ስሑል ሽረ

ሚካኤል ደስታ ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል

ላለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት መቐለ 70 እንደርታን በአምበልነት የመራው ሚካኤል ደስታ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ለስሑል ሽረ ፊርማውን አኑሯል። የእግርኳስ ሕይወቱን በመቐለ ጀምሮ ወደ ጣልያን በማምራት በሃገሪቱ የታዳጊ ቡድኖች ቆይታ አድርጎ በድጋሚ ወደ መቐለ ተመልሶ በትራንስ ኢትዮጵያ የክለብ እግርኳስ የጀመረው “ጣልያኑ” ለሰባት ዓመታት በትራንስ ቆይታ ካደረገ በኋላ በ2000 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መድን አቅንቷል። በመድን ለአንድ የውድድር […]

ስሑል ሽረ ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ስሑል ሽረ የ29 ዓመቱን ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ አስፈረመ፡፡ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለመጀመር ለተጫዋቾቻቸው የኮቪድ 19 ምርመራን ያደረጉት ስሑል ሽረዎች የዩጋንዳ ዜግነት ያለው ግብ ጠባቂ ብሪያን ብዌቴን በአንድ ዓመት ውል የክለቡ አራተኛ አዲስ ፈራሚ አድርገው ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል። የ29 አመቱ ይህ ግብ ጠባቂ በሀገሩ ክለብ ቢድኮ ቡል እና ዩአርኤ እንዲሁም በዲሪ ኮንጎው ቡካቩ ዳዋ የተጫወተ ሲሆን […]

ስሑል ሽረ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ባለፈው ሳምንት ወደ ዝውውር የገባው ስሑል ሽረ ሁለት ተጫዋች አስፈርሟል፡፡ ደሳለኝ ደባሽ ወደ ቀድም ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል፡፡ ይህ የቀድሞ የአዳማ ከተማ የአማካይ እና የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ስሑል ሽረን ከለቀቀ በኃላ የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በሰበታ ከተማ አሳልፎ በድጋሚ ወደ ስሑል ሽረ ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል፡፡ ሌላኛው የክለቡ ፈራሚ አጥቂው ዘካሪያስ ፍቅሬ ነው፡፡ ይህ የቀድሞው ሀላባ ከተማ፣ […]

የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ቅሬታን እያሰሙ ይገኛሉ

የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ለወራት የቆየው የደሞዝ ጥያቄያችን አልተመለሰም በማለት ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛል። በርካታ ክለቦች ከወርሀዊ የደመወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ ጥያቄ እየተነሳባቸው ይገኛል፡፡ ከነዚህም ክለቦች መካከል በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተወዳደረ የሚገኘው ስሑል ሽረ ተጫዋቾቹ ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ ተደጋጋሚ የይከፈለን ቅሬታን እያሰሙ ይገኛሉ። ቁጥራቸው በርከት ያሉ የክለቡ ተጫዋቾች “እስከ አሁን ምንም አይነት ደመወዝ እያገኘን አይደለም። ለክለቡን […]

“የዘመናችን ክዋክብት ገፅ” ከረመዳን የሱፍ ጋር…

በስሑል ሽረ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተሳኩ ጊዜያትን እያሳለፈ የሚገኘው ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ረመዳን የሱፍ የዛሬው የዘመናችን ክዋክብት ገፅ እንግዳችን ነው፡፡ ትውልድ እና ዕድገቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ተጫዋቾችን ለእግርኳሳችን እያበረከተ በሚገኘው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ውስጥ በምትገኝ አረብ ሰፈር ተብላ በምትጠራ ሰፈር ውስጥ ነው። ለስታዲየም አቅራቢያ በሆነችው ሰፈሩ ኳስን በማንከባለል የጀመረው የተጫዋችነት […]

“አብዛኛው የታዳጊነት ጊዜዬን ከዋናው ቡድን ጋር ማሳለፌ ብዙ ጠቅሞኛል” ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ዋልታ ዓንደይ

