ሦስቱን የትግራይ ክልል ክለቦችን በተመለከተ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር አስተያየት ሰጥተዋል። የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተነሳው የፀጥታ ችግር ምክንያት በውድድሩ ያልተሳተፉት መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ እና ስሑል ሽረ በቀጣዩ ዓመት (2014) ወደ ሊጉ የመመለሳቸው ነገር እስካሁን መልስ ሳያገኝ ቀርቷል።Read More →

ሦስቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቤትኩንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ መሳተፍ ያልቻሉት መቐለ 70 እንደርታ ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ በቀጣይ ዓመት ለመሳተፍ በሚችሉበት ሁኔታ ዙርያ በቅርቡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ከተሾሙት አብርሀም በላይ (ዶ/ር)Read More →

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ከሦስቱ የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ባደረገው ውይይት ክለቦቹ በቀጣዩ የውድድር ዘመን የመሳተፍ ፍላጎታቸውን እንደገለፁ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው መረጃ ይህንን ይመስላል:- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከ3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ስለ ቀጣይ የውድድር ዘመን ተሳትፏቸው በተመለከተRead More →

ዘንድሮ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ሳይሳተፉ የቀሩት በትግራይ ክልል የሚገኙት ሦስቱ ክለቦች በአመራሮቻቸው በኩል ስብሰባ ሊቀመጡ ነው። መቐለ ሰባ እንደርታ፣ ወልዋሎ እና ሱሑል ሽረ በወቅታዊው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተሳታፊ አለመሆናቸውን ተከትሎ ሊጉ በአስራ ሦስት ክለቦች መካከል መካሄዱ ይታወቃል። በቀጣይ ዓመት ዳግም ወደ ውድድሩ ይመለሳሉ ወይስRead More →

በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተካፋይ ያልነበሩት መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ስሑል ሽረ በቀጣይ ዓመት ወደ ውድድር እንዲመለሱ በማሰብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ከክለቦቹ ጋር ግንኙነት መጀመሩ ተገልጿል፡፡ በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ በትግራይ ክልል የሚገኙት ሦስቱ ክለቦች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በሊጉ ሳይሳተፉ በመቅረታቸውRead More →

በ13 ክለቦች መካከል ለመደረግ የተቃረበው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወራጅ እና በ2014 ውድድር ለመሳተፍ ከከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ ክለቦች ስንት እንደሆኑ ታውቋል። በትግራይ ክልል መቀመጫቸውን ያደረጉት መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ እና ስሑል ሽረ በ2013 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የመሳተፍ እድል እጅግ ጠባብ መሆኑን ተከትሎ ሊጉን በበላይነት የሚያስተዳድረው የሊጉ አክሲዮንRead More →

በመቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ እና ስሑል ሽረ የሚገኙ ተጫዋቾችን የተመለከተ አዲስ የዝውውር ደንብ መውጣቱ ታውቋል። እንደ ስሑል ሽረ ሁሉ በ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመሳተፋቸው ነገር ያከተመ የሚመስለው መቐለ 70 እንድርታ እና ወልዋሎ ዓ/ዩ የያዟቸው ተጫዋቾችን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ሰንብቷል። በተለይ ክለቦቹ በሊጉ የማይሳተፉ ከሆነ የተጫዋቾቹ ቀጣይ ህይወትRead More →

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ አድርገው ስድስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ክለቡ ተጫዋቾቹ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን የኮቪድ 19 ምርመራ ከተደረገላው በኋላ ጥቅምት 17 ዝግጅት እንደሚጀምሩ ታውቋል። ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በወልዋሎ ስታዲየም እድሳት ምክንያት በመቐለ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ያካሄዱት ቢጫዎቹ ዘንድሮ ግን በከተማቸው ዓዲግራት ዝግጅት የሚጀምሩRead More →

“ለውጦች በማድረግ ክለቡን አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ግልፅነት የተሞላበት አሰራር ለማምጣት እየሰራን ነው። የክለባችን ቤተሰብም ጊዜ እንዲሰጠን እንጠይቃለን” አቶ ቴዎድሮስ ካሕሳይ አዲሱ የወልዋሎ ዓ/ዩ ምክትል ፕሬዝደንት ክለቡን ለረጅም ዓመታት ያገለገለው ሰለሞን ገብረፃዲቅ ህይወት ካለፈ በኃላ በሦስቱም ዓመታት የተለያዩ አመራሮች በመሾም እና በመሻር ለዓመታት የሚዘልቅ የተረጋጋ አወቃቀር መገንባት ያልቻሉት ወልዋሎዎችRead More →

ትውልድ እና እድገቱ በዓዲግራት ከተማ ነው። ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ተሰልፎ ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በቢጫ ለባሾቹ ቤት ተስፋ ከሚጣልባቸው ወጣቶች ተርታ እንዲመደብ አድርጎታል። በመስመር ተከላካይነት እና በመስመር ተጫዋችነት መሰለፍ የሚችለው ስምዖን ማሩ በተለይም በወልዋሎ ሁለተኛ ቡድን የተሳካ ጊዜ አሳልፏል። ባለፈው የውድድር ዓመትRead More →