በጠንካራ ግብጠባቂነቱ የሚታወቀው በሀገሪቱ ትልልቅ ክለቦች እስከ ብሔራዊ ቡድን ድረስ ለረጅም ዓመት ማገልገል የቻለው የቀድሞ ድንቅ ግብጠባቂ ሳዳት ጀማል ማነው? በኢትዮጵያ የግብጠባቂዎች አብዮት በተነሳበት ዘመን ከተገኙ ኮከብ ግብጠባቂዎች መካከል አንዱ ነው። በስልጤ ዞን ተወልዶ እስከ አምስት ዓመቱ ድረስ ይደግ እንጂ የዕድሜውን አብዛኛውን ዘመን የኖረው በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት ጡረታ ሠፈር በምትባልRead More →

ሜዳ ውስጥ ለለበሰው መለያ ሟች ነው። ሁሉን ሳይሳሳ አውጥቶ በመስጠት፣ በአልሸነፍ ባይነቱ፣ በታጋይነቱ እና በጠንካራ ሠራተኝነቱ ይታወቃል። ጥቂት በማይባሉ ክለቦች በነበረው የእግርኳስ ሕይወቱ በአመዛኙ በቋሚነት የተጫወተው ያልተዘመረለት የዘጠናዎቹ ኮከብ በቀለ እልሁ (እልሁ) ማነው ?  በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ውስጥ በቀደመውም ሆነ በአሁኑ ዘመን በርካታ ተጫዋቾችን እያፈራች መሆኗ ብዙም በማይነገርላት ቢሸፍቱ (ደብረRead More →

በሜዳ ላይ ቡድን ከመምራት ውጪ ከአንደበቱ ክፉ የማይወጣው እና በጣም የተረጋጋው ሰው እንደሆነ ብዙዎች የሚመሰክሩለት በዘጠናዎቹ ውስጥ ከተመለከትናቸው ድንቅ ግብ ጠባቂዎች መካከል የሚመደበው ጸጋዘአብ አስገዶም ማነው ? አስመራ ከተማ ውስጥ ወጣቶች ተሰባስበው በየቀበሌያቸው ውድድሮች የማድረግ ልምድ ነበራቸው። በአንድ የቀበሌ ተወካይ ቡድን ውስጥ ታዲያ ግብጠባቂው የቀን ስራ ያገኝና ኑሮን ለማሸነፍ ሲልRead More →

እርሱ የአንድ ቡድን የልብ ምት ነው። ሜዳ ውስጥ ካለ ከኃላም ከፊትም ያሉት የቡድን ጓደኞቹ ምቾት ይሰማቸዋል። በዘጠናዎቹ ውስጥ ከታዩ ድንቅ የተካከላካይ አማካይ መካከል አንዱ የሆነው ግዙፉ ተጫዋች አንተነህ አላምረውአሳልፏል። ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ በጦር ኃይሎች እና ልደታ መሀል በሚገኘው ቶሎሳ ሰፈር ነው። ለኳስ ተጫዋችነት መነሻ የሆኑት አባቱ ናቸው። እሱም በልጅነቱRead More →

በሁለቱም እግሩ ይጫወታል፤ በተጫወተባቸው ክለቦች ሁሉ ምርጡን አቋሙን አሳይቷል። የሜዳውን መስመር አልፎ ከገባ መሸነፍ የማይወድ ጀግና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በዘጠናዎቹ ከታዩ ኮከቦች መካከል ጌታቸው ካሣ (ቡቡ) ማነው ? ቄራ ቀበሌ ዘጠኝ አልማዝዬ ሜዳ ከፈጠረቻቸው ድንቅ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። በልጅነቱ ትልቅ ተጫዋች እሆናለው ብሎ ሳያስብ ከሠፈሩ ልጆች ጋር እግርኳስን መጫወትRead More →

