ወልዲያ

አንዱዓለም ንጉሴ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወልዲያ አምርቷል፡፡ ከሙገር ሲሚንቶ የተገኘውና ለረጅም ዓመታት እየተጫወቱ ከሚገኙ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሰበታ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አጥቂ በ2009 እና 2010 በወልዲያ በግሉ ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በሁለተኛው ዓመትም ቡድኑን በአምበልነት መምራት ችሎ ነበር። በ2011 የውድድር ዘመን በወላይታ ድቻዝርዝር

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የልዑካን ቡድን አባላት በወልዲያ ከተማ በመገኘት የመሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ ስታዲየምን ጎበኝተዋል። ቡድኑ ጉብኝት ያካሄደው ስታዲየሙ የካፍን ጨዋታ የሚያስተናግድ መሆን አለመሆኑን እና የዓለም አቀፉን የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) መለኪያ መስፈርቶች ማሟላት አለማሟላቱን ለመገምገም ነው። በጉብኝቱ ላይ የሜድሮክ ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ አረጋ ይርዳው እናዝርዝር

ለወራት ከሜዳ የራቀው ተስፋዬ አለባቸው ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ እና ቀጣይ እቅዱ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል። በ2003 ሰበታ ከተማን ለቆ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካመራ በኋላ በክለቡ መልካም የውድድር ጊዜያት በማሳለፍ አምና ነበር ወልዲያን የተቀላቀለው። ሆኖም በአብዛኛዎቹ ጨዋታዎች በጉዳት ምክንያት ሳይጫወት የቀረ ሲሆን ሰኔ 9 ቀን 2010 ቡድኑ በጅማ አባ ጅፋር 2-0 ተሸንፎዝርዝር

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ተከናውነው ወልዲያ እና ኤሌክትሪክ ነጥብ ሲጥሉ ለገጣፎ በአሸናፊነቱ ገፍቶበታል። ባህር ዳር ላይ ለገጣፎ ለገዳዲን ያስተናገደው አውስኮድ 1-0 ተሸንፏል። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተዳክመው የታዩ ሲሆን የጠራ የግብ ማግባት ሙከራዎችንም ቡድኖቹ ለማስመልከት ሲቸገሩ ተስተውሏል። በ7ኛው ደቂቃ የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ የተስተናገደ ሲሆን በተጋባዦቹ ለገጣፎዎች በኩልዝርዝር

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ተከናውነው ወልዲያ ከሁለት ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ሲጥል ኤሌክትሪክ እና ለገጣፎ አሸንፈው ነጥባቸውን ከወልዲያ ጋር አስተካክለዋል።  ጎፋ አካባቢ በሚገኘው የልምምድ ሜዳው አማራ ውሀ ስራ (አውስኮድ)ን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1-0 አሸንፏል። የኤሌክትሪክን ብቸኛ የድል ጎል ያስቆጠረው ከሳምንታት በፊት ቡድኑን በውሰት የተቀላቀለው ተከላካዩ ዮሀንስ ዘገየዝርዝር

ምድብ ሀ እሁድ ኅዳር 23 ቀን 2011 FT ኤሌክትሪክ 1::0 አክሱም ከተማ 67 ‘ታፈሰ ተስፋዬ – FT ፌደራል ፖሊስ 0-0 አውስኮድ –  – FT ሰበታ ከተማ 2-0 ወሎ ኮምቦልቻ 4′ ኢብራሒም ከድር (ፍ) 42 ናትናኤል ጋንቹላ – FT አቃቂ ቃሊቲ 0-1 ወልዲያ – 73′ በረከት አፈወርቅ FT ገላን ከተማ 0-0 ለገጣፎዝርዝር

– በሁለቱ ክልል በሚገኝ ሜዳ የእርስ በእርስ ጨዋታ ከተደረገ 375 ቀናት ተቆጥሯል። በኢትዮጵያ የውስጥ ውድድሮች ባለፉት ሁለት ዓመታት የታየውን ያህል ፈታኝ ጊዜያት አሳልፎ አያውቅም። ለዓመታት ተንሰራፍቶ የቆየው የስታድየም ስርዓት አልበኝነት ከሀገሪቱ ተከስቶ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተደምሮ ወደ ፖለቲካዊ የብሔር ቅራኔ መልኩን በመቀየር ክስተቶችን በእግርኳሳዊ ህግጋት ለመዳኘት አስቸጋሪ ሲሆን ተስተውሏል። በእነዚህዝርዝር

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወረደውና በቀጣዩ የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊግ የሚሳተፈው ወልዲያ ስፖርት ክለብ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። 2009 የውድድር ዓመትን በዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጀምሮ በእገዳ ምክንያት በዘላለም ሽፈራው እየተመራ ያገባደደው ወልዲያ የቅጥር ማስታወቂያ በማውጣት አሰልጣኞችን አወዳድሮ በመጨረሻም አረጋዊ ወንድሙን መርጧል። አሰልጣኝ አረጋዊ ወንድሙ ከዚህ ቀደም በእህል ንግድ፣ ኢትዮጵያዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ሰበታ ላይ ወልዲያን የገጠመው ወላይታ ድቻ 3-0 አሸንፎ ከመውረድ የተረፈበትን ውጤት አስመዝግቧል። ከሌሎቹ ጨዋታዎች ጋር እኩል ለማስጀመር በኮሚሽነሮች መካከል የስልክ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን ከ3 ደቂቃ ቀደም ብሎ በተጀመረው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል መልኩ ወላይታ ድቻ የበላይነት የታየበት ነበር። ወልዲያዎች በአንዱዓለም ንጉሴ አማካኝነት በ5ኛውዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲጀምሩ አዲስ አበባ ላይ መከላከያ መውረዱን ያረጋገጠው ወልዲያን አስተናግዶ ሁለት ለምንም በሆነ ውጤት አሸንፏል። በቀዝቃዛማው የአዲስ አበባ ስታዲየም አየር በተከናወነው ጨዋታ የአንድ ቡድን የበላይነት የተስተዋለ ሲሆን በኳስ ቁጥጥርም ሆነ ወደ ጎል በመድረስ ባለሜዳዎቹ እጅግ ተሽለው ሲጫወቱ ታይቷል። መውረዱን ገና በጊዜ ያረጋገጠው እና በዛሬውዝርዝር