ሴካፋ (Page 20)

  የሴካፋ ዋንጫ በቀጣዩ ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይጀመራል፡፡ በርካታ ተጫዋቾችን ከምስራቅ አፍሪካ የሚያመጡት ክለቦቻችንም በሃገራችን ከሚስተናገደው ውድድር ተጫዋች ለመመልመል ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥርላቸዋል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ክለቦቻችን በትክረት ሊመለከቷቸው የሚገቡ ተጫዋቾችን በተከታታይ ታቀርብልዎታለች፡፡ በዛሬው ፅሁፋችን ሳምንቱን በድንቅ አቋም ያሳለፈው የዩጋንዳው የመስመር አጥቂ ፋሩክ ሚያን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡   በሃምሌ ወር 2006ዝርዝር

– የምድብ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ፣ ባህርዳር እና ሐዋሳ ስታዲየሞች ይደረጋሉ   ከህዳር 11 እስከ 26 ድረስ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚደረገው የ2015ቱ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዛሬ ናይሮቢ በሚገኘው የሴካፋ ዋና መስሪያ ቤት ወጥቷል። ውድድሩ በ11 የሴካፋ አባል ሃገራት መሀል የሚደረግ ሲሆን የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በተጋባዥነት ይሳተፋል። በተለያዩ የሚድያዝርዝር

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2015 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሃገራት ውድድር የሚሳተፉ ሃገራት 10 መድረሳቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ውድድሩን አስመልክቶ ከ2 ሳምንታት በፊት በኢሊሊ ሆቴል በተሰጠው መግለጫ ላይ በሴካፋ ውድድር እንደሚካፈሉ የተረጋገጡት ቡድኖች ብዛት 5 ብቻ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው 10 ሃገራት በውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ ከሴካፋ ማረጋገጫ ተልኳል፡፡ዝርዝር

ታንዛኒያ በምታዘጋጀው የሴካፋ ክለቦች ካጋሜ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ አዳማ ከነማ እንደሚሳተፍ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና በሁለተኛ ደረጃነት የጨረሰው ደደቢት በውድድሩ ላይ መሳተፍ ስላልፈለጉ ዕድሉ በሊጉ በሶስተኛ ደረጃነት ለጨረሰው አዳማ ከነማ ተሰጥቷል፡፡ አዳማ ከነማ በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመራ ስኬታማ የውድድር ዘመን አሳልፏል፡፡ በሜዳውዝርዝር