የክለቦች የውድድር ዘመን ቅድመ ዳሰሳ | ለገጣፎ ለገዳዲ
ለገጣፎ ለገዳዲ የታሪኩን የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ለማድረግ ከወትሮው የአዲስ አዳጊዎች መንገድ የተለየ አቅጣጫን መርጧል። ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ ዕርከን ለማደግ ከፍ ያለ ፉክክር በሚደረግበት የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከ2009 ጀምሮ ሲፋለም የቆየው ለገጣፎ ለገዳዲ በተለይም በ2011 እና በኮቪድ ምክንያት በተቋረጠው ቀጣዩ የውድድር ዓመት ሊጉን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ ሳይሳካለት ቀርቶ ነበር።Read More →