መቐለ 70 እንደርታ (Page 38)

ሚካኤል ደስታ ከመከላከያ ጋር የነበረውን ቀሪ የአንድ አመት ውል በስምምነት አፍርሶ ወደ መቐለ ከተማ አምርቷል፡፡ ከ10 አመታት በኋላም ወደ መቐለ ተመልሷል፡፡ ሚካኤል በ1990ዎቹ ከመቐለው ክለብ ትራንስ ኢትዮጵያ ጋር የተሳኩ ጊዜያትን አሳልፎ በአዲሱ ሚሌንየም ወደ ኢትዮጵያ መድን ያመራ ሲሆን በ2002 ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ አምርቶ ሁለት የውድድር ዘመናት በፈረሰኞቹ ቤት አሳልፏል፡፡ ከ2004ዝርዝር

በዝውውር መስኮቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳተፈ የሚገኘው መቐለ ከተማ መድሀኔ ታደሰ እና ዮናስ ግርማይን አስፈርሟል፡፡ መድሀኔ ታደሰ ትራንስን ከለቀቀ ከ10 አመታት በኋላ በድጋሚ ወደ መቐለ የተመለሰበትን ዝውውር በማድረግ ለመቐለ ከተማ የ1 አመት ውል ፈርሟል፡፡ በትራንስ ኢትዮጵያ የተሳኩ አመታትን አሳልፎ በ1999 ወደ መከላከያ ያመራው መድሀኔ በ1997 የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አግቢ ከመሆኑዝርዝር

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ መቐለ ከተማ ሁለት ጋናዊያን እና አንድ የኢኳቶርያል ጊኒ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡ ኢኳቶሪያል ጊኒያዊው ግብ ጠባቂ ፊሊፔ ኦቮኖ ምባንግ ለመቐለ ከፈረሙት ተጫዋቾች መካከል ነው፡፡ ከ2009 ጀምሮ በዋና ቡድን ደረጃ እየተጫወተ የሚገኘውና ለሀገሩ 10 ጨዋታዎቸች ማድረግ የቻለው ምባንግ በሀገሩ ክለቦች ሶኒ ንጉኤማ እና ዴፖርቲቮ ሞኞሞ ከተጫወተዝርዝር

መቐለ ከተማ በክረምቱ የሚያደርገውን የዝውውር እንቅስቃሴ በማጠናከር ሶስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ሙሉጌታ ረጋሳ ፣ አለምነህ ግርማ እና ዮሴፍ ድንገቱ ለመቐለ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዮሴፍ ድንገቱ በወላይታ ድቻ 6 የውድድር ዘመናትን ማሳለፍ የቻለ ተጫዋች ሲሆን ክለቡ ከብሔራዊ ሊግ ጀምሮ ባሉት አመታት ባደረገው ጉዞ ከሚጠቀሱ ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ ነበር፡፡ዝርዝር

መቐለ ከተማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ አመለ ሚልኪያስን በአንድ አመት ኮንትራት የግሉ አድርጓል፡፡ አመለ ባለፈው የውድድር አመት ሀዋሳ ከተማን ለቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ አርባምንጭ ከተማ ካመራ በኋላ በተለይ ዘንድሮ በመጀመርያው ዙር መልካም እንቅስቃሴ ማድረግ የቻለ ሲሆን ከክለቡ ጋር የነበረውን ኮንትራት ማጠናቀቁን ተከትሎ ማረፊያውን መቐለ ከተማ አድርጓል፡፡ መቐለ ከተማ በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎዝርዝር

መቐለ ከተማ ያለፉትን 4 አመታት በሀዲያ ሆሳዕና ያሳለፈው ዱላ ሙላቱን በእንድ አመት ውል አስፈርሟል፡፡ የመስመር አጥቂው ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት መካከል ግንባር ቀደሙ እንደነበር የሚታወሰ ሲሆን በሊጉ ቆይታውም በግሉ ጥሩ ተንቀሳቅሷል፡፡ ዘንድሮም ከክለቡ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ ተቃርቦ በመጨረሻ ጨዋታ በመቐለ ከተማ ተሸንፈው ሳይሳካዝርዝር

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ መቐለ ከተማ ጫላ ድሪባ እና ታደለ ባይሳን የግሉ አድርጓል፡፡ ጫላ ድሪባ አዳማ ከተማን ለቆ የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በወልድያ ያሳለፈ ሲሆን ከበድሩ ኑርሁሴን ጋር በመፈራረቅ በወልዲያ አጥቂ መስመር ላይ ከአንዷለም ንጉሴ ጋር ሲሰለፍ ቆይቶ ኮንትራቱን በማጠናቀቁ ወደ መቐለ ተጉዟል ፡፡ ሌላው ለክለቡ የፈረመው ታደለ ባይሳ ነው፡፡ ከፋሲልዝርዝር

በ2010 የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ተሳታፊ የሚሆነው  መቐለ ከተማ የ16 ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ አንተነህ ገብረክርስቶስ እና ዳንኤል አድሀኖምን ያስፈረመው መቐለ የውድድር አመቱን በወሎ ኮምቦልቻ ያሳለፈው ግብ ጠባቂው ሙሴ ዮሀንስን 3ኛ የክለቡ ፈራሚ ሲያደርግ ራሱን ለቀጣይ አመት ውድድር አጠናክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ ተጫዋቾችን የማስፈረም እንቅስቃሴ እንደሚቀጥልዝርዝር

የ2009 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እጅግ ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ ድሬዳዋ ስታድየም ላይ ተደርጎ መቐለ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 2-1 በመርታት ለመጀመርያ ጊዜ ፕሪምየር ሊጉን ተቀላቅሏል፡፡ ይህን ወሳኝ ጨዋታ ለመከታተል በርካታ ተመልካች በድሬደዋ ስታድደም የታደመ ሲሆን በሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ህብረ ዜማ ታጅቦ ተካሂደል፡፡ በከተማው ከነበረው ከፍተኛ ሙቀት አንጻር በድንገት የጣለውና ጨዋታውንዝርዝር