Soccer Ethiopia

ሀዲያ ሆሳዕና

መድሀኔ ብርሀኔ ከስሑል ሽረ ተለያይቶ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቷል

ባለፈው ክረምት ስሑል ሽረን የተቀላቀለው መድሀኔ ብርሃኔ ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቷል። ከደደቢት ጋር የተሳካ ዓመት ካሳለፈ በኋላ በክረምቱ ዝውውር መስኮት የመጨረሻ ቀን ስሑል ሽረን የተቀላቀለው ሁለገቡ መድሀኔ ብርሀኔ በስሑል ሽረ ቆይታው መስመር ተከላካይነት ፣ በመስመር ተጫዋችነት እና በፊት አጥቂነት መጫወት የቻለ ሲሆን በሊጉ የመጀመርያ ሳምንታት ቡድኑን በቋሚነት ቢያገለግልም ቆይቶ ባልታወቀ ምክንያት […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 0-1 መቐለ 70 እንደርታ

በአብዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደ የ16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለዎች ከሜዳቸው ውጪ ሀዲያ ሆሳዕናን 1-0 ከረቱ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል። “ከሜዳችን ውጭ አሸንፈን መውጣታችን ዕድለኛ ያደርገናል” ገብረመድህን ኃይሌ (መቐለ 70 እንድርታ) ከሜዳችሁ ውጭ አሸንፋችኋል። የጨዋታው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ? ጨዋታው ከባድ ነበር። ምክንያቱም እነርሱ ላለመውረድ እየተጋሉ ነው ያሉት እኛ ደግሞ ከፊት […]

ሪፖርት| መቐለ ከሜዳው ውጭ ወሳኝ ነጥብ ሲያሳካ ሆሳዕና የመውረድ አደጋ ተጋርጦበታል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛው ዙር የመጀመርያ ጨዋታውን ከቅጣት መልስ በአብዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና 1-0 ሽንፈት አስተናግዷል። በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው መቐለ እና ላለመውረድ የሚታገለው ሀዲያን ያገናኘው ይህ ሁለት መልክ ያለው ጨዋታ ከሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ይልቅ የጨዋታው ትኩረት የሚስቡ የነበሩ የተለያዩ ክስተቶች ተፈጥረዋል። በዙ ሳቢ ያልነበረው እና ረጃጅም ኳሶች በበዙበት […]

ሀዲያ ሆሳዕና ከ መቐለ 70 እንደርታ – ቀጥታ የውጤት መግለጫ

እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 FT ሀዲያ ሆሳዕና 0-1 መቐለ 70 እ. – 59′ ኦኪኪ አፎላቢ ቅያሪዎች 60′ ሱራፌል / ፍራኦል 78′ ዮናስ / ሙሉጌታ 69′ በኃይሉ / ሱራፌል ጌ 81′ ካሉሻ / ኤፍሬም – – ካርዶች 30′ በኃይሉ ተሻገር 36′ ቢስማርክ ኦፖንግ  36′ ሄኖክ አርፊጮ 45′ ታሪክ ጌትነት 45′ አማኑኤል ገብረሚካኤል 53′ አሚን ነስሩ […]

ቅድመ ዳሰሳ| ሀዲያ ሆሳዕና ከ መቐለ 70 እንደርታ

ሀዲያ ሆሳዕና ከቅጣት መልስ በአብዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታን የሚገጥሙበት ጨዋታን እንደሚከተለው ተመልክተነዋል። አዲስ አሰልጣኝ ከቀጠሩ በኋላ በጥሩ መነሳሳት ላይ የሚገኙት ነብሮቹ በቅጣት ምክንያት ሁለት የሜዳቸውን ጨዋታዎች ሀዋሳ ላይ ካደረጉ በኋላ ወደ ሜዳቸው በሚመለሱበት ጨዋታ ጥሩ ጉዟቸውን በማስቀጠል ሦስት ነጥብን ለማግኘት አልመው ይገባሉ ተብሎ ይገመታል። የሀዲያ ሆሳዕና ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ […]

