Soccer Ethiopia

ምስራቅ አፍሪካ

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሴካፋ ዋንጫ ይሳተፉ ይሆን?

በዩጋንዳ አዘጋጅነት በሚካሄደው ሴካፋ ዋንጫ ላይ በአንድ ምድብ የተደለደሉት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የመካፈላቸው ጉዳይ ቁርጡ አለየለትም። ለውትሮው እንከን የማያጣው የሴካፋ ሀገራት ዋንጫ ባሳለፍነው እሁች በታንዛኒያ ዳሬሰላም በሦስት ምድብ የተከፈለ ድልድል ይፋ በማድረግ ከሳምንት በኃላ ውድድሩን ለመጀመር መታቀዱ ይታወቃል። ከዩጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ከኤርትራ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ጥረት እያደረገች ይገኛል። በተለይ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ […]

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በኬንያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

በታንዛንያ አስተናጋጅነት ሲደረግ የቆየው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ዛሬ ሲጠናቀቅ ኬንያ አዘጋጇ ታንዛንያን በማሸነፍ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ከፍፃሜው አስቀድሞ 7:30 ላይ ዩጋንዳን ከቡሩንዲ ያገናኘውን የደረጃ ጨዋታ ዩጋንዳ 2ለ0 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ ቀጥሎ ለዋንጫ 10:30 ላይ አዘጋጇ ታንዛኒያን የገጠመችው ኬንያ 2-0 አሸንፋለች። ኢትዮጵያውያኑ ወጋየው ዘውዴ (በረዳት ዳኝነት) እና አስናቀች ገብሬ (በአራተኛ ዳኝነት) […]

የሴካፋ ምድብ ድልድል ኢትዮጵያ እና ኤርትራን አገናኝቷል

አስራ ሁለት ሀገራትን በሦስት ምድቦች ከፍሎ የሚደረገው የሴካፋ ወንድ ብሔራዊ ቡድኖች ዋንጫ እና ለመጀመርያ ጊዜ የሚከናወነው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ በታንዛንያ ተከናውኗል። በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከኅዳር 27 እስከ ታኅሳስ 9 ድረስ የሚደረገው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር ላይ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን ተሳታፊ በሚያደርግ ሲሆን በዚህ ሻምፒዮና ዲሞክራቲክ […]

ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ | ታንዛንያ እና ኬንያ ለፍፃሜ አልፈዋል

በሁለት ምድብ ተከፍሎ ባለፉት ዘጠኝ ቀናት በታንዛኒያዋ ዋና ከተማ ዳሬሰላም ሲደረግ የነበረው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ዛሬ በተደረጉ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተደርገው ለፍፃሜ ያለፉ ሀገራትን ለይቷል፡፡ ቀን 8:00 ከምድብ አንድ የበላይ የሆነችው ኬንያን ከምድብ ሁለት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀችው ብሩንዲን አገናኝቶ በኬኒያ 5ለ0 የበላይነት ተደምድሟል፡፡ ጀንትሪክ ሺካንጉዋ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ዶክራስ ሺኮቤ፣ ማዋሀሊማ አዳም እና […]

የሴካፋ ዋንጫ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይጀምራል

የሴካፋ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን እና ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከሁለት ሳምንት በኋላ መካሄድ ይጀምራል። በተለያዩ ጊዜያት ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች በመጥፋታቸው ምክንያት እየተቆራረጠ ለመደረግ የተገደደው የሴካፋ የወንዶች ሻምፒዮና ውድድር ከዘንድሮ ከኅዳር 27 – ታኅሳስ 9 በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚደረግ በታንዛኒያ እየተደረገ ባለው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ላይ ለጋዜጠኞች በተሰጠ መግለጫ ተጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ ለመጀመርያ ጊዜ የሚከናወነው የሴቶች […]

ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ | የምድብ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ የመጨረሻ ጨዋታዋን አሸንፋለች

