ከፍተኛ ሊግ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ የሚገኘው ስልጤ ወራቤ አዲስ አሰልጣኝ በይፋ ቀጥሯል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሐ ከተደለደሉ አስራ ሁለት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ስልጤ ወራቤ ያለፉትን ሦስት አመታት በወጣቱ አሰልጣኝ አብዱልወኪል አብዱልወሀብ እየተመራ መዝለቁ ይታወሳል፡፡የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በምድቡ በ24 ነጥቦች 9ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ክለቡ በቀጣዩ የ2014 የከፍተኛ ሊግ ውድድርዝርዝር

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚወዳደረው ኢትዮጵያ መድን የቀድሞ አሠልጣኙን ዳግም ቀጥሯል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው የሊግ እርከን (ከፍተኛ ሊግ) የሚወዳደረው ኢትዮጵያ መድን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በምድብ ሐ 35 ነጥቦችን በመያዝ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በአሠልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመራ ያለፈውን የውድድር ዓመት ያሳለፈው ክለብ ከአሠልጣኙ ጋር ከተለያየ በኋላ የቀድሞ አሠልጣኙን ወደ መንበሩ መልሷል።ዝርዝር

የተሳታፊ ቁጥር መፋለስ ያጋጠመው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በቀጣዩ ዓመት በምን መልኩ ይካሄዳል፣ በ2013 የውድድር ዘመን ወደ አንደኛ ሊግ ወርደው የነበሩ ክለቦችስ በከፍተኛ ሊጉ ይቀጥላሉ ወይንስ አይቀጥሉም የሚለው ጉዳይ በቅርቡ እልባት ያገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በሦስት ምድቦች ተከፍሎ የ2013 የውድድር ዘመን ሲደረግ ቆይቶ መከላከያ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማን ወደዝርዝር

የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና የከፍተኛ ሊግ የዝውውር መከፈቻ ቀን መቼ እንደሆነ ይፋ ተደርጓል። የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከሐምሌ ወር መጀመሪያ አንስቶ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከፕሪምየር ሊጉ ባሻገር የሚደረጉት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና የከፍተኛ ሊግ የዝውውር መስኮት እስከ አሁን ሳይከፈቱ የሰነበቱ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን የኢትዮጵያዝርዝር

የማሟያ ውድድሩ የመጨረሻ መርሐ-ግብር የሆነው የሀምበሪቾ እና ኤሌክትሪክ ጨዋታ አራት ግቦች ተቆጥረውበት በኢትዮ ኤሌክትሪክ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለአዳማ ከተማ ሦስት ነጥብ አስረክበው ለዛሬው ጨዋታ የቀረቡት ሀምበሪቾዎች አራት ለውጥ በማድረግ ጨዋታውን ጀምረዋል። በዚህም አሠልጣኝ ግርማ ታደሠ ሮቦት ሰለሎ፣ ዋቁማ ዲንሳ፣ ዳግም በቀለ እና አቤኔዘር ኦቴን አሳርፈው ብሩክ ኤልያስ፣ በረከት ወንድሙ፣ ፀጋአብዝርዝር

ወልቂጤ ከተማ ሦስት ግቦችን አስቆጥሮ ኮልፌ ቀራኒዮን ከረታበት ጨዋታ በመቀጠል ሁለቱም አሰልጣኞች የድህረ ጨዋታ ሀሳባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ጳውሎስ ጌታቸው – ወልቂጤ ከተማ ስለጨዋታው “ጨዋታው እንዳያችሁት ከባድ ነበር፡፡ምክንያቱም ሁለቱም ቡድኖች ኳስን ይዘው የሚጫወቱ ቡድኖች ስለሆኑ። በአጠቃላይ ግን ከጨዋታ በስተጀርባ እዚህ ድረስ የመጡ ደጋፊዎቻችን ማመስገን እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ከፕሪምየር ሊግ ወጥተናል ብለውዝርዝር

የትግራይ ክልል ክለቦችን ለመተካት የሚደረገው የማሟያ የመጨረሻ ጨዋታ በተመሳሳይ ሰዓት ከተደረጉ እና በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ በተከወነ መርሐግብር ወልቂጤ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮን 3-0 በመርታት አዳማን ተከትሎ ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በጅማ አባ ጅፋር ተረተው ወደ ዛሬው ጨዋታ የመጡት ኮልፌ ቀራኒዮዎች በአንድ ተጫዋች ላይ ብቻ ለውጥ አድርገዋል፡፡ በቅያሬውም ሀቢብ ከሚል ወጥቶ ክንዱዝርዝር

በተመሳሳይ ሰዓት ከሚደረጉ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው እና በሰው ሰራሹ ሜዳ የሚከወነው ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመግባት ዕድል ባላቸው ሁለት ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ወቅታዊ መረጃዎችን አጠናቅረናል፡፡ በአንፃሩ በጅማ አባ ጅፋር ሽንፈት አስተናግደው ወደ ዛሬው መርሐግብር ብቅ ያሉት የአሰልጣኝ መሀመድኑር ንማዎቹ ኮልፌ ቀራኒዮች ከባለፈው ጨዋታ ተሰላፊዎች ውስጥ ሀቢብ ከማልን በክንዱ ባየልኝዝርዝር

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ዳሞት ከተማ፣ ቡራዩ ከተማ፣ እንጅባራ ከተማ እና አምቦ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል። ከረፋድ ጀምሮ በአዳማ አበበ በቂላ ስቴዲየም ሲካሄድ በዋለው የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች በመጀመርያ ያገናኘው አምቦ ከተማ እና የአዲስ ከተማን ነበር። በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አልፎዝርዝር

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከምድብ ሐ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን ላረጋገጠው አርባምንጭ ከተማ ሽልማት ተበረከተለት፡፡ በነቀምት ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ውድድርን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ወደ 2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ማለፉን ያረጋገጠው የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ትናንት የደቡብ ክልል መቀመጫ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ሲደርስ በማርሽ ባንድ በታገዘዝርዝር