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር ክለቦች ዳሰሳ – ሀዲያ ሆሳዕና

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር በባለፈው ሳምንት መጀመሪያ መጠናቀቁን ተከትሎ ክለቦች በተናጥል መዳሰሳችንን ቀጥለን የመጀመሪያውን ዙር በ13 ነጥብ ግርጌውን ይዞ ያጠናቀቀው ሀዲያ ሆሳዕናን የአጋማሽ ጉዞ ተመልክተናል። የመጀመሪያ ዙር ጉዞ በ2011 ከከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተቀላቀሉት ሦስት ቡድኖች አንዱ የሆነው ሀዲያ ሆሳዕና ለሊጉ አዲስ አይደለም። በ2008 ፕሪምየር ሊግ የተሳተፈው ሆሳዕና በወቅቱ ያሳደጉት አሰልጣኝ […]

ሀዲያ ሆሳዕና ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ትናንት ሳሊፉ ፎፋናን በማስፈረም ወደ ዝውውር የገባው ሀዲያ ሆሳዕና አሁን ደግሞ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋችች አስፈርሟል። ቢኒያም ሲራጅ እና ተስፋዬ አለባቸውም አዲስ ፈራሚ ሆነዋል። ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ወላይታ ድቻን ተቀላቅሎ መልካም ጊዜ በክለቡ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ተስፋዬ አለባቸው በድቻ ለመቆየት በቃል ደረጃ በመስማማቱ ውሉን እንደሚያራዝም ቢጠበቅም ማረፊያው ሀዲያ ሆሳዕና ሆኗል። የቀድሞው የሰበታ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ […]

ሀዲያ ሆሳዕና አይቮሪኮስታዊውን አጥቂ አስፈረመ

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሁለተኛው ዙር ፈራሚ ተጫዋች በማድረግ አይቮሪኮስታዊው የስሑል ሽረ አጥቂ ሳሊፍ ፎፋናን አስፈርመዋል፡፡ ዐምና በዚህ ወቅት ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ የነበረው እና ክለቡ በሊጉ እንዲቆይ ከረዱ ተጫዋቾች መካከል ግንባር ቀደሙ የነበረው ሳሊፍ ፎፋና ከቀናት በፊት ውሉ በመጠናቀቁ ወደ ተለያዩ ክለቦች ያመራል ቢባልም ማረፊያው ሀዲያ ሆሳዕና መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ለቀጣዩ 1 ዓመትም […]

ሀዲያ ሆሳዕና ወልቂጤን ይቅርታ ጠየቀ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ላይ ባደረጉት ጨዋታ ለተፈጠረው ችግር ሆሳዕና ይቅርታ ጠይቋል። በወልቂጤ 2-1 አሸናፊነት በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ በተፈጠረ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ፌዴሬሽኑ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ጨዋታ ከሜዳው ውጪ እንዲያከናውን መቅጣቱሚታወስ ሲሆን ቅጣቱንም በዚህ ሳምንት ጨርሷል። ክለቡም ለወልቂጤ ከተማ በፃፈው ደብዳቤ ይቅርታ ጠይቋል። ደብዳቤ-

የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 1-0 ጅማ አባ ጅፋር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስራ አምስተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ በሆነው እና ሀዲያ ሆሳዕና የቅጣቱ የመጨረሻ ጨዋታውን ሀዋሳ ላይ አድርጎ ጅማ አባ ጅፋርን 1ለ0 ከረታ በኋላ የሁለቱ ቡድን ዋና አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተውናል። “ካጠገባችን ካሉ ክለቦች እንዳንርቅ ነጥቡ አስፈላጊ ስለነበር ተባብረን በጋራ አሳክተነዋል” ፀጋዬ ኪ/ማርያም (ሀዲያ ሆሳዕና) ስለ መጀመሪያ ድል እና ጨዋታው ቡድኑን […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top