ሀዲያ ሆሳዕና

የመስመር እና የፊት አጥቂው ሀብታሙ ታደሠ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቷል፡፡ በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት መሪነት እስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሀድያ ሆሳዕና ሀብታሙ ታደሠን አምስተኛ ፈራሚውን አድርጓል። በወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊጉ ሲጫወት ባሳየው መልካም እንቅስቃሴ መነሻነት በ2012 ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ የተጫወተው ሀብታሙ ሁለት ጥሩ የውድድር ዘመናትን በቡና ካሳለፈ በኋላዝርዝር

በሀዲያ ሆሳዕና እና በተጫዋቾቹ ውዝግብ ዙርያ ፌዴሬሽኑ ያስተላለፈውን ውሳኔ ክለቡ በመቃወም ቅሬታውን አሰምቷል። ለወራት በዘለቀው የክለቡ እና አስራ አምስት ተጫዋቾች ውዝግብ ላይ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ በመስጠት ሆሳዕና ተጫዋቾቹ ላይ የወሰነውን የሁለት ዓመት ዕግድ በመሻር በውላቸው መሠረት ክፍያቸውን እንዲፈፅም መወሰኑ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ክለቡ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ማስገባቱ ታውቋል። ክለቡ ዛሬ ባስገባው አራትዝርዝር

በአስራ አምስቱ ተጫዋቾች እና በሀድያ ሆሳዕና ክለብ መካከል የተፈጠረውን ክርክር ሲመለከት የቆየው ፌዴሬሽኑ በዛሬው ዕለት ውሳኔ ሰጥቷል። የማትጊያ ገንዘብ ክለቡ በሰጠን ማረጋገጫ መሠረት ይክፈለን በማለት አስራ አምስት ተጫዋቾች ለወራት ያቀረቡት ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት ከልምምድም ሆነ ከጨዋታ ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ክለቡ በወሰደው የዲሲፕሊን እርምጃ ተጫዋቾቹን ለሁለት ዓመት ማገዱምዝርዝር

በሁለቱ አካላት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመዳኘት እየመረመረ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን በሽምግልና መያዙ ታውቋል። በሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ እና በአስራ አምስቱ ተጫዋቾች መካከል ለወራት የከረመ አለመግባባት ኋኃላ ላይ ከሁለቱም ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት በሚወጡ ውሳኔዎች ምክንያት እየተካረረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ ወደ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳመራ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ባሳለፍነውዝርዝር

የሁለተኛ ደረጃን ለመያዝ ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው የ25ኛ ሳምንት የመዝጊያ ጨዋታ እንደሚከተለው ቃኝተነዋል። ሁለቱ የሸገር ክለቦችን በተከታታይ ያስተናገዱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያገኙትን ድል በሌላኛው የመዲናችን ክለብ ለመድገም እና የሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁበትን ዕድል በራሳቸው ለመወሰን ጠንክረው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይገመታል። ሦስት ነጥብ ካገኙ አምስት የጨዋታ ሳምንታት ያለፋቸውዝርዝር

ሀዲያ ሆሳዕና በሄኖክ አርፊጮ ብቸኛ የፍፁም ቅጣት ግብ ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። ኢያሱ መርሐፅድቅ – ሀዲያ ሆሳዕና  ስለተከሉት ጥብቅ መከላከል  “ስለመራን ብቻ ሳይሆን ስንጀምርም ጀምሮ ተከላክለን ለማጥቃት ነበር ያሰብነው ከግቧ በኃላ ያንን ሂደት ነበር አጠናክረን የቀጠልነው።” በጨዋታው ከወጣት ተጫዋቾቹ የጠበቁትን ስለማግኘታቸው  “ባለፈውም እንዳልኩት ነውዝርዝር

ትልቅ ተጫዋች ለመሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ያደረበት የእግርኳስ ፍቅር በፕሮጀክት ጀምሮ ዛሬ የሀድያ ሆሳዕና ዋናው ቡድን እስከመጫወት አድርሶታል። ተስፈኛው አጥቂ ደስታ ዋሚሾ ተወልዶ ያደገው በሀድያ ከተማ ልዩ ስሟ ጊቤ ወረዳ በምትባል ሠፈር ነው። በእግርኳስ ፍቅር የተለከፈው ደስታ በአሰልጣኝ አብነት ስር በሠፈር በፕሮጀክት ታቅፎ እግርኳስን በእውቀት መሠልጠን ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ በ2011 በሀድያዝርዝር

ከከሰዓቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሠልጣኞች የድህረ ጨዋታ አስተያየታቸውን ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። አብርሃም መብራቱ – ሰበታ ከተማ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ አስቆጥረው ስለማሸነፋቸው? እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ከነበረብን የስነ-ልቦና ችግር አንፃር ዛሬ ያገኘነው ውጤት ቀጣይ ለምናደርጋቸው ጨዋታዎች እጅግ የሚያነሳሳን ነው። በአጠቃላይ እንደውም እኔ የዛሬውን ውጤት ወርቃማ ድል ብዬ ነው የምገልፀው። በጨዋታውዝርዝር

ከውድድር ዘመኑ ጅማሮ እስከ መጠናቀቂያው ድረስ እየተንከባለለ እዚህ የደረሰው የሀዲያ የተጫዋቾቹና የክለቡ ውዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን ? በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመራ አስደናቂ የውድድር ጉዞ በማድረግ አጀማመሩን አሳምሮ የነበረው ሀዲያ ሆሳዕና ከሜዳ ውጭ በሚፈጠሩ የተጫዋቾቹ ‘የፊርማ ገንዘብ ይከፈለን’ እና ክለቡ ‘ቆይ ታገሱን እንከፍላለን’ ውዝግብ 22 የጨዋታ ሳምንታትን በአሰልቺ ሁኔታ አልፈዋል። ከወራትዝርዝር

ያለግብ ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት ሀሳባቸውን አካፍለዋል። አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና ካሉሻ አልሀሰንን ቀይረው አስገብተው መልሰው ስለማስወጣታቸው ስም እና ብቃት ይለያያል ። ሜዳ ላይ ምንም ካልሰራልህ ፣ የተሰጠውን ስራ ካልሰራልህ ምንም ልታደርገው አትችልም። ለእኔ ትልቅ ተጫዋች ነው ፤ ግን ትልቅነቱን ሜዳ ላይ ሲያሳይ ነው። በዚህዝርዝር