Soccer Ethiopia

ሀዲያ ሆሳዕና

ሀድያ ሆሳዕና ሁለት የውጪ ዜጋ ተከላካዮችን አስፈረመ

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በርካታ ዝውውሮችን ከፈፀሙ በኋላ ከነባሮቹ ጋር በማቀናጀት ያለፉትን ሳምንታት በሆሳዕና ከተማ ቅድመ ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ሀድያ ሆሳዕናዎች ሁለት የውጪ ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾች ወደ ክለቡ አምጥተዋል። የመጀመሪያው ፈራሚ ከአራት ዓመታት በኃላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው አይዛክ ኢሴንዴ ነው፡፡ የሀገሩን ክለብ ቪክቶርን ለቆ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመቀላቀል […]

የቀድሞው የፌዴሬሽኑ ፀኃፊ የሀድያ ሆሳዕና ረዳት አሰልጣኝ ሆኑ

ዶክተር ኢያሱ መርሐፅድቅ የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ረዳት በመሆን ተሹመዋል፡፡ ዶ/ር ኢያሱ በ1990ዎቹ አጋማሽ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ በቴክኒክ ኮሚቴ አባልነት እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ ክለብ በአማካሪነት የሰሩ ሲሆን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲም በመምህርነት እና የስፖርት ዲን በመሆን ከሰሩ በኃላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመስራት አሳልፈዋል። አሁን ደግሞ ወደ አሰልጣኝነቱ ብቅ […]

የዘመናችን ከዋክብት ገፅ | ቆይታ ከዳዋ ሆቴሳ ጋር…

በዛሬው የ”ዘመናችን ከዋክብት” ገፅ ላይ ፈጣኑን አጥቂ ዳዋ ሆቴሳን እንግዳ አድርገነዋል። በምዕራብ ጉጂ ቀርጫ ከተማ ተወልዶ ያደገው ዳዋ እንደማንኛውም ታዳጊ በልጅነቱ ኳስን አዘውትሮ ይጫወት ነበር። በተለይ ተጫዋቹ ከመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት የሚገኝ የመጫወቻ ሜዳ ላይ ውሎውን ያደርግ እንደነበር ያስታውሳል። በሰፈር ውስጥ የሚገኙትን እኩዮቹን እጅግ በልጦ የሚታየው ዳዋ ራሱን በተሻለ ደረጃ የሚያሳይበትን ዕድል በትምህርት ቤቶች ውድድር […]

ሀዲያ ሆሳዕና የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

ስንታየው ታምራት እና በረከት ወልደዮሐንስ ውላቸውን አድሰዋል፡፡ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ በረከት ወልደዮሐንስ አርባምንጭ ከተማን ለቆ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ጅማሮ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዲያ ሆሳዕና ተመልሶ ያሳለፈ ሲሆን የአንድ ዓመት ውሉን በማጠናቀቁ ለተጨማሪ ዓመት ግልጋሎት ለመስጠት ተስማምቷል፡፡ ከደደቢት ተስፋ ቡድን የተገኘው ስንታየው ታምራት ሌላው ውሉን ለተጨማሪ ዓመት በነብሮቹ ቤት ለመቆየት የተስማማ ነው፡፡ ይህ ግብ ጠባቂ በተሰረዘው […]

የሀዲያ ሆሳዕና ተጫዋቾች ቅሬታ…

ባለፈው ዓመት ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ቆይታ የነበራቸው ተጫዋቾች ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን አሰሙ። ተጫዋቾቹ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት መጀመርያ አከባቢ ከቡድኑ በጎ ምላሾች እያገኙ ደሞዛቸውን በመጠባበቅ ቢቆዩም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የክለቡ አመራሮች በደሞዙ ዙርያ ለመነጋገር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። እስከ አራት ወር የሚጠጋ ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዝ እንዳለ የገለፁት የቡድኑ ተጫዋቾች በዚህ ሰዓት በችግር ውስጥ መሆናቸው ሲገልፁ […]

