ዐበይት ጉዳዮች

የውድድር ዘመኑ የማሳረጊያ በነበረው የጨዋታ ሳምንት የታዘብናቸው አሰልጣኝ ነክ ጉዳዮች በዚህኛው ፅሁፋችን ተዳሷል። 👉 የቅድመ እና ድህረ ጨዋታ አስተያየቶች ሊጋችን የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ማግኘቱን ተከትሎ አሰልጣኞች ከጨዋታዎች መጀመር አስቀድሞ እና መጠናቀቅ በኃላ ቅድመ ጨዋታ እና ድህረ ጨዋታ አስተያየቶችን በዘመነ ሱፐር ስፖርት እየተመለከትን እንገኛለን። እርግጥ ድህረ ጨዋታ አስተያየቶች በሀገራችን እግርኳስ ባለፉትዝርዝር

የውድድር ዘመኑ መጋረጃ መዝጊያ በነበረው 26ኛ የጨዋታ ሳምንት የተመለከትናቸው የትኩረት ማዕከል የነበሩ ተጫዋቾች የሁለተኛው ፅሁፋችን አካል ናቸው። 👉 ሐት-ትሪክ ሠሪው አማካይ – ሐይደር ሸረፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጨረሻው የጨዋታ ሳምንት መውረዱን ያረጋገጠውን ወልቂጤ ከተማን 3-2 ሲረቱ አማካዩ ሐይደር ሸረፋ የትኩረቶች ሁሉ ማዕከል ነበር። በ2013 የውድድር ዘመን የመጀመሪያው ሐት-ትሪክ የሠራ የአማካይ ተጫዋችዝርዝር

የ2013 የውድድር ዘመን ተጠናቋል። በመጨረሻው የጨዋታ ሳምንት ትኩረትን የሳቡ ዓበይት የክለብ ትኩረቶችንም እነሆ ብለናል። 👉 የፋሲል ከነማ ቀጣይ የቤት ሥራ በ2009 የውድድር ዘመን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደጉበት ጊዜ አንስቶ ፋሲል ከነማ በሊጉ ከፍተኛ እምርታን እያሰየ ይገኛል። የዘንድሮው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻሉት ዐፄዎቹ በብዙ መመዘኛዎች ፍፁም የተዋጣለት የውድድርዝርዝር

በ25ኛ የጨዋታ ሳምንት ትኩረታችንን የሳቡ አሰልጣኝ ነክ ጉዳዮች እና ዓበይት አስተያየቶች የሦስተኛው ትኩረታችን ክፍል ናቸው። 👉 ባለውለታውን በክብር ያመሰገነው ሙሉጌታ ምኅረት የወቅቱ የሀዋሳ ከተማ ዋና አሰልጣኝ የሆነው የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድንቅ አማካይ ሙሉጌታ ምህረት በ25ኛ የጨዋታ ሳምንት ቡድን ከፋሲል ከነማ ጋር ካደረገው ጨዋታ ጅማሮ አስቀድሞ ለቀድሞውዝርዝር

ሊጠናቀቅ አንድ የጨዋታ ሳምንት በቀረው የ2013 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 25ኛ የጨዋታ ሳምንት የተጫዋች ትኩረታችንን እነሆ ብለናል። 👉 ሳልሀዲን በርጌቾ ወደ ሜዳ ተመልሷል ባለፉት ጥቂት የውድድር ዘመናት ከቅዱስ ጊዮርጊስ መደበኛ ተሰላፊ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሳልሀዲን በርጌች የተሰረዘው እና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የዘንድሮው ውድድር ዘመን በእግርኳስ ህይወቱ ፈታኞቹ ነበሩ ብሎዝርዝር

የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ መጠናቀቁ ቃርቧል። ከመጨረሻው ሳምንት አስቀድሞ በተካሄደው የ25ኛ የጨዋታ ሳምንት የተመለከትናቸውን ከለቦች ላይ ያተኮሩ ጉዳዮችንም በተከታይ መልኩ ለመዳሰስ ሞክረናል። 👉 ዐፄዎቹ በመጨረሻም ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል በ22ኛ የጨዋታ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያለግብ መለያየትን ተከትሎ ከወልቂጤ ከተማ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ሳያደርጉ የሊጉ አሸናፊ መሆናቸውንዝርዝር

የመጨረሻው የትኩረታችን ክፍል ሌሎች ትኩረት የሚገባቸው ጉዳዮች በተከታዩ መልክ ተዳሰውበታል። 👉 የተሻለው ነገርግን ይበልጥ መሻሻል የሚገባው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መጫወቻ ሜዳ  በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር እስካሁን በአራት የተለያዩ ከተሞች ተደርጎ አሁን ላይ በአምስተኛዋ አዘጋጅ ከተማ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ጅማሮውን ካደረገ ሦስተኛ የጨዋታ ሳምንቱ ላይ ደርሷል።  ላለመውረድ እንዲሁም ለሁለተኝነት በሚደረገው ፉክክር ወሳኝ የሆኑትንዝርዝር

በ24ኛ የጨዋታ ሳምንት የታዘብናቸው ትኩረት የሳቡ አሰልጣኝ ነክ ጉዳዮች እና ዓበይት አስተያየቶች የሦስተኛው የፅሁፋችን አካል ናቸው። 👉 ባለውለታቸውን ያልዘነጉት ኢያሱ መርሐፅድቅ (ዶ/ር)  አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከሀዲያ ሆሳዕና አመራሮች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከሥራ መታገዳቸውን ተከትሎ ኃላፊነቱን የተረከቡት የእሳቸው ረዳት የነበሩት ኢያሱ መርሐፅድቅ (ዶ/ር) ቡድኑ በዚህኛው የጨዋታ ሳምንት በታዳጊ ተጫዋቾቻቸው ድንቅ ብቃትዝርዝር

በ24ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተደረጉ ጨዋታዎች የታዘብናቸው ትኩረት የሳቡ ተጫዋች የሁለተኛው ፅሁፋችን አካል ናቸው። 👉ትንሹ ልዑል ክብረወሰኑን በእጁ አስገብቷል  ስለዚህ ታዳጊ የተሰለቹ የአድናቆት ቃላት መደርደር የእሱን የዘንድሮ አስደናቂ ብቃት ማሳነስ እንጂ እሱን ሊገለፅ የሚችል ቃል ፈልጎ ማግኘት እጅግ ከባድ ሆኗል። ይህ ከእድሜው በብዙ ርቀት የቀደመው በሳል አጥቂ በ2009ዝርዝር

የቻምፒዮኖቹ ያለመሸነፍ ጉዞ በተገታበት እንዲሁም ለሁለተኝነት እና ላለመውረድ የሚደረገው ፉክክር በርትቶ በቀጠለበት 24ኛው የጨዋታ ሳምንት የተመለከትናቸው ክለብ ነክ የትኩረት ጉዳዮች የመጀመሪያው ፅሁፋችን አካል ናቸው።  👉 የዐፄዎቹ ያለመሸነፍ ጉዞ መገታት በ2ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ፋሲል ከነማዎች ከ45 ያላነሱ ደቂቃዎች በጎዶሎ የተጫዋች ቁጥር በተጫወተው ኢትዮጵያ ቡናዝርዝር