Soccer Ethiopia

ሀዲያ ሆሳዕና

ሀዲያ ሆሳዕና አምስተኛ ተጫዋቹን አስፈረመ

የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሱሌይማን ሰሚድ አዳማን ለቆ ሀዲያ ሆሳዕናን የተቀላቀለ አምስተኛ ተጫዋች ሆኗል፡፡ በአንድ ዓመት ውል ነብሮቹን ለመቀላቀል የተስማማው የመሐል እና የመስመር ተከላካዩ ሱሌይማን ሰሚድ ከኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ የተገኘ ሲሆን በአዳማ ከተማ ላለፉት ሦስት ዓመታት መልካም ቆይታን ካደረገ በኋላ የቀድሞው አሰልጣኙን ፈለግ ተከትሎ ወደ ሆሳዕና አምርቷል፡፡ በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ መሪነት በዛሬው ዕለት አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን […]

ሀዲያ ሆሳዕና አራተኛ ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማምቷል

በዛሬው ዕለት የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቆ የነበረው ሀዲያ ሆሳዕና ኃይሌ እሸቱን አራተኛ ፈራሚ በማድረግ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ፣ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አጥቂ ባለፈው ክረምት ወላይታ ድቻን ለቆ በአዳማ ከተማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን እንደ አዲስ ህንፃ፣ በረከት ደስታ እና ቴዎድሮስ በቀለ ሁሉ የቀድሞ አሰልጣኙ ፈለግን በመከተል በአንድ ዓመት ውል ወደ ነብሮቹ አምርቷል። […]

“የዘመኑ ከዋክብት ገጽ” ከይሁን እንደሻው ጋር

የመተሐራው ፈርጥ፣ በዕይታውና የተሳኩ ኳሶችን ለአጥቂዎች በማቀበል የሚታወቀው የሀዲያ ሆሳዕናው አማካይ ይሁን እንደሻው የዛሬው የዘመኑ ከዋክብት ገጽ እንግዳችን ነው። የአልሸነፍ ባይ፣ ታታሪ እና ልባም ተጫዋች መሆኑ የእርሱ መገለጫዎቹ ናቸው። በተለይ ሳይታሰብ ዕይታውን ተጠቅሞ ወደፈለገው አቅጣጫ ለቡድን ጓደኞቹ የሚያቀበለው ኳስ አስገራሚ ነው። በ2007 ድሬዳዋ ከተማን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከማሳደጉ በተጨማሪ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋችም የመሆን ክብርን […]

የሀዲያ ሆሳዕና ተጫዋቾች የደመወዝ ቅሬታ እና የክለቡ ምላሽ

ከሁለት እስከ አምስት ወራት ድረስ ወርሀዊ የደመወዝ ክፍያን ሳይፈፅም የቆየው ሀዲያ ሆሳዕና እስከ ቀጣይ ሳምንት የደሞዝ ክፍያ እንደሚያጠናቅቅ አስታውቋል፡፡ በሀገራችን በኮሮና ስጋት የተነሳ ከሁለት ወራት በፊት ቀሪ የሊግ የእግር ኳስ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸውን ይታወሳል፡፡ ይሁንና ፌድሬሽኑ ውድድሮቹን ይሰርዛቸው እንጂ ክለቦች በገቡት ውል መሠረት ለተጫዋቾቻቸው ክፍያን በአግባቡ መፈፀም አለባቸው ቢልም በርከት ያሉ ክለቦች ግን ተፈፃሚ […]

ሀዲያ ሆሳዕና ስታዲየሙን ሊያድስ ነው

ቅሬታን ሲያስተናግድ የከረመው የሀዲያ ሆሳዕናው አቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታድየም ሙሉ በሙሉ የማሻሻያ ግንባታ ሊደረግበት ነው፡፡ በፕሪምየር ሊጉ በተደጋጋሚ በክለቦች ቅሬታ ከሚቀርብባቸው ሜዳዎች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ስታዲየም በተለይ አመቺ ያልሆነው የመጫወቻ ሳሩ በዋናነት ክለቦች አቤቱታ ሲያሰሙበት የነበረ ሲሆን ለተመልካቾች ምቹ መቀመጫ በበቂ ሁኔታ አለመገንባቱ የቅሬታ መነሻ ጉዳዮች እንደነበሩ በዚህ ዓመት በተደጋጋሚ ሲነሱ ተመልክተናል፡፡ በሊጉ ደካማ […]

ሀዲያ ሆሳዕና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

ሀዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ለኮሮና መከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ክለቡ በሀድያ ዞን አካባቢ ስርጭቱን ለመከላከል ለሚደረጉ ተግባራት ለተቋቋመው ግብረ ሀይል ከተጫዋቾች፣ ከአሰልጣኝ እና የስፖርቱ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች ጨምሮ ከደመወዛቸው 50% በድምሩ 445,366 (አራት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር) የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የቡድኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ለሶከር ኢትዮጵያ እርዳታው ቀጣይነት […]

ሀዲያ ሆሳዕና ይግባኝ ጠየቀ

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠንከር ያለ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣት የተጣለበት ሀዲያ ሆሳዕና ይግባኝ ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛው ሳምንት በሜዳው መቐለ 70 እንደርታን አስተናግዶ 1ለ0 ሽንፈት ገጥሞት የነበረው ሆሳዕና በወቅቱ በጨዋታው ላይ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ታይቷል በማለት በክለቡ ላይ በዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ቅጣት መጣሉ ይታወሳል፡፡ በቅጣቱ መሠረትም አምስት የሜዳውን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ እንዲጫወት እና […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 1-1 ሀድያ ሆሳዕና

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛው ሳምንት ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና አቻ ከተለያዩበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ክለብ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን እንዲህ ሰጥተውናል፡፡ “ተጫዋቾቹ ጋር የነበረው ችግር ምን እንደሆነ አላውቅም” የሀዋሳ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ብርሀኑ ወርቁ ስለጨዋታው “ጨዋታውን እንደጠበቅነው አይደለም ያገኘነው። እነሱም እኛም ተሸንፈን ነው የመጣነው። እኛ ሜዳችን ላይ የማሸነፍ አቅም ነበረን። ሆኖም ዛሬ ትንሽ ተቀዛቅዘን ነበር የገባነው። […]

ሪፖርት | ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርተዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛው ሳምንት ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና እጅግ ቀዝቃዛ በነበረው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል። ሀዋሳ ከተማዎች ባለፈው ሳምንት በድሬዳዋ ሽንፈት ካስተናገደው ቡድን ውስጥ በአራት ተጫዋች ላይ ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ሀብቴ ከድር በቢሊንጋ ኢኖህ ፣ ላውረንስ ላርቴን በወንድማገኝ ማዕረግ ፣ ተስፋዬ መላኩን በአክሊሉ ተፈራ ፣ ሄኖክ አየለን በብርሀኑ በቀለ ለውጠዋል፡፡ […]

ቅድመ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና

ከነገ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው የሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታን እንደሚከተለው ተመልክተነዋል። ሁለተኛውን ዙር በሽንፈት የጀመረው ሀዋሳ ከተማ ወደ ድል በመመለስ ደረጃውን ማሻሻልን አልሞ ወደ ሜዳ ይገባል። የሀዋሳ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ) ተሸነፈ አሸነፈ ተሸነፈ አሸነፈ ተሸነፈ ባሳለፍነው ሳምንት በጊዜያዊ አሰልጣኙ ብርሀኑ ወርቁ እየተመራ በድሬዳዋ ሽንፈት ያስተናገደው ቡድኑ ነገ በሜዳው በሚያደርገው […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top