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተደረገ ያለው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ ኢትዮጵያ ጅቡቲን 8-0፤ ኬኒያ ዩጋንዳን 3-0 አሸንፈዋል። በታንዛኒያዋ ዋና ከተማ ዳሬ ሠላም ባለፉት ቀናት በስምንት ሀገራት መካከል ሲደረግ የነበረው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የየምድቦቹ የመጨረሻ ጨዋታ ትላንት እና ዛሬ የተደረጉ ሲሆን ከምድብ አንድ ኬኒያ እና ዩጋንዳ፤ ከምድብ ሁለት ደግሞ ታንዛኒያ እና ቡሩንዲ ወደ ግማሽ […]

ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ | ኢትዮጵያ ከምድብ መውደቋን ስታረጋግጥ ዩጋንዳ እና ኬንያ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል

በታንዛኒያ ዳሬ ሠላም እየተደረገ ባለው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ከምድብ አንድ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ ኢትዮጵያ በኡጋንዳ 1ለ0 ተረታ ከምድቡ መውደቋን አረጋግጣለች። ኬንያ ደርዘን ግብ ጅቡቲ ላይ አስቆጥራ በማሸነፍ ከዩጋንዳ ጋር ወደ ግማሽ ፍፃሜው መግባቷንም አረጋግጣለች፡፡ 8:00 ላይ በጀመረው የኬንያ እና የጅቡቲ ጨዋታ ኬኒያ 12ለ0 ረምርማለች፡፡ አራት ፍፁም ቅጣት ምቶች በተሰጡበት በዚህ ጨዋታ ማዋሊማ ጄርካ እና […]

ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ | ከምድብ ሁለት ታንዛኒያ ማለፏን ስታረጋግጥ ደቡብ ሱዳን ድል ቀንቷታል

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የምድብ ሁለት መርሀግብሮች ዛሬ ሲከወኑ አስተናጋጇ ታንዛኒያ ቡሩንዲን 4ለ0 በማሸነፍ ማለፏን ስታረጋግጥ ደቡብ ሱዳን የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ድል አስመዝግባለች፡፡ 8:00 ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ዳኞች ፀሀይነሽ አበበ በዋና ዳኝነት፣ ወጋየው ዘውዴ እና ወይንሸት አበራ ደግሞ በረዳት ዳኝነት በመሩት የደቡብ ሱዳን እና ዛንዚባር ጨዋታ ደቡብ ሱዳን 5ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያውን የኢንተርናሽናል ነጥቧን አስመዝባለች፡፡ በመክፈቻው ሽንፈት ገጥሟት የነበረችው […]

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ከተጀመረ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል

በርካታ ግቦችን እያስተናገደ የሚገኘው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል። ትላንት ኢትዮጵያ በኬኒያ 2-0 ስትሸነፍ ዩጋንዳም ከደርዘን በላይ ግብ አስቆጥራ ጅቡቲን ረታለች፡፡ ስምንት ሀገራትን በሁለት ምድብ ከፍሎ እያሳተፈ የሚገኘው ይህ ውድድር ከትላንት በስቲያ ከምድብ ሁለት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሲጀመር ቡሩንዲ ዛንዚባርን 5-0፤ በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ታንዛኒያ ደቡብ ሱዳንን 9-0 መርታት ችለዋል። ምድቡን ከቡሩንዲ […]

ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ | ሉሲዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ትላንት የተጀመረ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሉሲዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ የምድብ አንድ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ትላንት መከናወን ሲጀመሩ 8:00 ላይ በመክፈቻው መርሀግብር በሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ዋና ዳኛ ፀሀይ እና ረዳቷ ወይንሸት አበራ የተመራው የቡሩንዲ እና ዛንዚባር ጨዋታ በቡሩንዲ 5-0 አሸናፊነት ተደምድሟል። 10:00 ላይ ደግሞ በሁለተኛው ጨዋታ አስተናጋጇ ታንዛኒያ ደቡብ ሱዳንን 9-0 […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top