የፋሲል ከነማ ክለብ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት መፈፀሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2013 ሻምፒዮን የሆነው ፋሲል ከነማ ራሱን ለማጠናከር ብሎም ለክለቡ የሚሆኑ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሮችን በተለያዩ ቀናት እያደረገ ይገኛል፡፡ ቡድኑ በተሻለ ጠንካራ ሆኖ ለመቅረብ ከሚያደርገው የገቢ ማሰባሰብ ባሻገር በተሻለ የትጥቅ እናContinue Reading

የዘንድሮ የውድድር ዘመን ኮከብ አሠልጣኝ ተብለው የተመረጡት አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ የተሰማቸውን ስሜት አጋርተዋል። የፋሲል ከነማው ዋና አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ቡድናቸውን ሻምፒዮን በማድረጋቸውም ከአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የዋንጫ እና 2 መቶ ሺ ብር ሽልማት ተቀብለዋል። አሠልጣኙም ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ተከታዩን አጭር ሀሳብ ሲናገሩ ተደምጧል። ” በቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሠግናለሁ። ይሄንንም ከፍተኛ ክብር በቅርቡContinue Reading

የ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን የሆነው ፋሲል ከነማ የገንዘብ አቅሙን ለማሳደግ በሸራተን አዲስ ሆቴል ያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ምሽቱን ተካሂዷል። “ስፖርት ለኢትዮጵያ ኅብረት” በሚል መሪ ቃል አመሻሽ ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ባለሀብቶች፣ የእግርኳሱ የበላይ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸውContinue Reading

ዐፄዎሉ በታሪክ የመጀመርያ የሊግ ዋንጫቸውን ባነሱበት ዕለት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ስለተፈጠረው ጉዳይ አምሳሉ ጥላሁን አስተያየቱን ሰጥቷል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመጠናቀቁ ከአንድ ጨዋታ አስቀድሞ ዛሬ የዋንጫ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት በፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ ላይ ሲከናወን በአቻ ውጤት ተለያይተው ዐፄዎቹ የድል ዋንጫቸውን ከፍ አድርገው ማንሳታቸው ይታወቃል። በዕለቱ ጨዋታ መጠናቀቂያ ላይContinue Reading

የረፋዱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት የሰጡት አስተያየት ይህንን ይመስላል። አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ – ፋሲል ከነማ ስለቻምዮንነት ስሜት ፋሲል ከነማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይህን ዋንጫ ሲያገኝ። የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ጨዋታዎች በ ዲ ኤስ ቲቪ መታየት ሲጀምሩ መሆኑ ነው። በዚህ ዘመን የመጀመሪያውን ዋንጫ በማግኘቴ እጅግ ነው ደስ ያለኝ። እንዴትContinue Reading

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናቸዋል። የግላቸው ያደረጉትን ዋንጫ በዛሬው ዕለት የሚረከቡት ፋሲል ከነማ ከ19 ጨዋታዎች በኋላ ከተሸነፉበት የድሬዳዋው ፍልሚያ ስምንት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ስዩም ከበደ ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ ሳሙኤል ዮሐንስ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሰዒድ ሀሰን፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ሽመክት ጉግሳ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ፍቃዱ ዓለሙን በማሳረፍ ሳማኬ ሚኬል፣ ሄኖክ ይትባረክ፣Continue Reading

ፋሲል ከነማ ቀድሞ የግሉ መሆኑን ያረጋገጠውን ዋንጫ የሚረከብበትን የነገ ረፋድ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ፋሲል ከነማ በመጨረሻ ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ ከደረሰበትን ሽንፈት ለማገገም፣ አሁንም በጥንካሬው ላይ እንደሚገኝ ለማሳየት እና የዋንጫ ርክክብ መርሐ-ግብሩን በድል ለማሳጀብ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይታሰባል። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉት ሀዋሳContinue Reading

የ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ ፋሲል ከነማ በሁለት ሺህ ደጋፊዎች ፊት ዋንጫውን ከፍ እንደሚያደርግ ታውቋል። የዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ያለ ደጋፊዎች ሲደረግ ቆይቷል። እርግጥ በውድድሩ መሐል የየክለቦቹ 10 ደጋፊዎች ወደ ሜዳ እንዲገቡ ተፈቅዶ የነበረ ቢሆንም ከቫይረሱ ስርጭት አንፃር ክልከላው ዳግም ተጥሎ ሊጉ ያለContinue Reading

“ስፖርት ለኢትዮጵያ ሕብረት” በሚል መሪ ቃል ፋሲል ከነማ ባዘጋጃቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። ረፋድ በሸራተን አዲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተሰጠው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ፣ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ስዩም ከበደ እና አንደኛው አምበል ያሬድ ባዬ እንዲሁም አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴውContinue Reading

የፋሲል ከነማው አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ከቀናት በፊት የወልቂጤ እግርኳስ ክለብ ቡድናቸውን “ከአቅም በታች ተጫውቷል” በሚል ስለከሰሰበት ጉዳይ ሀሳብ ሰጥተዋል። የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ ፋሲል ከነማ በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሮች ጋር በተያያዘ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተነሱ ሙሉ ሀሳቦችን ከቆይታ በኋላContinue Reading