አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን የሾመው ለገጣፎ ለገዳዲ በቋሚ እና በውሰት ውል ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ለገጣፎ ለገዳዲ በ13 ጨዋታዎች ባስመዘገበው አንድ ድል እና ሦስት የአቻ ውጤት ስድስት ነጥብ ይዞ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል። ሊጉ ለብሔራዊ ቡድን የቻን ውድድር በሚቋረጥበት ጊዜም ክለቡ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስንRead More →

ያጋሩ

የአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እና ሀዲያ ሆሳዕናን አለመስማማት ተከትሎ የቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስተላልፏል። ሀዲያ ሆሳዕና በተጠናቀቀው የ2014 የውድድር ዓመት በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እየተመራ እንደነበር አይዘነጋም። የውድድር ዓመቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ግን አሠልጣኙ እና ክለቡ ከውል ስምምነት ማቋረጥ ጋር በተያያዘ አለመስማማት ውስጥ የነበሩ ሲሆን ጉዳያቸውም ወደ ሀገሪቱ የእግርኳስ የበላይRead More →

ያጋሩ

ከቀናት በፊት አዲስ አሠልጣኝ የሾመው ፋሲል ከነማ በዛሬው ዕለት የመስመር ተጫዋች የግሉ አድርጓል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፉት ፋሲል ከነማዎች ከኃይሉ ነጋሽ ጋር ከተለያዩ በኋላ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝ እያሱ መርሀፅድቅን በረዳት አሰልጣኝነት በመቅጠር በቀጣይ ከአዳማ ጀምሮ ለሚደረገው የሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች ማረፊያቸውን አዲስ አበባ ሆሊዴይ ሆቴል በማድረግ ዝግጅታቸውን የቀጠሉRead More →

ያጋሩ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የቡድኑ አካል አድርጓል። በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተወዳዳሪ የሆነው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀናት በፊት አብዱርሀማን ሙባረክን ማስፈረሙ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከሀገር ውስጥ እና ከኤርትራ ወደ ስብስቡ ስለ መቀላቀሉ በተለይ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል። ከሀገር ውስጥ አማረRead More →

ያጋሩ

ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ የነበረው አህመድ ሁሴን በዛሬው ዕለት በአዞዎቹ ቤት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ከስድስት ወራትን ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ ከቀናቶች በፊት አጥቂው አህመድ ሁሴንን በሁለት ዓመት ውል ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር ድርድር በማድረግ ከስምምነት ደርሰውRead More →

ያጋሩ

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው ተከላካይ አሳዳጊ ክለቡን ዳግም ተቀላቅሏል። በአሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው አርባምንጭ ከተማ 13 ነጥቦችን በማግኘት በሰበሰበው ቁጥር ልክ 13ኛ ደረጃን በፕሪምየር ሊጉ ይዞ መቀመጡ ይታወቃል። የሚታወቅበትን ጠጣር የመከላከል አደረጃጀት ዘንድሮ ለማስመልከት እየተቸገረ የሚገኘው ቡድኑ በአራት እና አምስት የተከላካይ ክፍል መዋቅር ሲጫወት የሰነበተ ሲሆን አሁን ደግሞ በተከላካይRead More →

ያጋሩ

ሀዋሳ ከተማ በኢትዮ ኤሌክትሪክ በተሸነፈበት ጨዋታ ያልተገባ ባህሪን ያሳየችው አጥቂዋ ቱሪስት ለማ ላይ የቅጣት ውሳኔዎች ተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በሀዋሳ ከተማ እየተደረገ የአንደኛ ዙር መርሀግብር ሊጠናቀቅ የመጨረሻ ሳምንቱ ላይ ደርሷል። የ12ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ከአንድ ቀን በፊት ተከናውነው የተጠናቀቁ ሲሆን ተጠባቂ በነበረው የሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ላይRead More →

ያጋሩ

የመስመር አጥቂው አብዱራህማን ሙባረክ የኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ፈራሚ ሆኗል። በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዳግም ከታችኛው የሊግ ዕርከን በማደግ እየተወዳደረ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማን ከረዳት አሰልጣኝነት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ቦታ ላይ ከሾመ በኋላ ለቀጣዮቹ ቀሪ አስራ ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ በትናንትናው ዕለት ዝግጅት የጀመረRead More →

ያጋሩ

አሸናፊ በቀለ አዲሱ የዐፄዎቹ አሰልጣኝ ሲሆኑ ረዳት አሰልጣኛቸውንም ይፋ አድርገዋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ላይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብቅ ብለው ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን ከቻሉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ፋሲል ከነማ በዘንድሮው የሊግ ውድድር ላይ ቡድኑ ባደረጋቸው 13 ጨዋታዎች ላይ ካስመዘገበው ደካማ አቋም የተነሳ አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽን ከኃላፊነት በማሰናበት በይፋ እስከRead More →

ያጋሩ

በሊጉ ደካማ የውድድር ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዲስ ሥራ አስኪያጅ ሾሟል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዳግም የመሳተፍ ዕድልን ያገኘው እና በውጤት ቀውስ ውስጥ ከደረጃ ግርጌው ፈቀቅ ብሎ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሰሞኑ ጊዜያዊ አሰልጣኞቹ ገዛኸኝ ከተማ እና ስምዖን አባይን በዋና እና ረዳት የአሰልጣኝነት ሚና መሾሙ ይታወሳል። አሀን ደግሞ ክለቡ አዳዲስRead More →

ያጋሩ