ለሀዲያ ሆሳዕና ለመፈረም ተስማምቶ የነበረው መሳይ አያኖ በሲዳማ ቡና ውሉን ዛሬ አራዘመ

ትናንትት ወደ ሆሳዕና ለማምራት ተስማምቶ የነበረው ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ በሲዳማ ቡና ውሉን አራዝሟል፡፡ ደቡብ ፖሊስን ከለቀቀ በኃላ ከ2010 ጀምሮ ለሲዳማ ቡና በመጫወት ላይ የሚገኘው ተጫዋቹ ዘንድሮ ውሉ በሲዳማ ቤት መጠናቀቁን ተከትሎ ለመቀጠል ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ከጥቅማ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ መግባባት ሳይችል በመቅረቱ ሆሳዕና ተገኝቶ ለሀዲያ ሆሳዕና ለመጫወት የአንድ ዓመት ቅድመ ስምምነትን መፈፀሙን […]

ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ሀዲያ ሆሳዕናን ለመቀላቀል ተስማሙ

ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ እና አማካዩ ብሩክ ቃልቦሬ ወደ ሀድያ ሆሳዕና ለማምራት ከስምነት ደርሰዋል፡፡ የቀድሞው አርባምንጭ ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ ግብ ጠባቂ መሳይ አያኖ በአንድ ዓመት ውል ሆሳዕናን ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡ ደቡብ ፖሊስን ከለቀቀ በኃላ ከ2010 የኢትዮጵያ የውድድር ዓመት ጀምሮ ለሲዳማ ቡና በመጫወት ላይ የሚገኘው ተጫዋቹ ዘንድሮ ውሉ በሲዳማ ቤት መጠናቀቁን ተከትሎ ከሰሞኑ በክለቡ ሲዳማ ለመቀጠል […]

ሀዲያ ሆሳዕና ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ሀዲያ ሆሳዕና የቀድሞ የአዳማ ከተማ ተጫዋቾችን ማሰባሰቡን በመቀጠል አጥቂው ዳዋ ሆቴሳ እና ግብ ጠባቂው ደረጄ ዓለሙን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡ በናሽናል ሲሚንት እና ኦሊምፒክ ቡድን ባደረገው እንቅስቃሴ የብዙዎች ዕይታ ውስጥ የገባው ፈጣኑ አጥቂ ዳዋ ሆቴሳ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማምራት ሁለት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈ ሲሆን በመቀጠል በአዳማ ከተማ ጥሩ ቆይታን ማድረግ ችሏል። የአዳማ ቆይታው በመጠናቀቁም የተነሳ አሰልጣኝ አሸናፊ […]

ሀዲያ ሆሳዕና ሦስት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማማ

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ምኞት ደበበ፣ አበበ ጥላሁን እና አማኑኤል ጎበናን በማስፈረም ተስማማ፡፡ የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና የመሐል ተከላካይ አበበ ጥላሁን ባለፉት ሁለት ዓመታት በመከላከያ በመጫወት አሳልፏል፡፡ ከፋሲል ከነማ ጋር ስሙ በስፋት ሲያያዝ የነበረው ይህ ተከላካይ ሆሳዕናን በአንድ ዓመት ውል ከደቂቃዎች በፊት ተቀላቅሏል፡፡ ሌላኛው ወደ ነብሮቹ ያመራው አማኑኤል ጎበና ነው፡፡ […]

ሀዲያ ሆሳዕና የጋናዊውን አጥቂ ውል አራዝሟል

ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ቢስማርክ አፒያ በነብሮቹ ቤት ውሉን ለማደስ ተስማምቷል። በ2010 ክረምት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጅማ አባ ጅፋርን የተቀላቀለውና መስመር አጥቂነት እንዲሁም በመሐል አጥቂ ስፍራ ላይ ተሰልፎ መጫወት የሚችለው ጋናዊው ቢስማርክ አፒያ ጅማን ለቆ በስሑል ሽረ በ2011 የውድድር ዘመን በመጫወት ካሳለፈ በኃላ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቅሎ መጫወት ችሏል፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ ያልተሳካ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top