በሀገራችን እግርኳስ ስላለው የአበረታች መድኃኒቶች ቁጥጥር ተከታዩን ፅሁፍ አዘጋጅተናል። በእግርኳስ ውስጥ ጨዋታን ፍትሃዊ ማድረግ ከዋና የውድድሩ መርሆች መካከል ዋናው ነው፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥ ከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከል አበረታች መድኃኒቶች ላይ የሚደረግ ቁጥጥር አንዱ ነው፡፡ የእግርኳስ የበላይ አካል የሆነው FIFA ከዓለም አቀፍ የፀረ-አበረታች መድኃኒት ባለስልጣን (WADA) ጋር አንድ ላይ በመሆን ሰፊ ሥራዎችን እየሰራRead More →

ወቅቱ ክለቦች አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረሙ የሚገኙበት እንደመሆኑ የተጫዋቾችን ጤንነት በተመለከተ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦችን በዚህ ፅሁፍ አንስተናል። የ2014 የውድድር ዘመን መጠናቀቅን ተከትሎ ክለቦች በስፋት በዝውውር መስኮት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ዝውውሮች ግን ምን ያህል በህክምና ምርመራ የተደገፉ እና የተጫዋቾቹን ጤንነት ግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው የሚለው ጉዳይ ጥያቄን ያስነሳል፡፡ በፕሮፌሽናል ደረጃ አንድRead More →

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″] ከእግር ኳስ መሰረታዊ አካላት መካከል አካል ብቃት አንዱ ነው። በተለይም በእግር ኳስ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ በቻሉት ሀገራት ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበት እንመለከታለን። በሀገራችን ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ በተለያዩ ጊዜያት ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል። ይህንን ነገር ይዘን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአካል ብቃት አሰልጣኝ የሆኑት ዶ/ር ዘሩ በቀለን አናግረናል። *Read More →

እግር ኳስ ውስጥ የሚያጋጥሙ ጉዳቶችን እና የጤና እክሎችን ከነመፍትሄዎቻቸው በምንዳስስበት የሶከር ሜዲካል አምዳችን በዛሬው ዕለት የምንመለከተው በሜዳ ውስጥ የሚያጋጥሙ የቁስል እና የመድማት አደጋዎችን እና የሚታከሙበትን መንገድ ይሆናል፡፡ የመድማት እና የመቁሰል አደጋዎች በእግር ኳስ ተዘውትረው ከሚያጋጥሙ አደጋዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይም በታዳጊዎች እግር ኳስ ውስጥ ከሚያጋጥሙ ጉዳቶች በአራተኛ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ እነዚህRead More →

በእግር ኳስ ውስጥ የሚከሰቱ ጉዳቶች እና ህመሞችን በምንቃኝበት የሶከር ሜዲካል አምዳችን ከዚህ ቀደም የድንገተኛ የልብ ድካም ምንነትን እና ተያይዘው የሚያጋጥሙ የጤንነት እከሎችን መዳሰሳችን የሚታወስ ነው፡፡ በዚህኛው ጽሁፍ ደግሞ የህክምና መፍትሄዎችን የምንመለከት ይሆናል፡፡ አንድ ተጫዋች ለልብ ህመም ችግር ተጋላጭ መሆኑን ለማወቅ የልብ ምርመራ አይነት የሆነውን ECG መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን ምርመራRead More →

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ትናንት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር የገለፀውን የተጫዋቾች የጤና ምርመራ ዝርዝር ጉዳዮች የፌዴሬሽኑ የህክምና ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ ለሶከር ኢትዮጵያ አብራርተዋል። በአቶ ኢሳይያስ ጂራ የሚመራው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሀገሪቱን እግርኳስ ለማሳደግ ያለሙ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ቀናት በተሰማ መረጃRead More →

በእግር ኳስ ውስጥ የሚያጋጥሙ የተለያዩ የጤና እከሎችን በምንበለከትበት በሶከር ሜዲካል ዓምድ የዛሬው ትኩረታችን የሚሆነው ድንገተኛ የሆነ የልብ ድካም እንዴት መከላከል እና ማከም እንደሚቻል ነው፡፡ የልብ ህመም ተዘውትረው ከሚታዩ እና ከፍተኛ ጉዳት ከሚያስከትሉ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በተፈጥሮም ሆነ ከሚያደርጓቸው ጫና የበዛበት እንቅስቃሴ አንጻር ለእነዚህ ህመሞች ተጋላጭ ናቸው፡፡Read More →

እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሚያጋጥማቸው እከሎች ዋንኛው በከባድ ጉዳት ምክንያት ከሜዳ ዘለግ ላለ ጊዜ መገለል ነው፡፡ ይህም በአዕምሮ ጤናቸው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው፡፡ ከሜዳ በራቁ ቁጥር ብቸኝነት እና ድባቴ ሊሰማቸው ይችላል፡፡ በዛሬው የሶከር ሜዲካል አምዳችን የምንመለከተው ይህንን ጉዳይ ነው፡፡ ከበድ ያሉ ጉዳቶች በሚያጋጥሙበት ወቅት ወደ ሜዳ ለመመለስ የሚደረጉት ስራዎች ጊዜንRead More →

Anterior Cruciate Ligament አልያም ACL በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ጉዳት ከሚያጋጥማቸው ጅማቶች መካከል አንዱ ነው። ተጫዋቾች ከሜዳ ለረጅም ወራት እንዲርቁም ያስገድዳል። በዛሬው የሶከር ሜዲካል አምዳችን ስለዚህ ጅማት ይህንን ፅሁፍ አዘጋጅተናል። በምስሉ ላይ እንደሚታየው ACL በጉልበታችን በፊተኛው በኩል የሚገኝ ጅማት ሲሆን ከአጥንቱ ክፍል የlater condyle በስተግራ ተነስቶ የtibial spine በስተቀኝ ላይRead More →

ከዚህ በፊት በነበረው የሶከር ሜዲካል ፅሁፋችን በእግር ኳስ ተጫዋቾች የአዕምሮ መዛል መንስኤዎች መካከል የሆነውን መዋቅራዊ ተፅዕኖ ተመልክተናል። በዚህኛው ፅሁፍ ደግሞ ከስነ ልባና ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጫናዎችን እንመለከታለን። አትሌቲክ በተሰኘው የእግር ኳስ ድረ ገፅ የሰፈረውን ” we need to talk about mental burnout in football.” እንደ ግብዐት ተጠቅመናል።  ሥነ ልቦናዊ ጫናዎችRead More →