Soccer Ethiopia

የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ

የአፍሪካ እና የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን ታወቀ

በኮቪድ-19 ምክንያት የተራዘሙት የአፍሪካ ዋንጫ እና የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን ዛሬ ታውቋል። ወደ 2022 የተሸጋገረው የ2021 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረጉበትን ቀን ካፍ አሳውቋል። በዚህም መሠረት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 8 ቀን 2013 ባሉት ቀናት የየምድቡ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በምድብ 11 የምትገኘው ኢትዮጵያም በተጠቀሱት ቀናት ከኒጀር ከሜዳዋ ውጪ እና በሜዳዋ […]

“የካዛብላንካው ድራማዊ ምሽት” ትውስታ በደሳለኝ ገብረጊዮርጊስ አንደበት

በቀደመ ዘመን ከሀገር ወጥቶ መጥፋት በተለመደበት የኢትዮጵያ እግርኳስ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ሞሮኮ ተጉዞ ድራማዊ ክስተት ስላስተናገደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ስለጠፉት ተጫዋቾች እንዲሁም በተጫዋቾች እጥረት ምክንያት አሰልጣኙ አጥቂ፣ ግብጠባቂው ደግሞ አማካይ ሆነው ስለተጫወቱበት አስገራሚ ክስተት በትውስታ አምዳችን ይዘን ቀርበናል። ወቅቱ 1985፤ ውድድሩ ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስ በሚስተናገደው 15ኛው የ1994 ዓለም ዋንጫ የሚያልፉ ሦስት […]

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ስለ ቀጣይ የማጣርያ ጨዋታዎች ይናገራሉ

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በቅርቡ ሽግሽጎች በተደረጉበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እና የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድልን አስመልክቶ በፌደሬሽኑ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል። በመጪው የፈረንጆቹ ሴፕቴምበር ይካሄዳል ተብሎ አስቀድሞ መርሐግብር ተይዞለት የነበረውን የኒጀሩ የደርሶ መልስ ጨዋታ ወደ መጋቢት መጠጋቱን አስመልክቶ ተካታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። “አስቀድሞ ወጥቶ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ መርሃግብር በመቀየሩ […]

2022 ዓለም ዋንጫ| የኢትዮጵያ የምድብ ማጣርያ ተጋጣሚዎች ተለይተዋል

ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ድልድል የተደረገ ዛሬ ይፋ ሲሆን ዋልያዎቹ በምድብ ‘ G’ ተደልድለዋል። የማጣርያው ምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት በካይሮ ናይል ሪትዝ ሆቴል ይፋ የሆነ ሲሆን ማጣርያውም በርካታ ተጠባቂ ጨዋታዎች አካቷል። በቅድመ ማጣርያው ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚል ህግ ወደ ምድብ ድልድሉ የገባችው ኢትዮጵያም በምድብ ‘G’ ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ተደልድላለች። ቀድሞ በወጣው […]

ኳታር 2022 | ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ድልድል የሚገኙበት ቋት ተለየ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን በመጪው ጥር በግብፅ ካይሮ ከሚካሄደው የ2022 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ድልድል አስቀድሞ አራት ቋቶችን ይፋ አድርጓል። ዋሊያዎቹም በ4ኛው ቋት ላይ ተመድበዋል። በ10 ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄደው የአፍሪካ ዞን ማጣርያ 40 ሀገራትን የሚያሳትፍ ሲሆን ወቅታዊ የዐለም ሀገራት ደረጃን መሠረት በማድረግ ቡድኖቹን በአራት ቋት መድቧል። 146ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት […]

“ቡድኑ በወጣቶች እየተገነባ መሆኑና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ማሳየቱ በግሌ ደስተኛ ያደርገኛል” አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ቡድኑ በዓለም ዋንጫ እና ቻን ማጣርያ ስለነበረው ጉዞ ከሰጡት መግለጫ በማስከትል በስፍራው ከታደሙ የመገናኛ ብዙሃን አካላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ከተነሱት ጥያቄዎች መካከልም አንኳር አንኳሮቹን በሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡ በሌሶቶ ጨዋታ ወቅት ስለተፈጠረው የጉዞ መስተጓጓልና ተያያዥ ጉዳች “ከዚህ ቀደም የብሔራዊ ቡድኑን አደረጃጀት ዘመናዊ ለማድረግ ቃል መግባታችን የሚታወስ ነው፤ የሁሉም ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች […]

“በገባነው ቃል መሠረት ወደ ቻን ማለፍ ባለመቻላችን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አስቻለው ታመነ

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሴሽነረ ፅህፈት ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ እና የቡድኑ አምበል አስቻለው ታመነ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ እና ቻን ማጣርያ ስለነበራቸው ጉዞ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ የቡድኑ አምበል የሆነው አስቻለው ታመነ ተከታዮቹን ሀሳቦች አጋርቷል። “የሌሶቶው ጨዋታ የቡድኑ መንፈስ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ያሳየ ጨዋታ ነበር፤ ጨዋታውን ለማሸነፍ የነበረው የቡድኑ ፍላጎትና የተነሳሽነት […]

ፌደሬሽኑ ይቅርታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋልያዎቹ ለደረሰባቸው እንግልት ይቅርታ በመጠየቅ ብሄራዊ ቡድኑ ወደ ምድብ ድልድል በመግባቱም ሽልማት አበርክቷል። ዋልያዎቹ ሌሶቶን ከሜዳ ውጭ ጎል ህግ አሸንፈው ወደ ምድብ ማጣርያ መግባታቸውን ካረጋገጡ በኃላ በተፈጠሩ የአሰራር ክፍተቶች ብሔራዊ ቡድኑ ባልተመቻቸ ሁኔታ እዛው ለመቆየት እንደተገደደ ይታወቃል። ትላንትም እግር ኳስ ፌደሬሽኑ ለተፈጠሩት ነገሮች ይቅርታ ጠይቆ ጥፋተኛ ባላቸው ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ […]

ዋሊያዎቹ በመጨረሻም ኢትዮጵያ ገብተዋል

ላለፉት ቀናት በሌሶቶ ጥሩ ያልሆነ ቆይታ የነበራቸው ዋሊያዎቹ ከደቂቃዎች በፊት በሠላም አዲስ አበባ ገብተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ለኳታር የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ሌሶቶን ለመግጠም ወደ ማሴሩ አምርተው እሁድ ዕለት ጨዋታውን ካካሄዱ በኋላ በተፈጠሩ የአሰራር ክፍተቶች በሀገሪቱ ለመቆየት ተገደው የብዙዎች መነጋገርያ ሆነው የነበሩት ዋሊያዎቹ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቦሌ አየር ማረፍያ ደርሰዋል። ከጨዋታው በኋላ ከትኬት ጋር በተያያዘ […]

ሪፖርት | ኢትዮጵያ ወደ ምድብ ማጣርያ አልፋለች

በ2022 የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ላይ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በባህር ዳር ሌሶቶን አስተናግዳ 0-0 በሆነ ውጤት መፈፀሟ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ማሴሮ ላይ በመልሱ ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት በመለያየቷ ከሜዳ ውጪ ጎል ህግ መሠረት ወደ ምድብ ማጣርያው መግባቷን አረጋግጣለች፡፡ ከባህርዳሩ ጨዋታ የሦስት ተጫዋቾችን ቅያሪ በማድረግ ወደ ሜዳ የገቡት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ረመዳን ናስር፣ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top