የስሑል ሽረው ተስፈኛ ግብ ጠባቂ የዛሬው የተስፈኞች ዓምድ እንግዳችን ነው። በተቀያሪ ወንበር ላይ በሚያሳያቸው እንቅስቃሴዎች በልዩ ይታወቃል። ቡድኑ የግብ እድሎች ሲያመክን ይቁነጠነጣል፤ በተጨማሪ ደቂቃዎችም ለቡድኑ ኳሶችን ለማቀበል ወዲያ ወዲህ ይላል። ለአሳዳጊ ክለቡ ልዩ ፍቅር እንዳለው የሚገልፀው የዛሬ እንግዳችን ዋልታ ዓንደይ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ጥቂት ጨዋታዎችም ተስፋ ያለው ግብ ጠባቂ እንደሆነ አስመስክሯል። በሽረ እንዳሥላሴ ተወልዶ በከተማዋ እግርኳስን […]

የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ጥያቄ እና የክለቡ ምላሽ

የስሑል ሽረ ተጫዋቾች የደሞዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ክለቡም ምላሹን ሰጥቷል። ከቀናት በፊት በቁጥር ጥቂት የማይባሉ የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ክለባቸው ደሞዛቸው እንዳልከፈላቸው እና በችግር ውስጥ እንዳሉ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀው ነበር። እንደ ተጫዋቾቹ ሀሳብ ክለቡ ያልከፈላቸው ደሞዝ እንዳለ እና። ከወቅታዊ የወረርሺኙ ሁኔታ ጋር ተደማምሮ ችግር ውስጥ እንዳሉ ገልፀው ክለቡ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በጉዳዩ ዙርያ ለሶከር ኢትዮጵያ ምላሻቸው […]

የዘመኑ ከዋክብት | ዳግም የተወለደው ዮናስ ግርማይ

የዘንድሮ የውድድር ዓመት እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ጥሩ እንቅስቃሴ ካሳዩት የመሐል ተከላካዮች አንዱ የነበረው ዮናስ ግርማይ የዛሬው የዘመኑ ከዋክብት አምድ እንግዳችን ነው። የእግር ኳስ ሕይወቱን በትራንስ ኢትዮጵያ ሦስተኛ ቡድን ጀምሮ በፕሪምየር ሊጉ ለሚገኙ በርካታ ክለቦች ተጫውቷል። በትራንስ ኢትዮጵያ የመጨረሻ ዓመታት በዋናው ቡድን ደረጃ መጫወት ጀምሮ በወቅቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ተከላካይ አሳዳጊ ክለቡ ከፕሪምየር ሊግ […]

ስለ ሙሉዓለም ረጋሳ ሊያውቋቸው የሚገቡ ዕውነታዎች

በኢትዮጵያ እግርኳስ እስካሁን ምትክ እንዳልተገኘለት የሚነገርለት የዘጠናዎቹ ኮከብ አንጋፋው የመሐል ሜዳው ንጉስ ሙላዓለም ረጋሳ (መካኒኩ) ማነው? ኳስሜዳ ካፈራቻቸው ፈርጦች አንዱ ነው። በ1989 ነበረ ለዓመታት የነገሰበትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ታዳጊ ቡድንን መቀላቀል የቻለው። በወቅቱ የፈረሰኞቹ ቁልፍ ተጫዋቾች ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ትራንዚት ለማድረግ ጣልያን ገብተው በመጥፋታቸው ለአንድ ዓመት ቆይታ ብቻ ካደረገበት የታዳጊ ቡድን በፍጥነት ወደ ዋናው ቡድን በ1990 […]

መብራህቶም ፍስሀ እና ያልተጠበቀው ሽግግር

ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ላይ ሳይጠበቅ ስድስት ዓመታት የተጫወተበት ክለብ ባቀረበለት ጥያቄ መሰረት ጫማውን ሰቅሎ ወደ አሰልጣኝነት ሥራ ገብቶ ቡድኑን በረዳት አሰልጣኝነት እያገለገለ ይገኛል። በሜዳ ውስጥ በሚያሳያቸው ስሜታዊ ባህርያት እና ተጫዋቾች የሚመራበት መንገድ የብዙዎች ትኩረት ስቦ የነበረው እና በቅፅል ስሙ ‘ጉንዲ’ በመባል የሚታወቀው  መብራህቶም ፍስሀ ስላልተገመተው ሽግግሩ እና ስለገጠሙት ፈተናዎች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top