Soccer Ethiopia

ዝክር

አፈወርቅ ኪሮስ እና ኃይሉ አድማሱ ስለአሰልጣኝ ሐጎስ ደስታ

ዛሬ እየዘከርናቸው የምንገኘው ሐጎስ ደስታን የአሰልጣኝነት ባህሪ፣ የተጫዋቾች አያያዝ እና የቡድን አገነባብ ሂደት አስመልክተን ካሰለጠኗቸው ተጫዋቾች መካከል አፈወርቅ ኪሮስ እና ኃይሉ አድማሱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዚህ መልኩ እናስነብባችኋለን። የአሰልጣኞችን የግል ስብዕናም ሆነ የሥራ ባህል ለመመስከር ከተጫዋቾች በላይ እማኝ ማግኘት ይከብዳል። አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች በዕለት ተዕለት የሥራ ግንኙነታቸው የሚያዳብሩት የመቀራረብ መንፈስ ማንነታቸውን በአግባቡ ለመረዳት በቀላሉ ይረዳቸዋል። […]

ምጥን ምስክርነት ስለማስተር ቴክኒሻን ሐጎስ ደስታ – ከደብሮም ሐጎስ እና ገነነ መኩሪያ

በህይወት ከተለዩ ዛሬ 20 ዓመት የሆናቸው የቀድሞው አሰልጣኝ ሐጎስ ደስታን ስብዕና በተመለከተ ከልጃቸው ደብሮም ሐጎስ እና ከጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ “ሊብሮ” ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። ኅዳር 07 ቀን 1993 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን አሰልጣኝ ሀጎስ ደስታን አስመልክተው በሥራቸው ያለፉ ተጫዋቾች እና የሙያ አጋሮቻቸው ብዙ ይላሉ። ዘመናዊነት በተላበሰው የቡድን ግንባታቸው እና በአሰለጣጠን ሂደታቸው የሚሞገሱት ሀጎስን ለማሰብ […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፲፩) | የታላቁ ሰው የባይተዋርነት ጊዜ

በህይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምን ጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን እያሰብን እንገኛለን። ለዛሬ የመንግሥቱ ወርቁን የስድስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማግስት ትውስታ እናነሳለን። ማስታወሻ ፡ በገነነ መኩሪያ በመፅሀፍ መልክ የተዘጋጀው ከመንግስቱ ወርቁ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ ፣ ‘ይድረስ ለባለንብረቱ’ የሚለው በፋንታሁን ኃይሌ ፣ ኃይማኖት ቃኘው እና ተዘራ አለነ […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፲) | “ታላቅ ስህተት…”

በሕይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምን ጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን እያሰብን እንገኛለን። የዛሬ ትኩረታችን ደግሞ ኢትዮጵያ በብዙ ተጠብቃበት ሳታሳካው በቀረችው ስድስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የነበረውን የመንግሥቱ ወርቁ ሚና ይሆናል። ማስታወሻ ፡ በገነነ ሊብሮ በመፅሀፍ መልክ የተዘጋጀው ከመንግሥቱ ወርቁ ጋር የተደረገው ሰፊ ቃለ ምልልስ ዋነኛ ግብዓታችን መሆኑን እንገልፃለን። […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፱) | አንድ ኮካ በመቶ ዶላር

በህይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምን ጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን እያሰብን እንገኛለን። የታላቁን የእግርኳስ ሰው ዕድገት ፣ የእግር ኳስ አጀማመር ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን ትውስታዎች እና የብሔራዊ ቡድን አስተዋፅኦን እያነሳንም ሰንብተናል። ዛሬ ደግሞ ከሜዳ ውጪ የተከሰተን አጋጣሚ እናነሳለን። ማስታወሻ ፡ ለዚህ ፅሁፍ ግብዓት የሆነን በፋንታሁን ኃይሌ ፣ […]

ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ሲታወሱ

መስከረም አንድ ቀን የተወለዱት ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ በህይወት ቢኖሩ ዛሬ 99ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ይከበር ነበር። ይህንን የታሪክ አጋጣሚ አስመልክተንም በዕለተ እሁድ በሕይወት የሌሉ የእግርኳስ ባለውለታዎችን የምንዘክርበት ዓምድን ወደ ዛሬ አሸጋሽገን ልንዘክራቸው ወደናል። የአንዳንዶች ስኬት ከመቃብር በላይ ከፍ ብሎ መታየቱ ብቻ ሳይሆን የትናንት ሥራቸውን በዛሬ መነፅር እንኳን ስንመዝነው እና በተመሳሳይ የሙያ መስክ ከሚገኙ የዛሬዎቹ ባለሙያዎቻችን […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፯) | መንግሥቱ ወርቁ ወይስ መንግሥቱ ነዋይ ?

በህይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምን ጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን እያሰብን እንገኛለን። የታላቁን የእግርኳስ ሰው ዕድገት ፣ የእግር ኳስ አጀማመር ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን ትውስታዎች እና የብሔራዊ ቡድን አስተዋፅኦን እያነሳንም ሰንብተናል። ዛሬ ደግሞ ታላቁ ስምንት ቁጥር ከሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ድል በኋላ ካሳደጉት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጋር የነበረውን አጭር […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፮) | ከጡጫ የተነሳችው ድልን ያወጀች ጎል በሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ

በህይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምን ጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን እያሰብን እንገኛለን። የታላቁን የእግርኳስ ሰው ዕድገት ፣ የእግር ኳስ አጀማመር ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን ትውስታዎች ፣ የብሔራዊ ቡድን አጀማመር እና የሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫን ትዝታ እያወሳን ቆይተናል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን ብቸኛ አህጉራዊ ድል ከመንግሥቱ ወርቁ ሚና ጋር አብረን […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፬) | ቅንጭብጫቢ ትውስታዎች ለፈገግታ

በህይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምን ጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን እያሰብን እንገኛለን። የታላቁን የእግርኳስ ሰው ዕድገት ፣ የእግር ኳስ አጀማመር ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን ቆይታ እና ከተክሌ ኪዳኔ ጋር ስለተፈጠረው ክስተት ባለፉት ሳምንታት አጫውተናችኋል። ዛሬ ደግሞ ለፈገግታም ዘመንን ለማነፃፀርም በማለት የታላቁን እግርኳሰኛ ቅንጭብ ገጠመኞች እናነሳለን። ማስታወሻ ፡ […]

መንግሥቱ ወርቁ ሲታወሱ (፪) | የክለብ ታማኝነት ፣ የ8 ቁጥር ቁርኝት ፣ የሜዳ ላይ ብቃት እና የውጪ ዕድል

በህይወት የሌሉ የእግርኳስ ሰዎችን በምናስታውስበት አምዳችን የቀድሞው እና በበርካቶች ዘንድ የምንጊዜውም ታላቅ እግርኳስ ተጫዋች እንደሆኑ የሚነገርላቸው መንግሥቱ ወርቁን ይዘን ቀርበናል። ታላቁን የእግርኳስ ሰው ማስታወስ በጀመርንበት ፅሁፉችን ከተወለደበት ቋራ ጀምሮ ቅዱስ ጊዮርጊስን እስከተቀላቀለበት ጊዜ ድረስ ስላሳለፈው ህይወቱ አስነብበናችኋል። ዛሬ ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዜውን፣ የሜዳ ላይ ክህሎቶቹን እና ወደ አውሮፓ ተሻግሮ ለመጫወት አጋጥሞት ስለነበረው ዕድል እናወሳለን። ማስታወሻ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top