Soccer Ethiopia

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

ወልዋሎዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ አድርገው ስድስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ክለቡ ተጫዋቾቹ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን የኮቪድ 19 ምርመራ ከተደረገላው በኋላ ጥቅምት 17 ዝግጅት እንደሚጀምሩ ታውቋል። ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በወልዋሎ ስታዲየም እድሳት ምክንያት በመቐለ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ያካሄዱት ቢጫዎቹ ዘንድሮ ግን በከተማቸው ዓዲግራት ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል። እስካሁን ድረስ ዓወት ገብረሚካኤል፣ […]

በወልዋሎ እየተደረጉ ስላሉ ለውጦች የክለቡ ም/ፕሬዝዳንት ይናገራሉ

“ለውጦች በማድረግ ክለቡን አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ግልፅነት የተሞላበት አሰራር ለማምጣት እየሰራን ነው። የክለባችን ቤተሰብም ጊዜ እንዲሰጠን እንጠይቃለን” አቶ ቴዎድሮስ ካሕሳይ አዲሱ የወልዋሎ ዓ/ዩ ምክትል ፕሬዝደንት ክለቡን ለረጅም ዓመታት ያገለገለው ሰለሞን ገብረፃዲቅ ህይወት ካለፈ በኃላ በሦስቱም ዓመታት የተለያዩ አመራሮች በመሾም እና በመሻር ለዓመታት የሚዘልቅ የተረጋጋ አወቃቀር መገንባት ያልቻሉት ወልዋሎዎች አሁንም ለውጦች ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በተወሰኑ […]

” ትልቁ እቅዴ ከምወደው ክለቤ ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ማንሳት ነው” ስምዖን ማሩ

ትውልድ እና እድገቱ በዓዲግራት ከተማ ነው። ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ተሰልፎ ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በቢጫ ለባሾቹ ቤት ተስፋ ከሚጣልባቸው ወጣቶች ተርታ እንዲመደብ አድርጎታል። በመስመር ተከላካይነት እና በመስመር ተጫዋችነት መሰለፍ የሚችለው ስምዖን ማሩ በተለይም በወልዋሎ ሁለተኛ ቡድን የተሳካ ጊዜ አሳልፏል። ባለፈው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ አማካኝነት ወደ […]

የወልዋሎ ተጫዋቾች ጥያቄ እና የክለቡ ምላሽ

የወልዋሎ ተጫዋቾች የደሞዝ አልተከፈለንም ጥያቄ ሲያቀርቡ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ ምላሽ ሰጥተውናል። ከሦስት ሳምንታት በፊት ገደማ የወልዋሎ ተጫዋቾች የደሞዝ ጥያቄ እንዳላቸው እና ከወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ተዳምሮ ችግር ውስጥ እየገቡ እንዳሉ ጠቅሰው ነበር። በቁጥር በርከት ካሉ ተጫዋቾች የተነሳው ይህ የደሞዝ ጥያቄ ምንም እንኳ በክለቡ ጆሮ ዳባ ልበስ ባይባልም አብዛኞቹ ተጫዋቾች ውላቸው በቀጣይ ወራት የሚጠናቀቅ […]

ተስፈኛው የመሐል ተከላካይ ዳዊት ወርቁ …

” በትልቅ ደረጃ መጫወት እፈልጋለሁ” ትውልድ እና እድገቱ ባህር ዳር ከተማ፣ ህዳር 11 የተባለ ሰፈር ነው። እግር ኳስን በፉትቦል ባህርዳር ጀምሮ በታዳጊ ቡድን ደረጃ በአውሥኮድ እና ደደቢት የተጫወተው ይህ ተከላካይ በዚህ ወቅት በወልዋሎ የሚገኝ ሲሆን በተከላካይ ቦታ ላይ ተስፋ ካላቸው ተጫዋቾ አንዱ ነው። የአማራ ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ መኖርያ ካደገበት መንደር በቅርብ ርቀት መኖሩ እግር […]

“የዘመኑ ኮከቦች ገፅ” ከሳሙኤል ዮሐንስ ጋር…

የቢጫዎቹቹ ቁልፍ ተጫዋች ሳሙኤል ዮሐንስ የዛሬው የዘመናችን ኮከቦች እንግዳ ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሊጉ በግራ መስመር ተከላካይ ላይ ከታዩት ድንቅ የማጥቃት ባህሪ ያላቸው ተከላካዮች አንዱ ነው። ሐረር ከተማ የተወለደውና በሐረር እና ባህርዳር ያደገው ሳሙኤል በልጅነቱ ያሳለፈው እጅግ አስቸጋሪ ጊዜ ሁኔታዎችን ፈታኝ ቢያደርግበትም እግርኳስ ተጫዋች ከመሆን አላገደውም። በ2007 ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተስፋ ቡድን በማምራት በቀጣዩ […]

ወልዋሎዎች ድጋፍ አድርገዋል

የወልዋሎ እግርኳስ ክለብ ለዓዲግራት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለደረሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከል በርካታ ድጋፎች እየተደረጉ መቆየታቸው ይታወሳል አሁን ደግሞ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩንቨርስቲ እግርኳስ ክለብ፣ የክለቡ የአሰልጣኞች ቡድን አባላት እና የፅህፈት ቤት ሰራተኞች በጋራ 165,000 (አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) ድጋፍ አድርገዋል። ክለቡ ካደረገው […]

ወልዋሎዎች አማካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ሄኖክ ገምቴሳ የአማካይ ክፍል ተጫዋች በማፈላለግ ላይ ወደሚገኙት ወልዋሎዎች ለማምራት ተቃርቧል። ከዚህ በፊት በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ሥር በፋሲል ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር የተጫወተው ሄኖክ ባቀረበው የመልቀቂያ ጥያቄ መሰረት ቀሪ የስድስት ወር ውል እያለው ከጅማ አባጅፋር ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን ዝውውሩ በተሳካ ሁኔታ የሚያጠናቅቅ ከሆነ በርካታ አማካይ ላስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ ተጨማሪ ግብአት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። […]

ፀጋአብ ዮሴፍ ሳይፈርም ቀርቷል

ከወልዋሎ ጋር ልምምድ ጀምሮ ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ፀጋአብ ዮሴፍ ሳይፈርም ቀርቷል። ከቀናት በፊት ወደ ዓዲግራት አምርቶ ከወልዋሎ ጋር ልምምድ በመጀመር በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው አማካዩ ፀጋአብ ዮሴፍ ዝውውሩ ባልታወቀ ምክንያት ተጨናግፏል። የውድድር ዓመቱ ከሲዳማ ጋር ጀምሮ ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ጋር የተለያየው ይህ የቀድሞ የፋሲል ከነማና የሀዋሳ ከተማ አማካይ በመጀመርያው ዙር ካለቡድን […]

ወልዋሎ አማካይ ለማስፈረም ተቃርቧል

ከወልዋሎ ጋር ልምምድ የጀመረው ፀጋአብ ዮሴፍ ወደ ክለቡ ለማምራት ተቃርቧል። በውድድር ዓመቱ መጀመርያ ወደ ሲዳማ ቡና ፈርሞ ለሳምንታት ከቡድኑ ጋር ቆይታ ካደረገ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ጋር የተለያየው ይህ ተጫዋች ላለፉት ቀናት ከወልዋሎ ጋር ልምምድ እየሰራ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በይፋ ፌርማን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን ወጥቶ ለአሳዳጊው ክለቡ ዋና ቡድን እና ፋሲል […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top