ጥሪ በማድረግ አመሻሽ ባህር ዳር ደርሷል። ለ41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሰኔ የመጀመሪያ ቀናት አንስቶ ሲዘጋጅ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አመሻሽ ላይ ውድድሩ ወደሚደረግበት ባህር ዳር ከተማ አቅንቷል። እርግጥ ብሔራዊ ቡድኑዝርዝር

ዛሬ ረፋድ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደረገው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ ባህር ዳር ከማምራቱ በፊት ምሽት ላይ አሸኛኘት ተደርጎለታል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በሚደረገው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ጠንካራ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። በሳምንቱ አጋማሽ ከኢትዮጵያ መድህንዝርዝር

በተጋባዥነት በሴካፋ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ ሲጠበቅ የነበረው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ ከውድድሩ ራሷን አግላለች ቢባልም ከሦስት ቀን በኋላ ለውድድሩ ሀገራችን እንደምትገባ ታውቋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ የምታስተናግደው የቀጠናው ውድድር (ሴካፋ) በአስራ አንድ አባል ሀገራት እና አንድ ተጋባዥ ሀገር መካከል እንደሚደረግ ቀድሞ ሲነገር ቆይቷል። ይህ ቢሆንም በተጋባዥነት በውድድሩ ለመሳተፍዝርዝር

በግል ምክንያታቸው ከብሔራዊ ቡድኑ የተገለሉትን ሁለት እንዲሁም በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ የወጡትን ሦስት ተጫዋቾች ለመተካት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ አዲስ ጥሪ ለሦስት ተጫዋቾች አቅርበዋል። ከቀናት በኋላ በባህር ዳር ከተማ በሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን በካፍ የልዕቀት ማዕከል እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ እያደረገ ይገኛል። በትናንትናውዝርዝር

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ እየተዘጋጀ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ አድርጓል። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን ከሳምንት በፊት 28 ተጫዋቾችን በመያዝ አያት በሚገኘው የካፍ የልህቀት ማዕከል ሲዘጋጅ መቆየቱ ይታወቃል። በዛሬው ዕለትም የመጨረሻዎቹን ተጫዋቾችን ለመለየት በአዲስ አበባ ስታዲየም ረፋድ ላይ ከኢትዮዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያዋቀረው የሎካል ኦርጋናይዚንግ ኮሚቴ ውድድሩ የሚደረግበትን ከተማ ለሁለት ቀን ተመልክቶ መመለሱ ተገልጿል። ከ1926 ጀምሮ መደረግ የጀመረው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር የ2021 የውድድር ዓመት ፍልሚያው በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እንደሚከናወን ይታወቃል። ከሰኔ 26 – ሐምሌ 12 ድረስ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚከናወነው ውድድር ከመጀመሩ አስቀድሞም የኢትዮጵያዝርዝር

ከአስራ ስድስት ቀናት በኋላ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ የምትሳተፈው ብሩንዲ ለተጫዋቾቿ ጥሪ ማቅረቧ ተገልጿል። በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለሁለት ሳምንታት የሚካሄደው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ ጀምረዋል። ከሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች ቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርቦ ዝግጅቱንዝርዝር

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የሴካፋ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆነው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ ማቅረቡ ተገልጿል። ከሰኔ 28 – ሐምሌ 12 ድረስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር በ12 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል እንደሚደረግ ይታወቃል (አዲስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ)። በውድድሩ የሚሳተፉት ብሔራዊ ቡድኖችም የቀጠናው ፍልሚያ ከመጀመሩ ከሦስት ሳምንታትዝርዝር

በሰኔ ወር መጨረሻ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከሳምንታት በኃላ በሚካሄደው የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካፍ የልህቀት ማዕከል ማረፍያውን በማድረግ ከቅዳሜ ጀምሮ በዛው ሜዳ ልምምዱን እየከወነ ይገኛል። በዛሬው ዕለት 28 ተጫዋቾችን በመያዝ ከአስር ሰዓት ጀምሮ ልምምዱን ሲሰራ የተመለከትነው ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻዝርዝር