ውድድሮች (Page 2)

ከክልል ክለቦች ሻምፒዮና ወደ 2014 አንደኛ ሊግ ያለፉ ክለቦች በዛሬው ዕለት ሙሉ ለሙሉ ተለይተው ሲታወቁ የሩብ ፍፃሜ መርሀ ግብርም ተከናውኗል፡፡ የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የ2013 የውድድር ዓመት በሀዋሳ ከሐምሌ 18 ጀምሮ በአርባ ስድስት ክለቦች መካከል እየተደረገ ሰንብቶ ከቀናቶች በፊት ስምንት ክለቦች ወደ ኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ መግባታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ተሸናፊ የነበሩዝርዝር

ለአምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የምስል መብት የገዛው ሱፐር ስፖርት ከደቡብ አፍሪካ በሚያመጣቸው ባለሙያዎች ለክለቦች ስልጠና ሊሰጥ ነው። ግዙፉ የቴሌቪዥን ተቋም ሱፐር ስፖርት የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሊግ እርከን (ፕሪምየር ሊግ) ውድድርን ከ2013 ጀምሮ ለአምስት ዓመታት በቀጥታ ለማስተላለፍ የቴሌቪዥን መብቱን በጨረታ ተወዳድሮ መግዛቱ ይታወቃል። ከምስል መብቱ በተጨማሪ የስያሜ መብቱንም የግሉ አድርጎ ለቤትኪንግዝርዝር

በትናንትናው ዕለት የቀጣይ ዓመት የሊጉ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ጥያቄ ያቀረቡ ስታዲየሞችን ምልከታ ማድረግ የጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ዛሬ ወደ አዳማ አምርቶ ግምገማ አድርጓል። የ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለማስተናገድ ጥያቄ ካቀረቡ ስታዲየሞች መካከል ቀዳሚው የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በትናንትናው ዕለት በሊጉ የበላይ አክሲዮን ማኅበሩ በተቋቋመው ኮሚቴ ምልከታ እንደተደረገበት እና ማሻሻያ በሚያስፈግላቸው ጉዳዮችዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የበላይ የሆነው አክሲዮን ማኅበሩ ዛሬ ወደ ሀዋሳ አቅንቶ ከዩኒቨርስቲው አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል። የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመዝጊያ አምስት የጨዋታ ሳምንታትን አስተናግዶ የነበረው የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የቀጣይ ዓመት ውድድርንም ዳግም ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቡን ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበርም የቀጣይ ዓመት ውድድርን ለማስተናገድዝርዝር

የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ እየተደረገ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ደርሷል፡፡ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ስምንት ክለቦች ወደ አንደኛ ሊጉ መግባታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ተሸናፊዎቹ እርስ በእርስ ተጫውተው አራት ክለቦች የሚለዩበት መርሐግብር ረቡዕ ነሐሴ 5 በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሌጅ ሜዳ ጨዋታቸው ይከውናል፡፡ ይህን ጨዋታ የሚያሸንፉ አራት ክለቦች ስምንቱን ቀድመው ማለፋቸውን ያረጋገጡ ክለቦችን ተከትለውዝርዝር

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአስር ክለቦች መካከል በሀዋሳ ሲደረግ የነበረው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚያድጉ ክለቦችን ለመለየት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተደረገ ያለው ይህ ውድድር ከቀናቶች በፊት አላፊ ስድስት ቡድኖች ተለይተው የታወቁ ሲሆን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ትላንት በሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ ተከናውነው ቀሪዎቹ ሁለት ቡድኖቹምዝርዝር

በሀዋሳ ከተማ እየተደረገ ባለው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከሰዓት በተደረጉ አራት ጨዋታዎች ወደ አንደኛ ሊግ ያደጉ ተጨማሪ አራት ቡድኖች ተለይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ ከሐምሌ 18 ጀምሮ በአርባ ስድስት ክለቦች መካከል እየተደረገ ዘልቆ ወደ መገባደጃው ደርሷል፡፡ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ አስራ ስድስት ውስጥ የገቡ ቡድኖች ጨዋታቸውንዝርዝር

ከሰዓታት በፊት እያሱ ለገሠን የግሉ ያደረገው ጅማ አባጅፋር አሁን ደግሞ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል። ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ተስፋዬ መላኩ ነው። የቀድሞው የወላይታ ድቻ፣ ኤሌክትሪክ እና ሀዋሳ ከተማ ሁለገብ ተጫዋች የሆነው ተስፋዬ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት በወልቂጤ ከተማ ቆይታ ያረገ ሲሆን አሁን ደግሞ በ2011 ተጫውቶ ወዳሳለፈበት ጅማ አባ ጅፋር አምርቷል።ዝርዝር

በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ረፋድ በተደረጉ ጨዋታዎች አራት ክለቦች ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ቀደም ብል ጠዋት 2፡00 ሲል የአማራ ክልሉ ቡሬ ዳሞት ከኦሮሚያው ዱከም ከተማ ተገናኝተው ዱከም ከተማዎች 1ለ0 ረተው ወደ አንደኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ቀጥሎ 4፡00 ሲል ቡሳ ከተማ እና ቦዲቲዝርዝር

👉”የቀጣይ ዓመት ውድድር ዝግጅትን በተመለከተ እስካሁን ከክለቡ የደረሰኝ ምንም አይነት መልዕክት የለም” እስማኤል አቡበከር (አሠልጣኝ) 👉”ዓምናም ዘገያችሁ ስንባል ነበር። ግን የእኛ ክለብ በስልት ነው ሁሉን ነገር የሚያደርገው” ነፃነት ታከለ (ሥራ-አስኪያጅ) በ2013 የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሁለት ተደልድሎ በ51 ነጥቦች ወደ ዋናው የሀገሪቱ የሊግ እርከን ማደጉን ያረጋገጠው አዲስ አበባዝርዝር