ያመኑበትን ነገር በግልፅ ፣ በዕውቀትና በምክንያታዊነት ከሚናገሩ ተጫዋቾች በግንባር ቀደምትነት ይመደባል። ብዙዎች ባላሰኩት መንገድ ለሁለቱ የሸገር ደርቢ ቡድኖች በአምበልነት ተጫውቷል። በቀለም ትምህርቱ ማስተርሱን የያዘው በዘጠናዎቹ ከተፈጠሩ ድንቅ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ግዙፉ አንተነህ ፈለቀ ማነው ? በተወለደበት አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በሠፈር ውስጥ በመጫወት ጅማሮውን በማድረግ በኃላም በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃRead More →

የቀድሞ ድንቅ ተጫዋች እና በቅርቡ በህይወት ያጣነው ተስፋዬ ኡርጌቾ ታናሽ ወንድም ነው። አንድ አጥቂ ሊያሟላ የሚገባውን ነገሮች ሁሉ አሟልቶ እንደያዘ የሚነገርለት የዘጠናዎቹ ድንቅ አጥቂ ተከተል ኡርጌቾ ማነው? በኢትዮጵያ እግርኳስ የራሷን አሻራ አሳርፋለች። ብዙ እግርኳሰኞችን መፍጠር ችላለች፤ ቀድሞም ብቻ አልቀረም በዚህ ዘመንም በክህሎታቸው የዳበሩ ጥበበኞችም እየፈጠረች ትገኛለች። የምስራቋ ፈርጥ፣ በስኳር ምርቷRead More →

የመሰለውን ያለምንም ፍራቻ በግልፅ በመናገር ይታወቃል። በኢትዮጵያ እግርኳስ በርካታ ክለቦች ተዟዙሮ በመጫወት ወደር አይገኝለትም። እርሱ ከተጫወተባቸው ክለብ ይልቅ ያልተጫወተበት ክለብ መጥቀስ ይቀላል ይባልለታል። የዘጠናዎቹ ድንቅ የመስመር አጥቂና አማካይ ዘላለም ምስክር (ማንዴላ) ማነው? ከወታደር (ከአርበኞች) ቤተሰብ ነው የተወለደው። በወታደራዊ ሥነ-ስርዓት ተኮትኩቶ ማደጉ ረጅም ዓመታት ለመጫወቱ እና የተሰማውን ሥሜት ያለምንም ፍራቻ በግልፅRead More →

ከዘጠናዎቹ ወርቃማ ትውልድ አባላት መካከል ነው። ጥበበኛ እና ባለ አዕምሮ ተጫዋች ነው። በኢትዮጵያ እግርኳስ የችሎታውን ያህል ያልተዘመረለት ድንቁ አማካይ ኃይሉ አድማሱ (ቻይና) ማነው ? ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባልተጠበቀ ሁኔታ የለውጥ ዐብዮት ላይ ነው። የቀድሞ ድንቅ ተጫዋቾቹን እየቀነሰ ቡድኑን በወጣት ተጫዋቾች የመቀየር እንቅስቃሴ ላይ ተጠምዷል። በቀነሳቸው አስራ ሁለት ነባር ተጫዋቾች ምትክ ከታዳጊ ቡድኑRead More →

ኳስ በእግሩ ሲገባ ቀንሶ አልፎ ከሮጠ እርሱን ማቆም አዳጋች ነው፤ በትልልቅ ክለቦች በዋንጫ የተጀበ የስኬት ዓመታትን አሳልፏል፤ ብዙ መጫወት እያቻለ በአሳዛኝ ሁኔታ በድንገት በጉዳት ሳይጠገብ እግርኳስን ለማቆም ተገዷል። አጥቂ እና ተከላካይ በመሆን ሲጫወት የምናውቀው የዘጠናዎቹ ጀግና ይልማ ተስፋዬ (ካቻማሊ) ማነው? የጣልያኑ የከባድ መኪኖች አምራች የሆው አይቬኮ ኩባንያ የሚያመርተውና አርባ አምስትRead More →