ጅማ አባ ጅፋር (Page 2)

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዳዊት እስጢፋኖስ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል፡፡ በተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በንቃት ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር ዳዊትን እስጢፋኖስን አስፈረመ፡፡ የቀድሞው የባንክ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኤሌክትሪክ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ለሁለተኛ ጊዜ የተቀላቀለው መከላከያን ከለቀቀ በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሰበታ ከተማ አሳልፏል፡፡ ከሰበታ ጋር ውሉንዝርዝር

በቅርቡ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ጅማ አባጅፋሮች በትናንትናው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ተጫዋቾች ሲያስፈርሙ የነባር ተጫዋቾችንም ውል አድሰዋል። በትናንትናው ዕለት አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ጅማ አባጅፋር የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ከጋሻው ፕሮጀክት የተገኘው የመስመር ተከላካዩ ኢዳላሚን ናስር እና ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ቡድኑንዝርዝር

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ከገባ በኃላ ሦስት አዳዲስ ፈራሚዎችን በእጁ ያስገባው ጅማ አባጅፋር የመስመር አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ የመስመር ተጫዋቹ እዮብ ዓለማየሁ በሁለት ዓመት ውል ጅማን የተቀላቀለው ተጫዋች ሆኗል። በወላይታ ድቻ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ቡድን ውስጥ አንፀባራቂ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን በማድረጉ በ2008 ወደ ዋናው ካደገ በኋላ ጥሩ ጊዜያትንዝርዝር

በፕሪምየር ሊጉ መክረሙን ያረጋገጠው ጅማ አባጅፋር ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አሠልጣኝ አግኝቷል። ከአሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን የጨረሰው ጅማ አባጅፋር አዲስ አሠልጣኝ ለመቅጠር ከሰሞኑን ሽር ጉድ ሲል ነበር። ክለቡ ከበርካታ አሠልጣኞች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረ ቢሆንም ከደቂቃዎች በፊት አሸናፊ በቀለን ዋና አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የቀድሞ የኢትዮጵያዝርዝር

በአዳማ ከተማ አንድ ለምንም አሸናፊነት ከተጠናቀቀው የማሟያ ውድድሩ ጨዋታ በኋካ አሠልጣኞች የድህረ-ጨዋታ አስተያየታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል። ዘርዓይ ሙሉ – አዳማ ከተማ በውድድሩ የተሳተፋችሁበትን ዓላማ አሳክታችኋል። ምን ተሰማህ? በቅድሚያ ለረዳን አምላካችን ምስጋና እናቀርባለን። የዚህ ውድድር ዕድል ሲመጣ ከአመራሮቹ ጋር የተነጋገርኩት ክለቡን በአንደኝነት እንደማሳልፈው ነው። የተነጋገርኩትን እና የተናገርኩትን በማሳካቴ ደግሞ በጣም ደስዝርዝር

አንደኛውን የማሟያ ውድድሩ አላፊ ክለብ ለመለየት የተደረገው የአዳማ እና የጅማ ጨዋታ በአዳማ ከተማ አንድ ለምንም አሸናፊነት ተጠናቋል። ኮልፌ ቀራኒዮን ረትቶ ለዛሬው ወሳኝ ጨዋታ የተዘጋጀው ጅማ አባጅፋር ድል ከተቀዳጀበት ጨዋታ አንድ ለውጥ ብቻ አድርጓል። በዚህም ዋውንጎ ፕሪንስ ወጥቶ ሱራፌል ዐወል ወደ ሜዳ ገብቷል። አዳማ ከተማ በበኩሉ ቀዳሚ አላፊ ቡድን መሆኑን ካረጋገጠበግዝርዝር

አንደኛውን የማሟያ ውድድር አላፊ ክለብ የሚለየውን ጨዋታ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎች እንዲህ አጠናክረናል። በአሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሚመራው ጅማ አባጅፋር ጥሩ ሆኖ ካየበት እና ሦስት ነጥብ ካገኘበት የኮልፌ ጨዋታ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገዋል። በዚህም ዋውንጎ ፕሪንስ ወጥቶ ሱራፌል ዐወል ወደ ሜዳ ገብቷል። በተቃራኒው በአራተኛ ዙር ጨዋታ የማሟያ ውድድሩ ቀዳሚ አላፊ ቡድን መሆኑንዝርዝር

አምስት ግቦች ከተስተናገዱበት ጨዋታ በኋላ ሱፐር ስፖርት ከአሠልጣኞች አስተያየት ተቀብሏል። ገብረመድኅን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና ስለ ጨዋታው? በጨዋታው ብልጫ እንደሚኖረን አስቤ ነበር። በዚህ ጨዋታ ሁሉንም ነገር ማጠናቀቅ ነበረብን። ጎልም ያስፈልገን ነበር። ሲዳማ ያለፉትን አስር ጨዋተዎች ጥሩ አመጣት ነው የመጣው። ዛሬ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ብቻ ሳይሆን ቡድኑ ምን እንደሚመስልም ማሳየት ነበርዝርዝር

ሦስተኛውን ወራጅ ቡድን ሊጠቁም የሚችለውን ጨዋታ በዳሰሳችን ተመልክተነዋል። ይህ ጨዋታ ለጅማ አባ ጅፋር የመርሐ ግብር ማሟያ ቢሆንም ለሲዳማ ቡና ግን እጅግ አስፈላጊ ነው። ቡድኑ ከዚህ ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ከቻለ ለከርሞው በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጥ ሲችል ወልቂጤ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ዕውን ይሆናል። በመሆኑም ተጠባቂነቱ ከጅማ ይልቅ ለወልቂጤ ያደላዝርዝር

የ23ኛውን ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ የተመለከቱ ነጥቦችን እንዲህ አንስተናል። የውድድር ሳምንቱ በመልካም ቁመና ላይ የሚገኘው ወላይታ ድቻን በሊጉ የመቆየት ተስፋው ከተመናመነው ጅማ አባ ጅፋር ጋር ያገናኛል። ካለፉት ሦስት ጨዋታዎች አምስት ነጥቦችን የሰበሰቡት ወላይታ ድቻዎች በሰንጠረዡ አጋማሽ ቢገኙም ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ደረጃቸውን ይበልጥ አሻሽለው ለመጨረስ ስለሚረዷቸው ካለብዙ ጨዋታ ሙሉ ነጥብ ለማሳካት ወደ ሜዳዝርዝር